ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች

https://www.facebook.com/shemsalnur/videos/3618186974915191/

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች እንኳን ደስ አለን አጨራረሷን ተመልከት

4 Comments

 1. ዋይ ለተሰንበት። አገራቺንን በጥሩ ስላስነሳሺ እግዚአብሔር ይባርክሽ

 2. ትልቅ ትልቅ የሚያኮራ ውጤት፡፡ እንኳን ደስ አለሽ ለታይ፤ አኩርተሺናል! ኦሎምፒክን ጨምሮ ለሚቀጥሉት በርካታ ዓመታት ትደምቂያለሽ፡፡ ራስሺን ጠብቂ፡ በርቺ ጽዮን ማርያም ትጠብቅሽ!!!!

 3. Under Mereja:
  ” የ5,000 ሜትር ሪከርድን ስፔን፣ ቫሌንሽያ ላይ ከሰበረችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ ጋር ያደረግኩት አጭር ቃለ-መጠይቅ! Elias Meseret
  – በመጀመርያ እንኳን ደስ አለሽ፣ ወደ ጥያቄዬ ስገባ፣ በአንቺ ስም እና ፎቶ የተከፈተ የፌስቡክ ገፅ ብዙ መረጃዎችን እያወጣ ነው። በአንድ ግዜ የተከታዮቹ ቁጥር ከ18,000 በልጧል፣ ይህ በእርግጥ የአንቺ ነው?

  አትሌት ለተሰንበት>> እኔ ምንም አይነት የፌስቡክም ሆነ የሌላ ሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ አይደለሁም፣ ሌላው ቀርቶ ስልክ እንኳን በአሰልጣኜ ነው የምጠቀመው፣ እንደምታውቀው አሁን እራሱ የማወራህ በሱ (ሀይሌ) ስልክ ነው። እኔ ሙሉ ትኩረቴ አትሌቲክስ ላይ ብቻ ነው። አንድ የፌስቡክ ገፅ ሰሞኑን እኔ ያላልኩትን ነገር እያወጣ እንደሆነ ሰምቻለሁ፣ አዝኛለሁም። ይህ ደስ አይልም፣ የሚፃፈው ነገር ሞራል ሊነካ ይችላል። ለህዝብ የእኔ እንዳልሆነ አሳውቅልኝ፣ ምንም የሶሻል ሚድያ አካውንት የለኝም።

  – ቦሌ ኤርፖርት ያጋጠመሽ ነገር ምን ነበር?

  አትሌት ለተሰንበት>> ያጋጠመኝ ነገር ያን ያህል ከባድ የሚባል ችግር አልነበረም፣ አሰልጣኜ (ሀይሌ) ነበር ሲያናግራቸው የነበረው። በሗላ አትሌት ደራርቱ መጥታ ችግሩ ተፈቷል፣ በቃ ይሄው ነው።

  – አሁን የ5,000 ሜትር ሪከርድ ሰብረሻል፣ ቀጣይ ውጤት ምን እንጠብቅ?

  አትሌት ለተሰንበት>> የአሁኑ ውጤት ትልቅ ብርታት ሆኖኛል ስለዚህ በቀጣይ ነገሮች ከተመቻቹ የ10,000 ሜትር ሪከርድን መስበር እፈልጋለሁ፣ እሱን ማሳካት ቀጣይ እቅዴ ነው።”

  እንዴት ነው ነገሩ ሁሉ? በሰላማውያን ተጋሩ ላይም ቦሌ ላይ ልዩነት ተጀመረ እንዴ? “ዘመንያ ግርምቢጥስ ማይ ንዓቐብ” እንዳይሆን አደራ…!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.