በኮለምበስ ኦሃዮ የአማራ ተወላጆች ማህበር ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰጠ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ

18/08/2012

የአማራ ህዝብ ለሕግ የበላይነት ፣ ለሰላምና ዴሞክራሲ መረጋገጥ ታላቅ ክብር ያለውና ለዘመናት ሀገሩን ለመገንባት ዘር ቀለም ሳይለይ ሲታትር ብሎም ገንዘቡን ፣ ጉልበቱንና ጥበቡን ተጠቅሞ ኢትዮጵያ እንደሀገር እንድትቆም ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ሀገር ያቆመና የገነባ ሕዝብ ነው። ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ ዛሬ ለአማራ ህዝብ ቅንጦት የሆኑበት መሠረተ ልማት፣ ህክምና፣ ዘመናዊ ትምህርት፣ እድገትና ብልፅግና ቀርቶ ሕዝባችን ሰብዓዊና ሕገመንግስታዊ መብቱ ተነፍጎ፣  የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት ፣ ሀብት የማፍራት ነፃነቱ ተገፎ ፣ በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ እኩል የሀብት ተጠቃሚ እንዳይሆን ተደርጎ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደለና እየተፈናቀለ እንዲሁም መሬቱ እየተቆረሰና ርስቱ ያለአግባብ እየተሸነሸነ በገዛ ሀገሩ ባይተዋር እንዲሆን ተደርጓል። አልፎ ተርፎም ላለፉት አመታት በመንግስታዊ አወቃቀር አማራውን ለጥቃት ያጋለጠ ትርክት በማኒፌስቶ ተቀርፆ ስለተሰራበት በህዝባችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል ። ዛሬም እንደቀድሞው በህዝባችን ላይ የሚደርስበት በደል ተጠናክሮ በመቀጠሉ የህዝባችን ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ ይገኛል። በመሆኑም በኮለምበስ የምንኖር የአማራ ተወላጆች እየተፈፀመ ያለውን ዘግናኝ ተግባር በመቃወምና በማውገዝ የሚከተለውን ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል ።

1ኛ. በአማራ ክልላዊ መንግሥትና በነሻለቃ መሳፍንት የፋኖ ሕዝባዊ ሚሊሻ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እናደንቃለን :: ይሁንና ስምምነቱ ዘላቂ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ይወጣ ዘንድ እየጠየቅን ህገወጦችን ለማጥፋት በሚል ስበብ በአማራ ክልል የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በከባድ መሳሪያ በታገዘ ጦር በማዝመት ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆኖ አምባገነኑን ስርዓት ያባረሩ ጀግኖቻችንን ማሳደድ፣ ማሰርና መግደል በአስቸኳይ እንዲቆምና መከላከያ ሰራዊቱ ከክልላችን እንዲወጣ በአፅንኦት እናሳስባለን ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖች አየመጡ ነው ብለው በታላቁ ሩጫ ላይ ዘመሩ | 65 ቢሊዩን ብር የገባበት ጠፋ!

2ኛ. ለአማራ ሕዝብ ደጀን የሆነውን ፋኖን የታጠቀ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ብሎ ያለአግባብ መፈረጅን እንቃወማለን ::

3ኛ. በገዥው ሥርዓት የሚደረጉ ስብሰባዎች የኮሮና ቫይረስን ስርጭት የሚያባብሱ ከመሆናቸው አንፃር ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም እንዲሁም በክልሉ የሚደረገው ቫይረሱን የመቆጣጠር ስራ እንዲሻሻል እንጠይቃለን ::

4ኛ . ከታገቱ ከአራት ወራት በላይ  ያስቆጠሩትን የደንቢዶሎ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች የደረሱበትን ሁኔታ መንግስት በአስቸኳይ ለህዝብና ለቤተሰቦቻቸው እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን ::

5ኛ. የትግራይ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ በተደጋጋሚ ወደ ክልላችን ዘልቆ በመግባት የሚፈፅመውን አፈናና ግድያ መንግስት እንዲያስቆም እንጠይቃለን ::

6ኛ. የአማራ ክልል መንግስት  ከክልሉ ውጭ ለሚኖሩት አማራዎች ዋስትና እንዲሰጥና ህዝባችን በሚኖርበት አካባቢ የራሱን ህዝብ የማስተዳደር መብቱ እንዲጠበቅ እንጠይቃለን ::

7ኛ. የአማራ ክልል  በተለያየ መልኩ የኃይል ሚዛኑን እንዳይጠብቅ የሚደረገውን አሰራር እንቃወማለን ::

8ኛ. በቤንሻንጉል ክልል  በመተከል ዞን በየጊዜው በአሰቃቂ ሁኔታ በአማራዎች ላይ የሚፈፀመው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆምና በገዳዮቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን ::

9 ኛ. አለም አቀፉን ማህበረሰብ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ኮሮና የተባለ ወረርሽኝ በተከሰተበት አስከፊ ሰአት በአዲሰአበባ ከተማ የዜጎችን መኖሪያ ቤት በማፍረስ መንገድ ላይ እንዲወድቁ ማድረግ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን።

10ኛ . የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ በከተማው ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የቀን ሰራተኞችንና የጎዳና ልጆችን ወደ ክልላችን ላኩን ብለውናል በሚል ምክንያት ከ5 አዉቶብስ በላይ ሰዎችን ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ ወደ አማራ ክልል  እንዲበተኑ ማድረጉን እንቃወማለን ::

11ኛ. የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት በሀይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው በመሆኑም መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ከጥፋት እንዲከላከልና በጉዳዩ ላይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሥሩ ዋንጫዎች:- አሥሮቹ ጀግኖችና አሥሩ ዓመታት በኦልድትራፎርድ – ክፍል 2

 

በኮለምበስ ኦሃዮ የአማራ ተወላጆች ማህበር ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ

ኮለምበስ ኦሃዮ

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ !!!”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share