ዉይይት፣ ኢትዮጵያ ከእንግዲሕ

ከድምፃዊነቱ እኩል በ2010 ለተደረገዉ ለዉጥ በተደረገዉ ትግል እዉቅናን ያገኘዉ ሐጫሉ ሁንዴሳ  ባለፈዉ ሰኔ 22 መገደሉና መዘዙ ያስከተለዉ ቁጣ፣ ጥፋትና ዉዝግብ ለዓለም ደግሞ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያበቃዉ ለዉጥ ጨርሶ እንዳይጨናጎል ብዙዎችን እያሰጋ ነዉ

ማስታወሻ፤- ይሕ ዥግጅት ባለፈዉ ዕሁድ (12.11.2012) የተሰራጨዉ ዝግጅት ረጅም አካል ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በየዘመኑ በተለይም ባለፉት 80 ዓመታት የተደረጉት የሥርዓት ለዉጦች ለየዘመኑ ሕዝብ የተሻለ አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ የዕድገት ብልፅግና ተስፋ እየፈነጠቁ በየዘመኑ ሥልጣን በሚይዙት ኃይላት ፍላጎትና በልሒቃን ስሕተት ተጨፍልቀዋል።

ኢትዮጵያዉን አርበኞች የኢጣሊያን ወራሪ ጦር ከ5 ዓመታት ትግል በኋላ በ1933 ድል አድርገዉ ሐገራቸዉን ነፃ ማዉጣታቸዉ፣ ለዚያ ዘመኑ ትዉልድ የጀግነቱ ኩራት፣ነፃ የመዉጣቱ ብስራት፣በነፃ ሐገሩ እኩል የመኖር-የመጠቀሙ ተስፋ፣ የዕድገት ፍላጎቱ መሰረት መጣሉ መስሎ ነበር።

የ1966ቱ የሥርዓት ለዉጥ የብዙ ኢትዮጵያዉን የረጅም ጊዜ ትግል ዉጤት፣ የልማት ዕድገት፣የእኩልነት ተስፋም ነበር።በ1983 ሌላ የሥርዓት ለዉጥ ነበር።ሌላ ተስፋ።የሰላም፣ የዴሞክራሲ፣ የልማት፣ ብልፅግና ትልቅ ተስፋ።

መጋቢት 2010 የበረቀዉ የለዉጥ ጭላጭልም እንዲሁ አዲስ ብሩሕ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር።ሁሉም ለዉጥ ግን ሕዝብ የሚመኘዉን ወይም ለአብዛኛዉ ህዝብ የሚጠቅመዉን ልማት፣ዕድገት፣ መልካም አስተዳደር አላመጣም።

ከድምፃዊነቱ እኩል በ2010 ለተደረገዉ ለዉጥ በተደረገዉ ትግል እዉቅናን ያገኘዉ ሐጫሉ ሁንዴሳ  ባለፈዉ ሰኔ 22 መገደሉና መዘዙ ያስከተለዉ ቁጣ፣ ጥፋትና ዉዝግብ ለዓለም ደግሞ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያበቃዉ ለዉጥ ጨርሶ እንዳይጨናጎል ብዙዎችን እያሰጋ ነዉ።የስጋቱ ደረጃ የልሒቃኑ ልዩነት  እና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ጉዞ ያፍታ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አምስት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች አባላቱ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ

4 Comments

  1. Berhane Meskel Sign hold the J.D. from university Minnesota, he never earned a doctoral degree at all. A Juris Doctor degree is the highest law degree in the United States and was originally a replacement to the Bachelor of Laws degree. I don’t know why this accepts when some one called him a doctor, his degree is equivalent to the Bachelor of Laws degree.
    Please stop calling him doctor

  2. ነጋሽ መሀመድ መች የህዝብ ጥያቄ ሆነ ብለህ ነው? እንደጋበዝከው ብርሀነ ሰኒ አይነት አድር ባይ ሲሾማቸው ካድሬ ሲገፏቸው ህዝብ ተገፋ የሚሉ ስብእና የሌላቸው ሰዎች እስካሉ ድረስ ችግሩ ይቀጥላል። ሌላው ግብጽ ጭኖ ይልክዋል እሱም የተከፈለውን ያህል ይበጠብጣል። እንዲህ አይነት ፕሮግራም ስታቀርብ ባላንስ የሚጠብቁ ወገኖችን አብረህ ብትጋብዝ መልካም ነበር።

  3. ነጋሺ መሀመድ ታላቅ ዜጋ ነህ እናዉቃለን አማርኛ የጠላት ቋንቋ ነዉ የሚል ታዳሚ በአማርኛ ፕሮግራም ተገቢ ስላልሆነ ወደፊት ብታስብበት መልካም ይመስለኛል። ብርሀነ መስቀልን ወጥረህ ልትይዘዉ በተገባ ነበር ተጀምሮ እስኪያልቅ ዉሸት ብቻ በመሆኑ። አንድ አሃዝ አልቆጠረለህም።

  4. ነጋሽ መሀመድ
    ብርሃነ መስቀል መስቀል በጭራሽ የዶክቶሬት ዲግሪ አግኝቶ አያውቅም
    ዶክትርም አደለም የውሸት ዶክተር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share