ሥጋህን አውልቀህ በነፍስህ ብታስብ፣
ህወሀትና ወነግ ከንቱው ይህ አድግም፣
አጋድሞ እያረደ የጠጣ የሰው ደም፣
ሲኮነን የሚኖር በምድር በሰማይም፣
ችሎት ያልቀረበ ወንጀለኛ አይደለም?
የአንተን ድሎት ሳይሆን ሰማእትን ብታስብ፣
ይህ አድግ የሚባል የጭራቅ ሥብስብ፣
ሰው ጠብሶ እየበላ እየፋፋ እሚያድር፣
ፍርድ ቤት እንዲቀርብ አትጮህም ነበር?
ሥጋህን ገሽልጠህ ብጠይቅ ነፍስህን፣
ጎጥ መንደርን ትተህ ብትጎበኝ ህሊናን፣
አማራን ታስበላው አሽከሩ ብአዴን፣
ቆንጆ ልትመራርጥ ቂጥ ታማታ ነበር?
በደመነፍስ ሳይሆን በዓይምሮህ ብታስብ፣
ጆሮን እየጠባ ስንት ያስፈጀን እባብ፣
አሻጋሪው ሙሴ ብለህ ትቃዥ ነበር?
በደንደስህ ሳይሆን በነፍስህ ብታስብ፣
እንደ አብዮት ግዛው እረግጠህ የሰው ደም፣
የአማራን ዘር ፍጅት ሽምጥ ትክድ ነበር?
ሥጋህን ገሽልጠህ በነፍስህ ብታስብ፣
የዘር ማጥፋት ወንጀል የካደውን ወንበር፣
ተዓለም ችሎት ቢሮ አትገትርም ነበር?
ክርስትያን እስላም እውነት አማኝ ብትሆን፣
ተገዳይዮች ጀርባ ቆመህ ትታይ ነበር?
ብታስብ ለነፍስህ ፈራሽ ሥጋን ትተህ፣
ነፍስ አጥፊን ባልደገፍክ ፍትህን ጨፍልቀህ፣
ሱስና መደመር በሰላይ ተሰብከህ፡፡
በነፍስህ ብታስብ ሥጋህን አውልቀህ፣
የሰላሳ ዓመታት ሰማእት እረስተህ፣
በክህደት ጫማ አስከሬን ደፍጠህ፣
ታራጁ ይህ አድግ ጋብቻ ፈጥመህ፣
ምድርና ሰማይ ታሪክ ባልኮነነህ፡፡
በላይነህ አባተ ([email protected])
ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.