እነ አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ከነብዩ ኤልያስ አመጣነው ያሉትን መልዕክት ይፋ አደረጉ

July 28, 2013

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ወትሮም በአወዛጋቢነቱ የሰነበተውን የነብዩ ኤልያስን ወደ ምድር መምጣትና በአራት ኪሎ እንደሚገኝ የተነገረውን ጉዳይ ይበልጥ እንዲያነጋግር አድርጎታል። ጋዜጣው በዘገባው አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረጉ ብሏል። በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ” የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ቅዱስ ኤልያስ በ2000 ዓ.ም ከመንግስተ ሰማያት ወደ ቅድስት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አስተምሯል ያሉት የማህበሩ በቅዱስ ኤልያስ፣ በሄኖክና በመልከፄዴቅ የተባረኩ በመሆናቸው እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የዳዊት መዝሙር ላይ በመመስረትና፣ ፓትሪያርኩ የቅዱሳን ሊቃውንት ክብረ በዓላት በብሔራዊ ደረጃ ለማስከበር በቦታው መገኘት ይገባቸዋል በማለት ፓትርያርኩን አሳስበዋል፡፡ የማህበር አባላት በኢትዮጵያ ደረጃ መስከረም 7፣ 12፣ 21 እና የካቲት 21 ብሔራዊ በዓላት እንዲሆኑ ነው ፓትሪያሪኩን ለመጠየቅ የፈለጉት ሲል አዲስ አድማስ ዘገባውን አጠናቋል።

ለግንዛቤ እንዲረዳ ለኤልሳውያን ወይም ለነጀማነሽ ስለሞን አዲስ እምነት ዲያቆን ምህረተአብ አቅርቦት የነበረውን ምላሽ ቪድዮ ከዚህ በታች አቅርበናል።

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop