ቢዘገይም አይከፋም –  ማላጂ

November 17, 2020
7 mins read
tplf empire

በህዝቦች የዕርስ በርስ ትስስር እና አብሮነት ፤ መኖር በእጅጉ ዕንቅልፍ የሚነሳዉ የታችአምናዉ የነጻነት ታጋይ(ትሕነግ) የትናንቱ መንግስት እና የዛሬዉ ዳግም ነጻ አዉጭ ለዓመታት የአንድን አገር ህዝብ ጠላት እና ወዳጅ በማድረግ ወዳጁን የሚደጉምበት ጠላቱን የሚጎዳበት አንዱ እና ዋነኛዉ ኢፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እና ፍሰት በማድረግ ነበር ፡፡

ለዚህም እንደዋና ስልት የተጠቀመባቸዉን መንገዶች ወደ ኋላ መመልከት አስካሁን ለነበረዉ በአገር ሀብት እና ንብረት ብዙዉን የበይ ተመልካች ያደረገ የመድሎ ኢኮኖሚ አገሪቷን እና ዜጎቿን ለአሳዛኝ ድህነት፣  ርሃብ፣ ስደት ፣ሞት እና ቸነፈር ዳርጓል፡፡

በዚኅች አገር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መንግስታዊ አስተዳደር የነበረዉን ጥግ የነካ አድሎ እና መድሎ የነበረበት ብሄራዊ ችግር ለታሪክ እና ለትዉልድ መተዉ እንጅ በባከነ ተዉልድ እና ጊዜ ሌላ ብክነት መጨመር ይሆናል ፡፡

የሖነ ሁኖ  ለሀገር እና ህዝብ ደህንነት ስጋት ከሆኑት ኃይሎች ጋር በገንዝብ እና መሰል ድጋፍ ይታማሉ በተባሉት 34 -ሠላሳ አራት- የንግድ እና አገልግሎት ተቋማት ላይ የሂሳብ ዝዉዉር ዕግድ በኢትዮጵያ ዐቃቤ ህግ መዉጣቱን ሰማን ፤ተመለከትን ፡፡

እርምጃዉ የዘገየ ቢሆንም አይከፍም ምክነያቱም “ሀረጉን ሲስቡ ዛፍ ይወዛወዛል” እና ለህዝብ ሞት እና ለአገር ጥፋት የሚዉል የገንዘብ ምንጭን ለመቀነስ አማራጭ በመሆኑ በጀ የሚባል ነዉ ፡፡

ነገር ግን ከረጅም ዓመታት አስቀድሞ ከህዝብ ወደ ግል ህብት የተዘዋወሩ እና በአንድ ድርጅት እና አባር ድርጅቶች ስም የሚገኙ የቀድሞ መንግስት ግዙፍ የልማት ድርጅቶች የት ገቡ በማን እና እንዴት እንደሚተዳደሩ አስከምን ድረስ እንደምናዉቅ ባላዉቅም ጤነኛ ዝዉዉር (Privatization ) እንዳልነበር እንዴት እና በማን ይመሩ ፤ይዘወሩ እንደነበር ስለሚታወቅ ነጻ ናቸዉ ማለት ይሆን ፡፡

ከዚህ ጋር በተዬያዘ ሁለት መሰረታዊ ቁም ነገር ማንሳት ይኖርብናል ፡-

  • የመንግስት እና የህዝብ የነበሩ ሠፋፊ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል የተዘዋወሩበት እና ተከታታይ ሁነቶች( ከ1990.ዓ.ም አስከ 2008 .ዓ.ም) ፡

በኢትዮጵያ የመንግስት እና ህዝብ ሀብት እና ንብረት የነበሩት ምን አልባት ከ1940ዎች ዓ.ም. ጀምሮ የዉጭ እና የአገር ዉስጥ ባለሀብቶች የለሙ በ1967 ዓ.ም ወደ መንግስት/ህዝብ ሀብት የተዛወሩ(Nationalized ) በኋላም ከ1990 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ  ወደ ግል ይዞታ እንዲዛወሩ የተደረጉት ሰፋፊ እርሻ(የቡና እርሻዎች እነ ፤ በበቃ፣ ቴፒ፣ ሊሙ……..)ማዕድን፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ……ወዘተ. የሚገኙበት በግል ተቋማት ስም ማን እየዘወራቸዉ እና እያዘዘባቸዉ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነዉ ፡፡

ሆኖም በአይነት እና መጠናቸዉ ብዙ የአገር ሀብት የሆኑት እና ለህዝብ አገልግሎት እና ጥቅም ሊሰጡ የሚችሉት የጥቂቶች የማይነጥፍ የገንዝብ ምንጭ መሆናቸዉ እየታወቀ ለዚህ በመሳሪያነት አስፈጻሚ የሆነዉ የግል ይዞታ አስፈጻሚ ተቋም(Privatization Agency ) የስራ ኃላፊዎች እና በተከታታይ የተሾሙት እና የተነሱት ምንአልባትም በምዝበራ (ሙስና) ስም ይሁን በሌላ በተከታታይ መሆኑ አንድ ፍንጭ ነዉ ፡፡ ከዚህም በላይ የመንግስት እና ህዝብ የልማት ድርጅቶችን ሆነ አዳዲስ ልማት ጅምሮችን በሚመለከት የነበረ ችግር እና የአገሪቷን እና ህዝቧን የልማት እና ዕድገት  ዕንቅፍት መሆን የሚያሳየን የችግሩ ምንጭ እና ባለቤት ሁሉ ነገር በግል እና ቡድን ትስስር እና ጥቅም ላይ የተመረኮዘ እንደነበር ነዉ ፡፡ የግል ድርጅት አስፈታሚ ተቋም ኃላፊ የነበሩትም ፡-

  • አቶ በሻህ አዝምቴ
  • አቶ ግዛዉ ወ/ማርያም(መሀንዲስ )
  • አቶ አሰፋ አብርሃ

የሚጠቁሙት በዚህች አገር የነበረዉን  በግላጭ በአገር እና ህዝብ ሀብት እና ንብረት የተደረገዉን እና እየጠሰራበት ያለዉን የተደራጀ የኢኮኖሚ ሻጥር አመላከች ነዉ ፡፡

2ኛ) ከ 1997 ዓ.ም. ምርጫ አስከ 2007 ዓ.ም ለፖለቲካ ማስፈጻሚያ እና ህዝብን በህዝብ በማነሳሳት የስልጣን እና የህዝብ ሀብት ቅርምት ለማስፋፋት በገንዘብ ምንጭነት የሚያገለግሉ እና በግል ድርጅት ስም የሚገኙ በህዝብ እና አገር ላይ የዕኩይ ተግባር ማስፈፀሚያነት የተገለገሉ እና የሚገለገሉ መኖራቸዉ ሊታለፍ አይገባም ፡፡

ያልተጠቀሱት ከተጠቀሱት 34 ድርጅቶች በስያሜ ካልሆ በባለቤትነት፣ በምግባር እና በተግባር አንድ የሆኑ ብዙ ስለሚኖሩ እና ይህም በ1997.ዓ.ም ብሄራዊ ምርጫ ማግስት እንዲሁም በ2006 -2007.ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ቴፒ/ሜጢ) በነበር አሰቃቂ የዜጎች ዕልቂት እና መፈናቀል ሚና የተጫወቱ ዛሬም ከዚህ የተለየ ምግባር ሊኖራቸዉ አይችልም እና ለአገር እና ለህዝብ ደህንነት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ፡፡

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

1 Comment

  1. መላ የትግራይ ህዝብ እንዲዘምት ዶክተር ደብረፂዮን ጥሪ አቀረቡ፡፡
    “ጦርነቱን ማፍጠን ይጠይቃል፣ ውጊያ በመግለጫ አይመራም! አስጊ ነው ያሉት የአማራ ልዩ ሀይል ከሞትና ከመበታተን ታደጋቸው”- ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Opinion
Previous Story

ከሕዝብ እውነተኛ ፍላጎቶች መማር ብልኅነት ነው – አምባቸው ደጀኔ

Next Story

ከኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ ፤በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop