ከምክክር ፓርቲ አገር አድን ለውጥ አቅጣጫን ያመላከተ መግለጫ

ቁጥር Ref.No ም/ለአ/ለዴ/ፓ/003/2013 ዓ.ም
ቀን  Date መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም

የሕገ መንግሥት ለውጥ – ለኢትዮጵያ የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው

ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት መልክ ያለው ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱና ተግባራዊ የማድረጉ ራዕይ ለሐገራችን ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው፡፡ ከጽንፈኛነት፤ ከዘረኛነትና ከጭቆና የተላቀቀ ኢትዮጵያዊነት እንዲጠናከር ምክክር ፓርቲ አበክሮ የሚታገልለት አጀንዳ ነው፡፡በመሆኑም፡-

  1. የአሁኑ ሕገ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጫነው የህውሀት ተጠያቂዎች አንደኛው ዓላማቸው ሕዝቡ በዘረኛነት እርስ በርስ እንዲናቆርና እንዲጨፋጨፍ ስለ ነበር ያለሙት ሁሉ እየተሳካላቸው ነው፣ እንዲሁም በዘረኛነት ሥርዓቱ ኢትዮጵያ በድህነትና በሙስና ታዋቂ እንድትሆን አድርገዋታል። በተጨማሪም፤ በብዙ ዓለም-አቀፋዊ መስፈርቶች ኢትዮጵያ የዓለም ጭራ በመሆንዋ ተመጽዋች ሀገር ሆናለች። በመንግስት ሚዲያ የምትነገረዋ ኢትዮጵያ እኛ የማናውቃት ሀገር እየሆነች መጥታለች፣ሀሰትን ማዳመጥ አድምጦ ዝም ማለት ከተባባሪነት ስለማይለይና ነገ ከታሪክ ተወቃሽነት ስለማያድን ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳን ስለ እውነት ትግላችንን አጠናክረን እንታገላለን፡፡
  2. አሁኑ በስራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ሕዝቡን በቋንቋና በጠባብ ዘረኛነት በተመሠረተ የክልል ሥርዓት ከፋፍሎ ባስከተለው የእርስ በርስ መናቆር፤ መከፋፈል፤ አለመተማመን፣ ለአንድነት አለመተባበር እጅግ አሰቃቂ እልቂትና መጠነ ሰፊ ቀውስ እያስከተለ በመሆኑ የአንድነት ሀይሉ ሊተባበርና አብሮ ሊሰራ ግድ የሚለው በመሆኑ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ፓርቲ አገርን ከውድቀት ለማዳን አብረን ልንሰራ የሚገባ በመሆኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
  3. በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ እትዮጵያውያን ልብ ሊሉት የሚገባው በዘረኛነት ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ብዙ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። ኢትዮጵያውያን በዓረብ ሐገሮች ጭምር በዝቅተኛ ደረጃ ለመኖር ተገደዋል።በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል። በጠባብ ጎሰኛነት መለያየት ምክንያት እጅግ ብዙ ንብረት ወድሟል። አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት አወቃቀርና ሥርዓት፤ “ክልል” የተሰኙ አንዳንድ አካባቢዎችም ለመገንጠል እያኮበኮቡ ያለበትን ሁኔታ ያለ በመሆኑ ሕገ መንግስቱ ኢትዮጵያዊነት መልክና ቁመና ባለው መልዕክት ሊተካ ይገባል ብሎ ምክክር ፓርቲ ስለሚያምን ለተግባራዊነቱ እንድትተባበሩ ጥያቄውን ያቀርባል፡፡
  1. ሰላም፤ ጸጥታ፤ አንድነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ሕብረት፤ መከባበር፤ ፈጣን ልማት፤ ወዘተ የሰፈነባት ሐገር እንድትሆንና ለማረጋገጥ ከ6ኛ አገራዊ ምርጫ በፊት ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገሉ ሀይሎች አንድ ላይ ሊሰሩ ይገባል ። የአንድነቱ ሀይል ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን ብቁ በሆኑ የሀገራችን ባለሞያዎችና የሚመለከታቸው ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅና ለተግባራዊነቱ የሚመለከታቸው ወገኖች ልንተባበርና በጋራ ልንሰራ እንደሚገባ በማመን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
  2. በምክክር ፓርቲ እምነት መሰረት በሚረቀው ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚያዘጋጅ የውይይት መድረክ እንዲፈጠር ማድረግ ያስፈልጋል ብሎ ምክክር ፓርቲ ያምናል፡፡ ረቂቅ ሕገ-መንግስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣መላው ሕዝብና የሚመለከታቸው ድርጅቶች ቀርቦ እንዲመረመር በመጨረሻም ተቀባይነት በሚኖረው ብሔራዊ ጉባኤ ሕገ መንግሥቱ እንዲቀርብ ሁሉም ወገን ሊወያይበት ይገባል፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሚመረጥ ምክር ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻል፣ብሎም ማዳበርና ማጽደቅ ይገባዋል ብሎ ምክክር ፓርቲ ያምናል፣ለዚህ ተግባር አንድነታችንን እንድናሳይ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአይምሮ ምጥቀት፣ሁለንተናዊ ድጋፍና ትብብር እንድናደርግ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  በሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች የተጀመረው እስር ተጠናቅሮ ቀጥሏል

                                               መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም

                                             ምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

                                                    (ምክክር ፓርቲ)

 

 

 

1 Comment

  1. ዘሃበሻ ትንሽ ቆይቶ የእድር ማስታወቂያ ፖስት የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡ ኡፕስ ለካ የፈለጉትን መጻፍ መብት ነው ይቅርታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share