October 8, 2020
14 mins read

“ የፍፃሜው ጦርነት ነው…” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

  አገር ታታሪ ና ጠንካራ የሥራ ዲሲፕሊን ባላቸው ዜጎቾ ነው የምትበለፅገው።አገር  ድካምን በማያውቁ  ዜጎቿ፣የለማቋረጥ በሚፈሥ ላብ፣በእውቀት ላይ በተመሠረተ ብርቱ ጥረት ልትበለፅግ ትችላለች።

   አገር፣    ዜጎቿ ለነገው ትውልዳቸው ምቾት ሲሉ መዕሥዋት በመክፈል በእድገት ጎዳና  ሥትበለፅግ የሁሉም ዜጋ ህይወቱ ይቀየራል።ለምሳሌ፣በዓባይ ወንዛችን ላይ እየተገነባ ያለው የኃይል ማመንጫ ግድብ ሥኬት የመሰዋታችን ሥኬት ነው። ዜጎች ከድህነት ለመውጣት ያላቸውን ጉጉት በተግባር ያሳዩበት ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ አባይን ግንድ ይዞ ከመዞር የገታውና ማደሪያ የሰጠው ፣ሀገር ወዳድነት የታየበት እንቅሥቃሴ ነው።የለው ብቻ ሳይሆን የሌለው ና   የሌላት  እንኳ ያቺኑ ያላቸውን የዕለት ጉርስ ለህዳሴው ግድብ ሰጥተዋል።    “ለምን እየተቸገሩ ለአባይ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያላቸውን ሰጡ? “ብለን ብንጠይቅ ብዙሃኑንን ምንዱባን ከድህነት የሚያላቅቀው ይህ የሚታይ፣የሚዳሰስ ና በተጨባጭ የሚያዩት ፕሮጀክት መሆኑን ከልብ በማመናቸው እንደሆነ ተገንዝበው ነው።ዛሬ አባይ “አባይ!”እንዳልሆነም አሥመሥክሯል።አባ ይ “አባ’ይ ” ነው። ነገ ለትውልዱ እንጀራ አውጪ በመሆኑ ኘው ፣ከሊቅ እሥከ ደቂቅ በአንድ ድምፅ “ግድቡ የኔ ነው። “ በማለት ዓለምን ያሥገረመው።

    ዛሬም ወደፊትም፣  እንደ አባይ፣ “አባ’ይ ” ከተገኘ ማለትም ሠርቶ የሚያሰራ፣የሚያበላ ፣ከተገኘ፣ሀገር ፣ በአጭር ጊዜ ውሥጥ ትበለፅጋለች።የአጠቃላይ ህዝቡም ኑሮ ይለወጣል።ገበሬው፣ሠርቶ አደሩ፣ወቶአደሩ፣ነጋዴው፣ወዘተ አልጋውን፣ልብሱን ፣ቤቱን ና ምግቡን ይቀይራል።በጎና ጠቃሚ ባህሉ ይዳብራል።ጎጂ ና አጥፊ ባህሉ ይጠፋል።ከአካባቢው፣ከጎሳው፣ከቋንቋ ተናጋሪው ባሻገር አርቆ መመልከት ና ማሰብ ይጀምራል።በማሰቡም በተፈጥሮ አንድ የሆነ፣የሚወለድ የሚያድግ፣የሚጎለመሥ፣የሚያረጅና የሚሞት መሆኑንን ይገነዘባል። በከንቱ መኮፎሱ ይቀርና የዓለም አካል ተፈጥሯዊ ልዩነት የሌለው ሰው መሆኑን በቅጡ ያውቃል።ከአድማስ ባሻገር እንዳያልም፣እንዳይተጋ እና ለትውልዱ የነገ ምቾት በብርቱ እንዳይጥር ካደረገው እና አዚም ሆኖ ካደነዘዘው  የአእምሮ ደህነትም ይላቀቃል።

  በመላው ኢትዮጵያ ድህነትና ያለማወቅ  እጅና እግሩን የሸበበውና  ቀፍድዶ የያዘው ሰው እልፍ እለአፍ ነው። የዘመናት “ ችግር ና ችጋር “  ዛሬም ከአገሬ ህዝብ ጫንቃ ላይ አልወረዱም።ይህ እውነት እያለ ነው፤ወያኔ/ኢህአዴግ የሚላሥ የሚቀመሥ ሥለማግኘቱ እርግጠኛ ያልሆነውን ብዙ አበሳን የተሸከመ ህዝብ፣  ጥጋበኞቹ በጥይት እሳት ሊያሥፈጁት ፣ጠግበው ውሥኪና ቮድካ እየጠጡ ይሚማማሉት።

    በቮድካ ደንዝዘው፣   ሚሊሻ ና ልዩ ኃይል ለእነሱ ጥጋብ ሲሉ ከንቱ  የሆነ የውሻ ሞት እንዲሞት ምሽግ አድርገውት፣ “ግፋ በለው!!…” ይሉታል።በእውነቱ ለመናገር በድህነት ተቀፍድዶ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አረንቋ ውሥጥ ያለን ህዝብ የጥይት እራት ለማድረግ መንቀልቀል በእጅጉ የሚያሳፍርና ህሊና አልባነትን ነው።

    ዛሬም የተገንጣይነት ሥም የያዙ፣ለህዝብ ያልቆሙ።27 ዓመት ኢትዮጵያን በተጭበረበረ ምርጫ ሲያሥተዳድሩ የነበሩ፣የትግራይን ደሃ ወዛደር እና ገበሬ ከምፅዋት ተቀባይነት ፣ከሥንዴ “ራሺን” ያላላቀቁ።ትላንት በበረሃ ሳሉ የሚቀመጡባትን የየዋሁን ገበሬ የዲንጋይ መቀመጫ ዛሬ በባለ አምሥት ኮኮብ ሆቴል በውድ ሶፋ የቀየሩ ናቸው። ከምቾት ወዳድነታቸውም የተነሳ ራሳቸውን ፈጣሪ ያደረጉ፣ሞትን የረሱ ፣ህሊና ቢስ “ማቶዎች” መሆናቸው ድርጊታቸው ያሤብቃል።

   እነዚህ ህሊና ቢሶች እያሉ ፣  እንዴት ነው በልፅግናን በአገራችን እውን የምናደርገው? በነገድ እና በቋንቋ ተጠራርቶ ፣በነፃ አውጪ ሥም ተደራጅቶ ፣ በመዝረፍ ነውን?ወይስ በአንዲት ሉአላዊ አገር የሚኖር “ሰው የሆነ ዜጋ ሁሉ ” እኩል መብትና ነፃነት ኖሮት በመላው ኢትዮጵያ ተዞዙሮ የመሥራት፣ሀብት የማፍራት፣ከወደደው ጋር ተጋብቶ ፣ተዛምዶ ና ተዋልዶ የመኖር መብቱ ተረጋግጦለት ያለ ሌብነት በወዙ እንዲከብር   ተገቢውን መንግሥታዊ ድጋፍ በማድረግ ነው?…

   ሌብነት አልባ፣ በወዝ ፣በድካም፣በልፋት፣በጥረት እና በግረት የመበልፀግ  ጎዳናው ሁለተኛው አማራጭ ነው።ይህ በህሊናቸው ጥንካሬ የሚመኩ ዜጎች የብልፅግና መገድ ነው።ይህ መንገድ ብቻ ነው ፣ ወደ ብልፅግና የሚወሥደን።ይህ መንገድ ወደ ብልፅግና እንደሚወሥደን እናውቃለን። አሻጋሪው የእውነተኛ ለውጥ መንግሥትም ተቋማትን በመገንባት ላይ መሆኑን በተጨባጭ እያየን ነው። “ቦሌ በአንድ ቀን አልተገነባም “በእርግጥ “ የፖለቲካ ጫዎታው” “ የማንችስተር “እና “የአርሴናል ” ጨዋታ እየመሰላቸው፣በሥራ፣በገብያ፣በመሸታ ቤት ፣በየካፊው …ሁሉ ተሰባስበው ፣በሥሜት በመናገር የራሳቸውን ማንነት በመዘንጋት የሚዘላብዱ አሉ።መዘላበድ መብታቸው ነው።ሆኖም ቆም ብለው በማሰብ ራሳቸውን ከተነጂነት ቢያላቅቁ ና እንደ ሰው ቢያስቡ እውነታውን ይረዳሉ።”ሀገር የምትመራው ፣በእውነት ላይ ተመሥርቶ፣ከግል ጥቅም እርቆ፣በመከባበር፣ በመደማመጥ እና ለመጪው ትውልድ ብልፅግና አርቆ በማሰብ እንጂ በቋንቋ፣በጎሳ እና በዘራፊ ቡድን ተደራጅቶ በህዝብ ሥም፣ህዝብን በእሳት እንዲማገድ እንደችቦ አቁሞ የምቾትና የድሎት ኑሮ መኖሪያ ምሽግ በማበጀት ባለፉት ሁለት ከመንፈቅ ዓመታት በአሻጋሪው   መንግሥት የተሰራውን ሀገርን ወደ ብልፅግና የሚያራምድ ሥራ በመናቅ አይደለም።

 እርግጥ ነው፣አሻጋሪው መንግሥት የሰውን አእምሮ መቆጣጠር የሚችል ሁሉን አዋቂ ሁሉን ቻይ እግዜር እንዳያደለ እናውቃለን።   ደሞም    የዚች ሀገር ችግር ውሥብሥብ እና በሴራ ፖለቲካ የተተበተበ ነው። በመሆኑም የፖለቲካ ጌሙን ያላወቀ፣በትንሹም በትልቁም በማልቀሥ ና አንደ ሰው ላይ ጣት በመቀሰር የሚነዛው የቅጥፈት ወሬ በቀላሉ ሀገርና ህዝብን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። ይህንን በመገንዘብ በለውጡ መንግሥት ላይ፣ አፍ እንዳመጣ ከራሥ ፍላጎትና ጥቅል ከሆነ የመንጋ ሃሳብ ከመወገን፣ ብንታቀብ ሐውጡን እንዲፋጠን እናደርጋለንና ሰከን ብለን ራሳችንን በማየትና የተከመረብንን ኃጥያት በመገንዘብ ለንግግራችን፣ለፅሑፋችን፣ለከት ቢኖረው መልካም ነው።… “ ከበሮ ችሎታ ባለው ሰው እጅ ሲመታ ያምራል እችላለሁ ብለው ስዩዙት ግን ያደናግራል። ‘

   ባለፉት ሁለት መንፈቅ ዓመታት ውሥጥ  የፍትህ ጠበቃ የሆኑት የህግ አሥፈፃሚ ተቋማት ገና ተገንብተው ባለማለቃቸው ፈተናው መብዛቱንም እንገነዘባለን።ይሁን እንጂ ውሥጥ ለውሥጥ ተቋማትን ከሌብነት የፀዱ፤ለእውነት የቆሙ፤በህግ የበላይነት የሚያምኑ ፣ ለሰው ፊት የማያደሉ እና ብቃት ያላቸው ፣ከበሮውን በወጉ የሚመቱ ለማድረግ በብርቱ እየተሠራ መሆኑን እንገነዘባለን።

  ይህ የመንግሥት አካሄድ  በእጅጉ የሚደገፍ  እና “ይበል!” የሚያሰኝ ነው።እንዲህ ዓይነቱ በጥንቃቄ የሚከናወን ብቃት ያለውን ዜጋ  የህዝብ አገልጋይ የመልመል ሥራ  ፣ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በቅንነት መንግሥትን የሚያግዙ አገር ወዳድ ምሁራን መኖራቸው ቢታወቅም ለ27 ዓመት በትግራይ ህዝብ ሥም ሲነግድ የኖረው ፣ዛሬም   ነፃ አውጪ ነኝ በዩ ህውሃት እና ነፃ አውጪው ኦነግ ሸኔ፣ “ አሻጋሪውን መንግሥት በሙሉ አቅሙ ሠርቶ ከዚህ የተሻለ የለውጥ ብርሃን እንዳያሳየን ፣በየጊዜው ጥላቸውን ሲያጠሉበት እንደነበር አንረሳም።ዛሬ ግን ሁለቱም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop