- ኦሮሞ ከወሃ ነው የመጣው የሚለው ከአባ ባሕሬ መጻፍ ያነበብኩት ሳይሆን የዛሬው የኦሮሞነት ልክፈት ካህን የሆነው ምሁር ነው የተባለ …. ነው ያለው፡፡ አባ ባሕሬ ከባሕር ወጣ ያሉበት አግባብማ ለዛሬው የማይረባ አእምሮ ትውልድ አይገባውም፡፡
- መሳይ ስለሸኔ ኦነግ የጠየቀው ተጠያቂ በኃይለስላሴ ጊዜ የገበሬ ልጅ ከ4ኛ ክፍል በላይ መማር አይፈቀድለትም ማለቱ ብቻም ሳይሆን እስከዛሬ እንደዚህ ማሰቡ እጅግ ገርሞኛልም አሳሳቢም ነው፡፡ ነገ አንዱ ወይም ተናጋሪው ሌላ መርዝ ታሪክ ይዘውበት ይነሳሉ፡፡ኃይለሥላሴ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት መሳካት ከጠረፍ ገጠሬዎች ሳይቀር ራሳቸው እያመጡ ብዙዎችን አስተምረው ዛሬ ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱ አሉ፡፡ ውለታቢስ ስለሆነ ስለተደረገላቸው አያወሩም፡፡ ለነገሩኮ ይሄ ሁሉ ፖለቲከኛ ነኝ እያለ እስከዛሬም መዥገር ሆኖ የኖረበት ያ የ60ዎቹ ትውልድ ከገጠር ሆነ ከከተማ አስተምረው ዩኒቨርሲቲም አድረሰውት ነበር፡፡
- በወያኔና ኦነግ ሕግ እየተገዛንና የአባቶቻችን ደምና አጥንት የታተመበት ሰንደቅ ዓላማ ላይ ሰይጣናዊ ምልክት አሁንም እየተጠቀምን ስለኢትዮጵያ ሠላም ማሰብ ዘበት ነው፡፡ መጀመሪያ የወያኔና ኦነግ ሕግ ይጣል፣ ለጠላት የሚያስፈራው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወደነበረበት ይመሰለስ፣ሸዋ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁሉ መዕከል እንደመሆኑ ራሱን የቻለ አስተዳደር ይሁን፡፡
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል ታላቁ ፈላስፋ፡፡ ከላይ በርዕስነት የተጠቀምኩት የእኔ አደለም የኦሮሞ ቁቤ ትውልድ ካህንና ትውልድን በአእምሮ እየገደለ ያለው የተናገረው ነው (ከታች በሊንኩ ስሙት፤ ብትችሉ ባትስቁ ጥሩ ነው ልክፍት ስለሆነ)፡፡ ርዕሱንም የወሰድኩት ሰዎች ከለጠፉት ነው፡፡ መጀመሪያ ኦሮሞ ከውሀ ወጣ የመጀመሪያው ፍጥረት ኦሮሞ ነው ይልሀል፡፡ መቼም ወደው አይስቁ ሆኖብኝ እንጂ ነገሩ የሚያስቅ ጉዳይ አደለም፡፡ እርግጥም ነው አያስቅም መርዛቸወን እንዲህ ባለ ሁኔታ እየዘሩ ብዙ ተከታይ አፍርተዋል፡፡ ሰዎች አእምሮአቸው ካልሰራ በምን ያስባሉ? ለማንኛውም ሁሉም ይይና ወይ ይሳቅ ወይ የዘን ከታች ያለውን ሊንክ ይዩት፡፡
https://www.facebook.com/girma.biru2/videos/3138159362958036
በነገራችን ላይ ኦሮሞ የሚባል ቃል ለብዙ ሰው ብዙ ታሪክ ያስቆጠረ ሊመስለው ይችላል፡፡ ዛሬ ማመን ሊያስቸግር ይችላል ከዛሬ 30 ዓመት በፊት አብዛኛው ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞ ተብሎ አይጠራም ነበር፡፡ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት ከወለጋ በቀር ይሄን ቃል የሚያውቀውም አልነበረም፡፡ ከዛሬ 200 ዓመት በፊት ኦሮሞ የሚባል ቃል ከነጭርሱም አልነበረም፡፡ እንደሚመስለኝ በወለጋ ሚሲዮናውያን በሚያስተምሩበት ወቅት የተፈጠረ ቃል ነው፡፡ እንደማስበው በወለጋ የዛሬው ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነጮቹን ኦሮማ (ባዕድ/እንግዳ/ሌላ) እያሉ ሲጠሩ ነጮቹ ኦርማ የሚለውን ቃል ኦሮሞ በሚል መልሰው የአካባቢውን ሰው ይጠሩበታል፡፡ በዚህ ሂደት የተፈጠረ ቃል ነው የሚመስለው፡፡ ይህ ቃል ወደ ሐረርና የመሣሰሉት በሚገርም ሁኔታ በጣም በቅርብ ነው በኦነጋውያን ዘመን ማለት ነው፡፡ ግፋ ቢል 60 ዓመት ቢሆነው ነው፡፡ በጅማ ቃሉ ቀደም ብሎ ቢታወቅም የጂማ ሕዝብ በዚህ ቃል መጠራት አይፈልግም ነበር፡፡ ምክነያቱም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይሄ ቃል ለማያምኑ ብቻ የተሰጠ ስያሜ ነበርና፡፡ ለዚህ ደግሞ አባጅፋርን ማንበብ ነው፡፡ አባ ጅፋር እኛ ኦሮሞ አደለንም እስላሞች ነን ብለው ነበር፡፡ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ነው፡፡ ቦረና ከቦረናነቱ በቀር ኦሮሞ የሚለውን ቃል አያውቀውም ነበር፡፡ ዛሬ በኬንያ ያሉ የቦራን (ቦረና) ነገዶች (ኦሮምኛ ተናጋሪዎች) ኦሮሞ ስለሚባለው ቃል አያውቁም፡፡ ግን በዜና አንዳንዶች እየሰሙ ስለሆነ ኦሮሞ ስለሚለው ቃል በአድናቆት ምን እንደሆነ ሲናገሩ ትሰማላችሁ፡፡ በአጠቃላይ ዛሬ ልክ ዘመናት ያስቆጠረ የሚመስለው ኦሮሞ የሚለው ቃል እንኳን ከዘፍጥረት የዛሬ 30 አብዛኛው ዛሬ ኦሮሞ የተባለው መጠሪያው እንዳልሆነ ሁሉም ቢያውቅ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ እውነት ነው፡፡ ብዙዎች ዛሬ እብድ እስከመሆን ሊክዱ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ዋናው ቦረና ቦረና ነበር እንጂ ኦሮሞ ሆኖ አያውቅም ከ30 ዓመት በፊት፡፡
ሰሞኑን መሣይ አንድ የሜጫ ቱለማ ሰው ስለ ኦነግ ሸኔ ሲጠይቅ ሰማሁ፡፡ ተጠያቂው በኃይለሥላሴ ጊዜ የገበሬ ልጅ ከ4ኛ ክፍል በላይ አይማርም ነበር ሲል ሰማሁ፡፡ እንግዲህ ነገ ጠዋት አንዱ ይሄን የሰማ ዋይመ ተናጋሪው ራሱ ታሪክ ጸሐፊ ሆኖ ብቅ ይልና ይሄንኑ ስህተት የዘራል፡፡ ከዛ አሁን ይሄው ሁሉም እንደፈለገው የሚነዳው ትውልድ ተቀብሎት ተጨማሪ ሮሮ ያሰማናል፡፡ እርግጥ ነው ተናጋሪው ወይ የሚያስተምረው አንዱ አስተማሪ፣ ወይም የትምህርት ቤቱ ሰው እንደዛ ብሎት እሱኑ አምኖ ወደቤቱ ሄዶ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ በዛ አካባቢ ገዥ የሆነው ባላባት ራሱ የፈጠረው ሕግ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ እነ ራስ መስፍን ስለሺ በዚህ አይነት ነገር ከማድረግ ላይመለሱ ይችላሉ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ኃይለሥላሴ በትምህርት እጅግ የለፉና ከጠረፍ ቦታዎች ሳይቀር እያመጡ በራሳቸው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች እያስተማሩ ዛሬ ድረስ ትልልቅ ቦታዋች ላይ የሚገኙ ምሁራን አሉ፡፡ እንደ እድል ሆኖ እነዛ ምሁራን ውለታ ቢስ በመሆናቸው ዛሬ ስለዛ ዘመን አያወሩም፡፡ ይልቁንስ የልደረሰባቸውን በደል ፈጥረው ለዛሬው ትውልድ መርዝ ይግቱታል፡፡ ለዚህ እንደነ ዶ/ር ገመቹ የሚባሉ ሰዎች እዩ፡፡ ለነገሩ ዛሬም ድረስ ይሄው አገር እያመሰ ያለ ፖቲከኛ ነኝ እያለ ያለው በብዛት እኮ በዛን ወቅት ትምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ደርሶ ትምህርት ጥሎ የሸፈተ ነው፡፡ ከገበሬም ከሌላም የመጣ፡፡ እኔ የገበሬ ልጅ ነኝ ኃይለስላሴን ባልደርስባቸውም በእሳቸው ጊዜ በተሰራ የገጠር ትምህርት ቤት ነው የተማርኩት፡፡ ይህ ትምህርት ቤት ሲጀምር እስከ 6ኛ ነበር የሚያስተምረው፡፡ እኔም ስማርበት እንደዛው ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ዩኒቨርሲቲ ሁሉ ገብቼ ስማር እንደዛ ያለ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አልገጠመኝም፡፡ በኋላ ለማስተርስ አውሮፓ ስሄድ ነው እንደዛ ያለ የመማሪያ ዕቃዎች ያሉት ዩኒቨርሲቲ ያየሁት፡፡ በእርግጥም ይህ እኔ አንደኛ ደረጃ የተማርኩበት የገጠር ትምህርት ቤት የተሰራው በስዊድኖች እርዳታ ስለነበር ሁለነገሩ ከአውሮፓ በመጣ እቃዎች የተሟላ ነበር፡፡መቀመጫ ወንበሮቹና ዴስኮቹ እጅግ የሚያማምሩ፣ ዳስተሮቹ፣ ሰሌዳዎቹ ጥቁር ሳይሆኑ አረንጓዴ ነበሩ፡፡ እኔ እስከተማርኩበት ጌዜ ድረስ እንኳን የእነዚህ ቁሳቁሶች ወበት አሁን ድረስ ይታወሰኛል፤፡ አረንጓዴ ሰሌዳ ያየሁ ከዚያ በኋላ ከኢትዮጵያ ወጥቼ አውሮፓ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁሉ ነገር የተሟላለት ቦታ እልም ያለ ገጠር ነው፡፡ የገበሬ ልጆች እንዲማሩበት፡፡ እንደውም በወቅቱ ችግር የነበረው ሰዎች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት አንሰልክም በማለታቸውነ ነው ሲባል ነው የሰማንው፡፡ ይሄን አይነት ልማት በእርግጥም በቀጥታ የንጉሱ እቅድ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ባላባቶች የራሳቸውን ሴራ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ መሳይ የጠየቀው ሰው በእርግጥም ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የማዝናው እስከዛሬ ድረስ ይሄንኑ የኃይለስላሴ ሥርዓት የትምህርት ፖሊሲ እንደሆነ ማሰቡ ነው፡፡ መቼም ውሎው ሁሉ መርዘኛ ከሆኑና ነገሮችን በተቃራኒው እንዲታዩ ከሚያደርጉ ጋር መሆኑ እንጂ የሆነ ከክፋት የጸዳ ዜጋ ጋር ቢኖር ይሄን ያህል ዘመን ችግሩ የኃይለስላሴ የትምህርት ፖሊሲ ሳይሆን ሌላ እንደሆነ በተረዳ፡፡ ትውልድ የሚጠፋው እንዲህ ነው፡፡ እሱም ይሄንኑ ለልጆቹ እየነገረ አሳድጎ ይሆናል፡፡ እንዲህ በሆነ መልኩ ነው ትውልድ እየጠፋ ያለው
በመጨረሻም ኢትዮጵያ እንደአገር እንድትቀጥል ከታሰበ ይሄን ያህል ዘመን በጥፋት ሲሴርብን የኖረውን ነገር ሁሉ መንግለን መጣል አለብን፡፡ እስካሁንም እኮ ወያኔና ኦነግ በሠረቱ ሕግ ነው እየኖርን ያለንው፡፡ እስካሁንም እኮ ወያኔና ኦነግ በሰጡን ሰንደቅ ነው ያለነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል መንግስትም ሆነ ቡድን እንግዲህ እስኪ መጀመሪያ ወንጀለኞች የሰሩትን ሕግ በሕጋዊ ሕግ ይቀይር፣ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ይሄን የጥንቆላ ምልክት ያንሳ፡፡ በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያለው ምልክት በግልፅ የእርግማን ምልክት እንጂ አንዳቸውም ከኢትዮጵያ ሕዝቦች መተሳስር ወይም ሌላ ሕዝብን የሚመለከት ምልክት እንዳልሆነ ሁሉም የወቅ፡፡ ይሄን ምልክት ስላልነካው እስከዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ በጀመረው ሂደት ከፍታውን ቀጥሏል፡፡ ሊያውም ይሄ ሁሉ ወሮበላ እየተፈራረቀበት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያስተውል፡፡ ይሄ እውነት ነው፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ የብዙዎች ደምና አጥንት የታተመበት የማይነበብ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ማህተብ ይዟል፡፡ በዚህ የአባቶቻችን አጥንትና ደም ማሕተባ ላይ ነው የሰይጣናዊ አምልኮ ተከታዮች ምልክት የተደረገው
ሌላው በኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በማዕከላዊ ብዝሐነት የሚያማክለው ሸዋ ለኢትዮጵየዊነት ምልክትም እንዲሆን የ30 ዓመት መርዙንም ለመንቀል መሳሪያ እንዲሆን ሸዋ ራሱን የቻለ የብዝሀ ቋንቋና ባኅል የሚንጸባረቅበጽ ልዩ መስተዳድር ሆኖ እንደገና የመለስ፡፡ ከሸዋ ውጭ ሁሉም ሕዝብና መልካም መሪዎች በሚወስኑበት አስተዳደር መዋቅሩ ይሰራ፡፡ ክልል የሚባል ነገር ሥሙ ራሱ ቀፋፊና የእርግማን ስለሆነ ክፍለ ሀገር፣ ወይም ጠቅላይ ግዛት፣ ወይም አስተዳደር፣ የሚመቸው ሌል ስም ይሰጠው፡፡ በነገራችን ላይ ደጋግሜ ተናገሬዋለሁ፣ ሰሞኑን ብዙዎችም እያነሱት ነው፣ አብዛኞቹ ክልሎች ለምሳሌ ኦሮሚያ የኦሮሞ እንጂ የሌሎች እንዳልሆነ በግልጽ በኦሮሚያ ሕገ-መንግስት በተባለው ተጽፏል፡፡ እንዲህ ያል ወነጀለኛ ሰነድን ሕግ አድርጎ እየኖረ ያለ መንግስት በምን መስፈርት ነው ሕግ የሚያስከብረው፡፡ ስለዚህ ሕግ ለማስከበር ወንጀኖች ያወጡት የወሮበላ ሰነድ እንደሕግ መስራቱ ይቁም፡፡ እስካሁን አንድም ነገር በህግ አግባብ ወደፊት ሊያስኬት የሚችልና የኢትዮጵያዊነት የሆነ ምንም ዓይነት ተግባራዊ ሥራ ሳይሰራ በወሬ ብቻ ስለኢትዮጵያዊነት እየሞሉት ጭራሽ ኢትዮጵያን ወደ አደጋ እየመሩና ያው በኖሩበት እየቀጠሉ መሆኑን አስተውሉ፡፡ አገር በሕግ ነው የምትመራው፡፡ ስለዚህ ጠላት ባወጣው ሕግ እየኖርን ሕግና ሥርዓት ብንል የቱ ሕግ እንዲከበር ነው? ክልል የተባሉት እኮ በሕግ ሌሎች የመኖር መብት እንደሌላቸው የተጻፉትን ሕግ ነው ክልል የሚያስተዳድሩበት፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከክፉ ይጠብቅ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ