July 21, 2020
23 mins read

የሁለቱ ሰልፎች ወግ – ሰሎሞን ጌጡ ከኑረምበርግ

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈፀመውን ፓለቲካዊ ግድያ (Assassination) ተከትሎ ፤ በኢትዮጵያ ንፁሀን ወገኖቻችን የብሔር እና ሀይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ ሰለባ ሁነዋል። ይህን ተከትሎም በሁለት የተቃርኖ አስተሳሰቦች የተቃኙ እና በሁለት የተለያዩ ቀለማት ያጌጡ ሰላማዊ ሰልፎችን በተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተሞች ሲካሄዱ  አስተውለናል። እኛም የሰብአዊ መብት ከተማ እየተባለች በምትጠራው ኑረምበርግ ቅዳሜ እለት በአንዱ ቀለም ደምቀን በጋራ ቁመን ነበር። በሰልፋ ላይ እያለው በተፈጠረብኝ ተጠየቅ ምክንያት ስለ ሁለቱ ሰልፎች እና እንድምታቸው ያለኝን እይታ እንደሚከተለው ላጋራችሁ ወደድኩ።

ሁለቱ ሰልፎች :- አንደኛው የአክራሪ ዘውጌ ብሔረተኝነት መሰረት ያደረገው ሰልፍ ሲሆን አላማው የሀጫሉ ገዳዮች ነፍጠዮች ናቸው በማለት በማመኑ ወይም በመሞላቱ ምክንያት የነፍጠኛን መውደም ፣ የኢትዮጵያን መፍረስ እና የዶ/ር አብይን አስተዳደር መንኮታኮት መፈክር በማድረግ ተቃራኒ የሚባለው ወገን ላይ ጥቃት ለማድረስ የተሞከረበት ብሎም አገር ቤት ብሔር እና ሀይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ የጥላቻ ንግግሮች የተስተዋሉበት “ሰላማዊ ሰልፍ” ነው። ይህ ሰልፍ አንዳንዶች እንደሚሉት አንድም ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንደሚባለው የተበዳይን ጩኸት በመቀማት፤ ተጎጂን ማውገዝ ላይ ያነጣጠረ እና ምናልባትም አገር ቤት ያለውን ሀቅ አለም አቀፍ ህብረተሰቡ በተሳሳተ መልኩ እንዲረዳው ለማድረግ ያቀደ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው። አንድም ደግሞ በሀጫሉ መሞት የተንገበገቡ እና ጥቂት የሀሳብ መሪዋች የነገሯቸውን መረጃ ሳያጣሩ በመሰልቀጥ በግብታዊነት በየዋሀዋች የተፈጠረ ስብስብ ነው። ሁለተኛው ሰልፍ ኢትዮጵያዊነት ቅኝትን መሰረት ያደረገ በኢትዮጵያዊነት እና አብሮነት ያጌጠው ሰልፍ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ አትፈርስም ፣ ፍትህ ለተበዳዮች ፣ ጨፍጫፊዋች ለህግ ይቅረቡ እና የጎሳ ፓለቲካ በህግ ይታገድ የሚል መፈክሮች የተስተዋሉበት ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። በኢትዮጵያዊነት፣ አዲስ አበቤነት እና አማራነት መካከል ባለው ያልተቀናጀ ስልት/ያልጠራ አካሄድ ምክንያት ሁለተኛው ቅኝት እንደ ቀድሞው ምሉዕ እና ጥኡም እንዳይሆን አድርጓል የሚል እምነት አለኝ። አሁንም ቢሆን ይህ የሁለተኛው ሰልፍ ጥኡም ቅኝት እንዲኖረው ከተፈለገ የነዚህን ሀይላት እና የሀሳቡን መሪዋች መቀራረብ እና መናበብ እጅጉን ይጠይቃል። በትግል ስልት መለያየት ምክንያት የጋራ አላማን ማክሸፍ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላልና።

ፓለቲካዊ ምንታዌነት በኢትዮጵያ :-  ይህን መሰል የምንታዌ/የሁለትዮሽ ተቃርኖ አስተሳሰብ ወይም እንቅስቃሴዎች በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አገሮች እና የታሪክ ጊዜአት ተስተውሏል። በ Ferdinand de Saussure Structuralist-Binary Opposition ንድፈ ሀሳብ መሰረት በሰው ልጅ ህይወት ወይም በአንድ ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ውስጥ ሁልጊዜ የሁለትዮሽ ተቃርኖዋች ይገኛሉ። አንድ ማህበረሰብንም ባግባቡ ለመረዳት እነዚህን ምንታዌ ተቃርኖዎች መመርመር አለብን ብሎ ያምናል። ለምሳሌ ብርሀን/ጨለማ ፣ ህይወት/ሞት ፣ ሰላም/ጦርነት፣ ልማት/ጥፋት፣ ፍቅር/ጥላቻ፣ እውነት/ሀሰት፣ ወንድ/ሴት፣ ሀብታም/ደሀ፣ አንድነት/ተገንጣይነት ፣ አቃፊነት/ገፊነት እና ሌሎችም። በዚህ ንድፈ ሀሳብ መሰረት እነዚህ የሁለትዮሽ ተቃርኖዋች ሁልግዜ የሚኖሩ ሲሆን ፤ በሁለቱ መካከል ግልፅ የሆነ ልዮነት/dichotomy አለ። በተጨማሪም አንዱ ለሌላው መኖር መሰረት ባይሆንም ቅሉ፤ ነገር ግን የተቃርኖዋቹን ምንነት፣ የእርስ በእርስ መስተጋብር ፣ ጥቅም እና እንድምታን ብሎም ማህበረሰቡን/ትልቁን ስዕል ለመረዳት የሁለቱም መኖር አስፈላጊ ነው። ለሰላም መኖር ጦርነት ባያስፈልግም ፤ የሰላምን ፋይዳ ለመረዳት እና በውስጡም በዘላቂነት ለመኖር ግን የጦርነትን ምንነት እና አስከፊነትን መረዳት ያሻል። በታሪክ የነበረውን የምንታዌ ተቃርኖ አስተሳሰብም ለመረዳት የ Karl Marx ን ሀሳብ ማየትም እንችላለን። Karl Marx እንዲሁ Historical Materialism በሚለው ሀሳቡ በየአንዳንዱ የማህበረሰብ የእድገት ደረጃ ውስጥ መደብን መሰረት ያደረጉ ቢሆንም የተቃርኖ አስተሳሰብ/መደብ እንዳለ Thesis/antithesis በሚለው ትንተናው አስቀምጦልናል። በዚህ ሀሳብ መሰረት በእያንዳንዱ የማህበረሰብ የእድገት ደረጃዎች ውስጥ የሁለትዮሽ ተቃርኖዋች ይገኛሉ። ለምሳሌ ባሪያ አሳዳሪ/ባሪያ፣ ፊውዳል/ጭሰኛ፣ ካፒታሊስት/ወዝ አደር በማለት የነበሩትን ተቃራኒ መደቦች እና በመካከላቸው የነበረውን የበዝባዥ-ተበዝባዥ መስተጋብር እና ውጤቱን/Synthesis ገልፆልናል። በአገራችን እንዲሁ በተለያዩ ግዜአት መሰረታቸው ዘርፈ ብዙ ቢሆንም የተለያዩ ምንታዌ ተቃርኖዋች ነበሩ። እስቲ Binary opposition የሚለውን ንድፈ ሀሳብ በአገራችን ያለውን ወቅታዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ለመቃኘት እንዋሰው። በእርግጥ በአገራችን የተለያዩ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴው እና እጅግ የበዙ ፓርቲዎች ይገኛሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁላ ፓርቲዎች የተለያየ ሀሳብ አላቸው ማለት አይደለም ፤ ብዙዋቹ የተለያዩ ስሞች ቢኖራቸውም ተመሳሳይ የሀሳብ ቅርጫት ውስጥ የሚገቡ ናቸው። ዝርዝር ፓለቲካዊ መስፈርቶችን እና ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደጎን ትተን ቡድንተኝነትን እንደ አንድ መለኪያ ብንወስድ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያዊነት እና ዘውጌነት የሁለትዮሽ ተቃርኖ ፓለቲካዊ አስተሳሰቦች ይገኛሉ።

የኢትዮጵያዊነት እና ዘውጌነት ምንታዌ ተቃርኖ አስተሳሰቦች በኢትዮጵያ:-

እነዚህ ተቃርኖዋች በኢትዮጵያ እንዳሉ እሙን ነው። እነዚህ ተቃርኖዋች ፈለግንም አልፈለግንም አሁን ባሉበት የተማጠነ ተገዳዳሪነት የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። አንዱ ከአንዱ ጋር ያለውን መስተጋብር ስንመለከት ለኢትዮጵያዊነት መኖር ዘውጌነት ግድ ባይሆንም ፤ የዘውጌነትን መኖር ማውገዝ ግን አይኖርብንም።  ይልቁን ዘውጌነት ዘመናዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ነው መሰራት ያለበት። ምክንያቱም በዘውጌነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ማጥራት ፣ ማዘመን እና ፋይዳውን መረዳት እንችላለን። ባሁኑ ሰአት ዘውጌነትን ያልተረዳ እና ከዘውጌነት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ያልገራ ኢትዮጵያዊነት አይፀናም። እንደ  ምሳሌ ኢትዮጵያዊነት ከአማራነት እና አዲስ አበቤነት ወይም ከሌሎች ቡድኖች ጋር ያለዉን ሚና እና ቁርኝት ማዘመን እና የጋራ ተግባቦት ላይ የተመሠረተ አንዲሆን ባለመደረጉ የሚፈለገዉን ያህል ወጤት እንዳያመጣ ሆኗል። ይህን ተግባቦት እና መናበብ በነዚህ ሃይላት መካከል በመፍጠር ረገድ ምሁራን ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል። በተቃራኒው ስንመለከት ለዘውጌነት መኖር ኢትዮጵያዊነት ግድ ባይልም ፤ ነገር ግን ለዘውጌነት መዘመን እና መዳበር ኢትዮጵያዊነትን መረዳት ያስፈልጋል። አንዱ ለአንዱ የህልውና መሰረት ባይሆንም : ለመዘመናቸው እና ትክክለኛ ቅርፅ ለመያዛቸው እና በጋራ ተግባቦት እና ተጠቃሚነት ላይ ለመመስረታቸው መሰረት ነው።

እውነት ነው ኢትዮጵያዊነት ሁሉ አንድ አይነት አይደለም በስልቱ ፣ በይዘቱ እና በሀሳቡ የተለያዩ ደረጃዋች እና መልኮች አሉት። እንዲሁ ዘውጌነትም መስመሩ አንድ ቢሆንም የተለያዩ መልኮች እና ክፍሎች አሉት። በዚህ እውነታ ምክንያት Binary Opposition በተቃርኖዋች መካከል dichotomy/ግልፅ መስመር ወይም ልዩነት አለ ወይም መሀል ሰፋሪ የለም የሚለው አስተሳሰብ ለኢትዮጵያዊነት እና ዘውጌነት ምንታዌ ተቃርኖዋች የሚሰራ አይመስለኝም። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያዊነት እና ዘውጌነት መካከል ያለው የእርስ በእርስ መስተጋብር ከ dichotomy ይልቅ በመሀከሉ ባሉት አስተሳሰቦች እና የተለያዩ አይነት ኢትዮጵያዊነት እና ዘውጌነት ምክንያት Continioum ወደሚለው ሀሳብ ያደላል ብዬ አምናለው።

Dichotomy/ግልፅ ልዩነት
ኢትዮጵያዊነት                           ዘውጌነት
አሃዳዊ/ግትር ኢትዮጵያዊነት ዘመናዊ/ ዲሞከራሲያዊ  ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደመ ዘውጌነት/ ቡድንተኝነት ዘውጌነትን  ያስቀደመ ኢትዮጵያዊነት ታቃፊ-አቃፊ /ዘመናዊ ዘውጌነት አክራሪ /ገፊ ዘውጌነት

 

Continioum/የተሰናሰለ ልዩነት

ሁለቱ ሰልፎች እና ቅርንጫፎቻቸዉ:-

ሰልፍ 1 / ኢትዮጵያዊነት:- ይህ ሰልፍ የሚከተሉትን ቅርንጫፎች ይዟል:

  • አሃዳዊ/ግትር ኢትዮጵያዊነት:- ይህ አስተሳሰብ ጫፍ የረገጠው እና በሀይል ዘውጌነትን የደፈጠጠ አሃዳዊ ኢትዮጵያን መመስረትን ያለመ አስተሳሳብ ነው። የኢትዮጵያዊነት ቀዩ መስመር ሲሆን ከዘውጌነት ጋር በሚፈጥረው ቅጥ ያጣ እና ያልተገባ ግብግብ ምክንያት አገርን ወደ ትርምስ ብሎም ወደ መፍረስ ሊወስድ የሚችል አደገኛ አካሄድ ነው። አደጋውን ለመቀነስም ይህን ቅርንጫፍ መስበር ወይም ወደ ሁለተኛው ቅርንጫፍ ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት እንዲንሸራተት ማድረግ ያስፈልጋል።
  • ዘመናዊ/ ዲሞከራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት:- ይህ ቅርንጫፍ እራሱን ከዘውጌ ሳጥን ውስጥ ያወጣ በኢትዮጵያውያን/በዜጎች መብት እኩል መከበር የሚያምን እና ዲሞክራሲያዊ ዘውጌነትን የተቀበለ እና በዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት የሚያምን ገንቢ አስተሳሰብ ነው። ይህ ቅርንጫፍ የመርህ ችግር ባይኖርበትም ፤ ከዲሞከራሲያዊ ዘውጌነት ጋር ተናቦ የመስራት የስልት እና የአካሄድ ችግር እንዳለበት በግልፅ አሳይቶናል። ከዲሞከራሲያዊ ዘውጌነት ጋር ያለውን የተግባቦት ችግር መቅረፍ ከቻለ ፤ የአገር ግንባታ ሂደቱን በጠንካራ መሰረት ላይ ሊያቆም የሚችል አስተሳሰብ ነው።
  • ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደመ ዘውጌነት/ ቡድንተኝነት:- ይህ ቅርንጫፍ ባለው የተለያየ የደመቀና የተደበላለቀ ስብጥር ምክንያት ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀደመ እና የሚደርስበትን መገፋት ለማስቆም ሲል ብቻ የተቧደነ እና የዘውግ ቅርፅ የያዘ ዲሞክራሲያዊ ቅርንጫፍ ሲሆን ፤  ከዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት ጋር ባለበት መጎተት ምክንያት የሚፈለገውን ርቀት መሄድ አልቻለም። ከዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት ጋር ተናቦ እና ተግባብቶ መስራት ከቻለ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የበከሉን አስተዋፅኦ ይወጣል የሚል እምነት አለኝ። በአዲስ አበባ፣ ድሬድዋ እና ሐረር ያለው በቡድንተኝነት የተቃኘ የኢትዮጵያዊነት እንቅስቃሴ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል።

 

ሰልፍ 2 / ዘውጌነት:- ይህ ሰልፍ የሚከተሉትን ቅርንጫፎች ይዟል:

  • ዘውጌነትን ያስቀደመ ኢትዮጵያዊነት:- ይህ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያዊነት እና በአንድነት የሚያምን ፤ ነገር ግን በተደጋጋሚ በደረሰበት መገፋት ምክንያት ያቀነቀነው ኢትዮጵያዊነት በሚፈለገው ልክ ከለላ ስላልሰጠው ፤ እራሱን ለመከላከል ኢትዮጵያዊነቱን በማንሸራተት በዘውጌነት የተደራጀ እና በኢትዮጵያዊነት የተቃኘ ዲሞክራሲያዊ ዘውጌነት ነው። ይህም ከላይ እንዳለው ቅርንጫፍ ከዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊነት ጋር የተግባቦት ችግር ያለበት ሲሆን፤ ይህን ችግር ቀርፎ በቅንጅት መስራት ከቻለ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የበኩሉን አዋንታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ።  እንደምሳሌ አማራው በአማራነቱ አሁን እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ መውሰድ እንችላለን።
  • አቃፊ /ዲሞክራሲያዊ ዘውጌነት:- ይህ ቅርንጫፍ ዘውጌነትን የሚያስቀድም/የሚመርጥ፣ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደ ፤ በተቀናጀ ጥረት እና በፓሊሲ ለውጥ ኢትዮጵያዊነት ሊሰርፀው የሚችል እና ከሌሎች ዘውጎች/ቡድኖች ጋር በመግባባት እና በጋራ መኖርን የመረጠ አቃፊ እና ዲሞክራሲያዊ ልንለው የምንችለው የዘውጌነት አይነት ነው።
  • አክራሪ /ገፊ ዘውጌነት:- ይህ አስተሳሰብ ጫፍ የረገጠው እና በሀይል ኢትዮጵያዊነትን በማጥፋት የአንድ ዘውግ የበላይነትን ማረጋገጥን ወይም አገር መገንጠልን አላማው ያደረገ አስተሳሰብ ነው።   የዘውጌነት ቀዩ መስመር ሲሆን ከኢትዮጵያዊነት  ጋር በሚፈጥረው ያልተገባ ግብግብ ምክንያት አገርን ወደ መፍረስ ሊወስድ የሚችል ብሎም ፋሺስታዊ አረመኔነት ውስጥ በመግባት ሰሞኑን የተመለከትነው አይነት አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋ ሊፈፅም የሚችል  አደገኛ አካሄድ ነው። አደጋውን ለመቀነስም ይህን ቅርንጫፍ መስበር ወይም ወደ ሁለተኛው ቅርንጫፍ ዲሞክራሲያዊ ዘውጌነት/ አቃፊነት  እንዲንሸራተት ማድረግ ያስፈልጋል።

እነዚህ ሁለት ሰልፎች አሁን ከደረሱበትን የእድገት ደረጃ አንፃር፤ ሁለቱን ሰልፎች ወደ አንድ ማምጣት ወይም አንዱ አንዱን እንዲውጠው ማድረግ የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል። ይልቁን በሁለቱም ሰልፎች ውስጥ ያሉትን ዲሞክራሲያዊ/አረንጎዴ ቅርንጫፎች በማጎልበት እርስ በእርስ እንዲናበቡ እና በጋራ ለጋራ ጥቅም እንዲሰሩ ማድረግ ግዜው የሚጠይቀው ሁነኛ መፍትሄ ነው። ለጋራ ተጠቃሚነት፣ ለአገር ሰላም እና አንድነት ሲባል ፤ በግራም በቀኝም ጫፍ የረገጡትን ሁለት ቀያይ አክራሪ ቅርንጫፎች መስበር ወይም ወደታች ማንሸራተት አማራጭ የሌለው የህልውና እርምጃ ነው።

 

የሁለቱ ሰልፎች እዉነት:- የትኛው ሰልፍ ነው እውነተኛው ሰልፍ ? እውነትስ ከማን ጋር ቁማለች?

ሁሉም የራሱ የሆነና በሂደት የገነባው የራሱ እውነት እና የእይታ መነፅር አለው። ስለሆነም  እውነት ነው ተብሎ የታመነው ሁሉ እውነት አይደለም ፤ ውሸት ሁሉም ውሸት አይደለም። እውነትን በጋራ እስካልገነባን ወይም የጋራ የእይታ መነፅር እስካላበጀን ድረስ ፤  በእውነት ውስጥ ውሸት፤ በውሸት ውስጥም እውነት አለ ።  ማህበረሰባዊ እውነት በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን፤ በማህበረሰቡ በሂደት በጋራ የሚገነባ ነው። ስለዚህ ማስተካከል የምንችለው አሁን ሰልፎቹ የያዙትን እውነት ሳይሆን ፤ በቀጣይነት ሰልፎቹ እውነት የሚገነቡበትን መንገድ እና ሂደት ብቻ ነው። ውሸትን እውነት አርጎ የመገንባት እብሪት እና እውነትን እውነት አርጎ ለመገንባት አቅም ማጣት አገር ያፈርሳል።

ስለዚህ በሁለቱ ሰልፎች መሀል እውነት እኔ ጋር ነው እያሉ መወነጃጀል መፍትሄ አይሆንም፤ ይልቁን የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ፣ ሀቅ የሆነ እና የጋራ የሆነ እውነት የምንፈጥርበትን ሂደት እና ተቋማት በጋራ ለመፍጠር እንሞክር  መልክቴ ነው።

 

ይቆየን

ሰሎሞን ጌጡ ከኑረምበርግ

21.07.2020

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop