በመላው አለም ከሚኖሩ የአርማጭሆ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

1/3/2020

ሰሞኑን በምዕራብ ጎንደር፣ በአርማጭሆና ጠገዴ መካከል በታጠቁ ሽፍቶች የታገቱ ስድስት ህጻናት መጨፍጨፋቸውን ስንሰማ እግጅ ከባድ ሀዘን ተሰምቶናል፣ አስደንግጦናል፣ አበሳጭቶናል። ይህ በታዳጊ ህጻናት ላይ የተፈጸመ ጥቃት የቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን፣ ወላጆች የሆንን፣ ከዛም አልፎ ሰዎች የሆንን ሁሉ ጥቃት ነው። ይህ ጥቃት የጎንደር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአማራው ህዝብ  ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊያሳስበው ይገባል።  ጎንደር ክፍለሀገር በተለይም አርማጭሆና ጠገዴ ተደጋጋሚ መርዶ የሚሰማበት፣ ህጻናት ላይ ግፍ የሚፈጸምበት፣ ህዝብ የሚፈናቀልበት አካባቢ ከሆነ ቋይቷል። በዚህ የተቀነባበረ ሴራ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለማጽናናት፣ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ ከምንጊዜውም የበለጠ የመግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና ህዝባዊ ማህበሮች አስቸኳይ እርዳታና ትብብር ያስፈልጋል።

ይህ ህጻናትን አግቶ ገንዘብ የማስከፈል ወንጀል በጎንደር ዙሪያ የተለይም በአርማጭሆ ሰንብቷል። በርካታ ሰዎች የታገቱ ልጆቻቸውን ለማስፈታት በመቶ ሺዎች ብር የሚቆጠር ገንዘብ መክፈላቸው የታወቀ ነው። አብዛኛው የገንዘብ ሽግግር የሚካሄደው ከተማው ውስጥ ባሉ ደላላዎች አማካኝነት ስለሆነ መንግሥት ችግሩን አያውቅም ለማለት ያስቸግራል። ከሁሉ የሚያሳዝነው፣ አርሶ አደሮች በመግሥት እምነት ስለሌላቸው ሽፍቶች የሚጠይቋቸውን ገንዝብ ንብረት ሽጠውም ሆነ ተበድረው መክፈል ይገደዳሉ። አንዳንድ አርሶ አደሮች ወንጀሉን ለመንግሥት አስታውቀን ባለስልጣናቱ ወንጀለኞችን አይከታትልም ወይም ደግሞ ለወንጀለኞች መረጃውን በማቀበል በተጎጅዎች ላይ ችግር ይፈጥራሉ የሚል ጥርጣሬ  አላቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ከሽፍቶች የሚደርሳቸውን የስልክና የቴክስት መልዕክት ለመንግሥት ሪፖርት አድርገን እርምጃ አይወሰድም ይላሉ። ይህም ሁኔታ ህዝቡ በመግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገው መጥቷል።  በዚህ ችግር የተነሳ በርካታ ገበሬዎች ችግሩን መቋቋም ባለመቻላቸው መኖሪያ እና የእርሻቸው ቦታቸውን እየተዉ ህይወታቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ከተማ በብዛት እየፈለሱ ነው። በርካታ የሃይማኖት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች በነዚህ ሽፍቶች ምክንያት የተለቀቁ መሆናቸው ተገልጿል። ከሽፍቶች ጋር ሲበሉና ሲጠጡ የሚውሉት የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ይህ ሁሉ የተቀነባበረ ደባ በህዝብ ላይ ሲፈጸም አያውቁም ማለት ይቻላል ወይ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዜና ዘ-ትግራይ (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

ትህነግ/ሕወሓት በአርማጭሆ እና የጠገዴ ህዝብ ላይ ደባ መሥራት የጀመረው የዛሬ አርባ ዓመት ወደ ወልቃይት ጠገዴ እንደገባ መሆኑ አይዘናጋም።። አማራ ጠላት ነው የሚለውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈጸም እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸውን ታሪክ የሚያውቁ ብዙ የህዝብ መሪዎችን በረቀቀ ዘዴ አጥፍቷል። ቀጥሎም በአምሳሉ የፈጠራቸው የብአዴን/አዴፓ መሪዎች አማካኝነት ህዝብን ከህዝብ በማናከስ በመላው ጎንደር ግጭቶች እንዲፈጠሩና ህዝቡ ከመኖሪያው እንዲፈናቀል፡ በአካባቢው ሰላም እንዲጠፋ የማድረግ ጸረ ህዝብ ተግባራቸውን እነደቀጠሉ ናቸው። ሰሞኑን በአርማጭሆና ጠገዴ ህዝብ ላይ የተፈጸምው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የዚህ ሴራ አካል በመሆኑ፤ እኛ በመላው አለም የምንኖር የአርማጭሆ ተወላጆች፤

  1. በንጹሀን ልጆቻችን ላይ የተፈጸመውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በጥብቅ እያወገዝን፣ የክልልና የፌደራል መንግሥት በአስቸኳይ ወንጀለኞችን ተከታትለው ለፍርድ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፣
  2. በዚህ ጨካኝ ጭፍጨፋ ለተጎዱ ወላጆች፣ ቤተሰቦችና በጠቅላላው ለአርማጭሆና ጠገዴ ህዝብ ጥልቅ ሀዘናችንን እየገለጽን፣ ወንጀሉን የፈጸሙት ሽፍቶች ተይዘው ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ከጎናችሁ ተሰልፈን ለልጆቻችሁ፣ ለልጆቻችን ድምጽ ሆነን ለመቆም ቃል እንገባለን፣
  3. በአርማጭሆና ጠገዴ የምትገኙ የሀገር ሽማግሌዎች፤ የሀይማኖት መሪዎችና በጠቅላላው ማህበረሰቡ፣ በልጆቻችን በተፈጸመው ጭፍጨፋ ለተጎዱ ቤተሰቦች በምክር፣ በጽሎትና በተለያዩ መንገዶች እርዳታ በማድረግ እንድትተባበሩ እንለምናለን፣
  4. በጎንደር ክፍለሀገር የምትንቀሳቀሱ የእርዳታ ሆነ የልማት ማህበራት በክፍለሀገሩ የተከሰተው ማህበራዊ ችግር ተዛማች ስለሆነ ጎንደርን ለማሳደግ የሚካሄደው ጥረት ሁሉንም አካባቢ ያካተተ እንዲሆን እንጠይቃለን፣
  5. ህጻናት የማገቱ ወንጀል በጎንደር በተለይ ደግሞ በአርማጭሆ የሰነበተ ማህበራዊ ችግር በመሆኑ፣ የክልሉ መንግስት በሌሎች ክልሎች እንደሚደረገው፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉ ከውጭም ከውስጥም የሚኖሩ የአካባቢውን የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና የሀይማኖት መሪዎች ያካተት የመፍትሄ ፍለጋ መድረኮች እንዲመቻቹ አጥብቀን እንጠይቃለን፣
  6. ወልቃይት ጠገዴ፣ ሁመራና ጸለምት ላይ የሰፈረው የወያኔ አገዛዝ አርማጭሆን ለማፈናቀልና አቅም ሲፈቅድለት አካባቢውን መቆጣጠር ህልሙን ዛሬም የቀጠለበት በመሆኑ፣ ሴራውን በማክሸፍ የአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ለማስክበር በትብብር እንድንሰራ ጥሪ እናደርጋለን፣
  7. በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ ወጣቶች ከሥራ እና ከትምህርት ተገልለው በገጠርና በተማ መሳሪያ ይዘው እንደሚዘዋወሩ ይስተዋላል። መንግሥት ለችግሩ ትኩረት ሰጥቶ ወጣቶችን ለሥራ የሚያበቃ የሞያ ማስልጠኛ ትምህርት ተሰጥቷቸው በመንግሥት ወይም በግል የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ሀገራቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት እንዲችሉ አሰፈላጊውን ትብብር እንዲያደግ እናሳስባለን፣
  8. መንግሥት ከሁሉ በፊት ግብር የሚያስከፍለውንና ይመርጠኛል የሚለውን ሕዝብ ደህንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩና ኃለፊነቱ ስለሆነ የፌደራልና የክልል መንግስት በአስቸኳይ የአካባቢውን ሕዝብ በማስተባበር ኃይሉን አሰማርቶ ወንጀለኞችን በመያዝና ለፍርድበ በማቅረብ የሕዝቡ ሰላም እንዲረጋገጥ አጥብቀን እጠይቃለን።
  9. በህዝብ መዋጮ፣ ለህዝብ አገልግሎት የተቋቋማችሁ የሚዲያ ተቋማት፣ በህዝብና በሀገር እንዲህ አይነት ግፍ እየተፈጸመ ስለሆነ፤ ችግሩን በማጋለጥና ትክክለኛ በመረጃ በማቅረብ ህዝብን እንድትረዱ እናሳስባለን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል

እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 

ለበለጠ መረጃ፤

armachihogonder@mail.com

1 Comment

  1. In today’s Ethiopia roads , clinics, hospitals , schools , buildings , bridges , statehood , cash material etc is doable in selected places .

    Rule of law , justice , security , safety , fairness is something the country is out of practice (not doable anytime soon) . Remember in selected places at least more than one third of the country is under state of emergency martial law , the whole country is not because ????

Comments are closed.

Share