July 30, 2020
11 mins read

“ኳራንቲን ስላላስገባችሁን እናመሰግናችኋለን” ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

ወደዝርዝሩ ጠልቄ ከመግባቴ በፊት አንድ ጉዳይ ለተደራሲያን ግልጽ ማድረግ ፈለግኩ። ለዚህ ጽሁፍ በመሪ ርእስነት የተጠቀምኩበት አስደማሚ የመወድስ ሀረግ ከሳምንታት በፊት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሀ.ት)ንና የብልጽግና ፓርቲን ሊያስታርቅ ከፍተኛ ተስፋ ሰንቆ ወደመቀሌ የተጓዘው የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ምክትል ሰብሳቢ ከድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ጋር ካካሄዱት ምጥን ቃለ-ምልልስ ውስጥ በቀጥታ ቀንጭቤ የወሰድኩት ነው። አባባሉ ስላስገረመኝ የፓስተር ዳንኤል ገብረ-ስላሴን ጀሮ–ገብ የመውጫ ቃለ-ውዳሴ በጉልህ ላነሳውና በርእስነት ልገለገልበት መርጫለሁ።

ሞገደኛው ጋዜጠኛ ሰውየውን አግኝቶ ያናዘዛቸው ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ሲዘጋጁ ነበርና ቡድናቸው ወደመቀሌ ስለተጓዘበት ተልእኮና በዚያ ስለተደረገለት መስተንግዶ ትንሽ ያወጉት ዘንድ መጠየቁ የማይጠበቅ አልነበረም።

እርሳቸውስ ቢሆኑ ምናቸው ሞኝ ነው መሰላችሁ?

የክልሉ መንግስትም ሆነ እርሱን የሚመራው የፖለቲካ ቡድን ለታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎቹና ለብጹኣን የሀይማኖት አባቶቹ በጊዜው ያደረጉላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል የተዋጣለት እንደነበር አስታውሰው የአንድ ቀን ቆይታቸው ፍሬያማ እንደነበር አውሸልሽለውም ቢሆን ሲነግሩት ተከታትለናል፡፡ በኮቪድ 19 ምክንያት ኳራንታይን ይገቡ ዘንድ እንግዶቹን ስላላስገደዷቸው በመሽኮርመም ከተሰነዘረ ተደራቢ ምስጋና ጋር፡፡

ይልቁንም ‘ምነው ዘገያችሁ’ ተብለው በአስተናጋጆቻቸው በኩል መወረፋቸውንና መገሰጻቸውን ሳይደብቁ በዚህ አገር የተፈጠረው ችግር እኮ ህወሃትንና ብልጽግና ፓርቲን ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ በምጸት እንደተነገራቸው በይፋ ሲገልጹለት አዳምጠናል፡፡

እንግዲህ ህ.ወ.ሀ.ት ያን ያህል ትእቢተኛና እብሪቱ ጠርዝ የነካ ባለጌ ቡድን ነው፡፡ ይህ በሚገባ እየታወቀ ለምን እስከዚያ ደረጃ ድረስ እየወረድን ዘወትር እንደምናጎበድድለትና እንደምናባብለው ግራ ያጋባል፡፡

ያም ሆኖ ወደመቀሌ ከተማ ተጉዞ የነበረው የዚያ የሽምግልና ቡድን የስራ ውጤት ምን እንደሆነ እስካሁን የረባና የተጨበጠ መረጃ የለንም፡፡ በርግጥ ወደመዲናዋ እንደተመለሰ ‘ጩኸቴን ቀሙኝ’ በሚል ድምጸት ህ.ወ.ሀ.ት በፌደራል መንግሥቱ ላይ የሚያቀርባቸውን ደረቅ ስሞታዎች አንስተው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባይጨምርም ከብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስለመወያየታቸው ፍንጭ አግኝተናል፡፡

ሲለምኗት እምቢ ብላ ሲጎትቷት

እነሆ ዛሬ ደግሞ ህ.ወ.ሃ.ት በተራው ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እንዲያስታርቀው የራሱን የሽምግልና ልኡክ ወደአዱ ገነት በህቡእ ላከ መባልን ሰማን፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ በምስጢር እንዲያዝ የተፈለገ ይመስላል፡፡ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ይህንኑ ለማረጋገጥ አልደፈሩም፡፡ ነገሩን መሸማገል ሳይሆን መሸነጋገል የሚያስመስለውም ይህ አይነቱ የሹሉክሉክታ አካሄድ ነው፡፡

ህ.ወ.ሀ.ት እንደሆነ መምጫው የማይታወቅ ዘረ-አካይስት ቡድን ነው፡፡ በራሳቸው አነሳሺነትም ይሁን አንዳንዶች እንደሚጠረጥሩት የሌላ ወገን ተልእኮ ተሰጥቷቸው ቀድመው ወደርሱ የተጓዙትን የተከበሩ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ገላምጦና አሳፍሮ የመለሰው ቡድን አሁን ደርሶ ‘እባካችሁ ሸምግሉኝ’ ማለቱ የጤና ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡ ይልቁንም በህቡእ የሚንደፋደፍበትን የቤት ስራ ያለስጋት ለማከናወን ያመቸው ዘንድ ጊዜ ለመግዛት መሆን አለበት፡፡

የወጣቱን ከያኒ የሀጫሉ ሁንዴሳን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በጽንፈኛ ሀይሎች እየተመራ በኦሮምያ ክልልና በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች በጭካኔ የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ሁከትና ሀገር አውዳሚ ጥፋት ተከትሎ ሀምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችና ተወካዮቻቸው ጋር አንድ የውይት መድረክ አካሂደው ነበር፡፡ በዚያ የውይይት መድረክ አሁንም አንዳንድ ወገኖች በከባድ ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙትን ሰዎች ይፈቱ ዘንድ ሽማግሌ እንደሚልኩባቸው በአግራሞት ይፋ አድርገዋል፡፡

ሆኖም እርሳቸው ተገቢ ባልሆነ መንገድ እጃቸውን በማስረዘም “እገሌ ይታሰር፣ እገሌ ደግሞ ይፈታ” እያሉ የትኛውንም አካል የማዘዝ ሕጋዊ መብት እንደሌላቸው ገልጸው ይህ ይደረግ ቢባል እንኳ ዝንባሌው አደገኛ በመሆኑ የሀገሪቱን የፍትህ ስርአት የማዛባት አሉታዊ ውጤት እንደሚኖረው በውል ይረዱት ዘንድ እቅጩን ነግረዋቸዋል፡፡

መቸም እንዲህ ያለው ቁርጥ ያለና አንጀት አርስ ማስገንዘቢያ የአንድ በሳልና አስተዋይ መሪ አስተያየት በመሆኑ በሀይለኛው ሊበረታታና ሊደገፍ ይገባዋል እላለሁ፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ከባለስልጣናት የተናጠል ውሳኔና የዘፈቀደ እርምጃ ይልቅ የሕግ የበላይነት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አንድና ሁለት የለውም፡፡

እርሳቸው፣ (ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማለቴ ነው)፣ የሕግ አስከባሪው የመንግሥት አካል የበላይ ቁንጮ እንጂ ቀድሞ ነገር ሸምጋይም አሸማጋይም እንዳልሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሰረቱ እነርሱ ብቻ ናቸው ባይባልም በመላው አለም የሚሰራባቸው አንጋፋዎቹ የሕግ ስርአቶች ሁለት ናቸው፡፡ የኮንቲነንታል (continental)ና የኮመን (common ሎው (law) ስርአቶች፡፡

የኮንቲነንታል የሕግ ስርአት በታወቁ የሕግ መርሆዎች ላይ ተመስርተው የሚጻፉ ዝርዝር የሕግ ድንጋጌዎችን በጥብቅ ተከትሎ በመፈጸምና በማስፈጸም ላይ የበለጠውን ሲያተኩር የኮመን ሕግ ስርአት ግን በተቃራኒው አስቀድመው በተጻፉ የሕግ ድንጋጌዎች ሳይወሰን ወይም እነርሱን ብቻ ሳያመልክ ሕግጋቱ ከወጡ በኋላ በመሬት ላይ ለሚያጋጥሙ ተጨባጭ ችግሮች ተግባራዊ )pragmatic) መፍትሄ የመስጠትን ተጨማሪ አቅም ያጎናጽፋል፡፡ በተመረጡ የወንጀል ጉዳዮችም ድርድርን ሳይቀር ይፈቅዳል፡፡

ለመጀመሪያው ስርአት ሀገረ-ፈረንሳይንና ለሁለተኛው ስርአት ደግሞ ታላቋብሪታንያን በወፍራም ምሳሌነት ይጠቅሷል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዋነኝነት የምትከተለው የኮንቲነንታል ሕግ ስርአትን ነው፡፡ ይህ ስርአት ግን ለፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር በተለይ የጠቅላላውን ህዝብ ደህንነት ለማረጋገጥና የመንግሥትን ጸጥታ ለማስከበር በሚወጡ የወንጀል ሕግጋት ተፈጻሚነት ረገድ የሽምግልናን ጣልቃ-ገብነት አይፈቅድም፣ አያበረታታምም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጠራው መድረክ የሠጡት ምላሽም ይህንኑ በሚገባ ያገናዘበ ስለሚመስል በአቋማቸው እንዲገፉበት ያስፈልጋል፡፡

ብራቮ ጠቅላያችን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop