July 18, 2013
10 mins read

ትንሽ ስለጃዋራዊያን (ለፋሲል የኔአለም መልስ)

ጎሳዬ(ጆሲ) ደስታ
አቶ ፋሲል የኔአለም እጄን ጠምዝዞ ክፉ ነገር ሊያናግረኝ እየገፋፋኝ ነው። “ትንሽ ስለጃዋራዊያን” በሚል ርእስ የጻፈው አስደናቂ ጽሁፉ ከልብ አስደስቶኛል። ሆኖም ግን አመለካከቱ አሁንም ሌላ ጀዋርን ከማስተናገድ የሚቆጠብ ስላልመሰልኝ አንድ ሁለት ነገር ላክልበት ተገድጃለሁ። በመጀመርያ ደረጃ በኛተቃዋሚ ውስጥ በሚድያ ገነህ ስላለህ ብዙ ግዜ ታግሼሃለሁ። ሆኖም ላርምህ ብሞክር ብዙ ሰው ቢያስቆጣም የመጣው ይምጣ ብዬ ልነግርህ መጥቻለሁ።
ጽሁፍህ ወደ መሃል ላይ እንድህ ይላል “አንድ ግዜ እናቴን አንቺ እኮ የኦሮሞ ደም አለሽ ፣ ይህ አካባቢ እኮ በኦሮሞዎች የተያዘ ነበር አልኩዋት”። አንተ ያንን ያልከው የጀዋርን ልብ ለማማለል ከሆነ ስለ ብሄርተኝነት የጠበቀ ግንዛቤ የለህም ማለት ነው። ታይለኖል ተውጦ ሚዳን ቢሆን ኖሮ እነ አቶ መለስበደዌው ተለክፈው ባልሞቱ ነበር። ኦሮሞ መሆን የሚያኮራ መሆኑን ማንም አይክድም። ግን ኦሮሞ ያልሆኑትን ሴትዮ በግድ ኦሮሞ ነሽ ማለት እራሱ ከኦነግ ጠባቦች አስተሳሰብ የተለየው ምኑላይ ነው? አንተ በግልህ ኦሮሞ መሆን ከፈለክ ሙሉ መብህ አለህ። ግን ያልሆኑትን አጉል ለመወደድ ብቻ በሚልሂሳብ ማስላቱ አስፈላጊነቱ አይገባኝም። አንድ ኢትዮዽያ ካልን ዘንዳ ምን ከዚ ነሽ ወይም ከዛ ነሽ አመጣው? ሁለትና ሶስት ትውልድ ከተዋለዱበት ቦታ ሰላማው ዜጎችን ያፈናቀለው ይህ አይነት አያትሽ/ህ ከዚ ብሄር ነው የመጣው የሚል አስተሳሰብ መስሎኝ? ደሞ ባክብሮት የምነግርህ ፥ የራስህትንአይደንቲቲ ክራይሲስ ሳትጨርስ ሌውን ለመስበክ ባትሞክር ጥሩ ይመስለናል።
ጽሁፍህ ወደመጨረሻ እንዲህ ይነበባል “…ፖለትከኞች ስልጣን ሲያምራቸው ታሪክን አጣመው ደጋፍዎችን ለማሰባሰብ ይሻሉ…”። እንደውም በተለይ አንተን ብዙ ግዜ በዚ ጉዳይ ኢሜል ላደርግህ ፈልግ ነበር። ለምሳሌ ያክል አንድ የአማራ ተውላጅ ድሮ ጫካ የነበረና በህዋላም ብአዴን ሆኖ ደሞ አሁንየከዳ ወጣት ኢንተርቪውን በሚያደርግበት ሰአት ደግመህ ደጋግመህ ኦነግ አልገደለም ወያኔ ነው የገደለው ብሎ እንዲናገር ስታጣድፈው ታይትዋል። እንድሁም በሌላ ግዜ ደሞ መምህር ኣባ ኒቆዲሞስ ኣስፋው ስለኦነግ አሰቃቂ ድርጊት ሲተነትኑ ወያኔ ብቻ ነው ያደረገው ብለው እንዲናገሩ ስታስጨንቃቸውነበር። ያንን ደሞ ስታደርገው የነበረው ከኦነግ ጋር የጀመራቹት ሰርግ ድግሱ ገና ስላላለቀ ነበር። አንተ የተደረገን ታሪክን በፈለከው መንገድ እየጠመዘዝክ ሌላውን እንዴት ልትገስጽ ታስባለህ። እኛ ዘመዶቻችን መሄጃ አጥተው ከዶዶላና ካርሲ አካባቢ እንደ እባብ እየታደኑ ሲጨፈጨፉ ማደርያ ቦታ አጥተውየዘመድ ቤት ሞልቶ ግቢ ሳር ላይ ሲያድሩ የምናውቀው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። ባህርዳር በሰላሙ ሃገር አንተ አኩኩሉ ስትጫወት ሌላው ሲታደን ነበር። ከፈለክ የብሄር ብጥብጥ ያስነሳል ብዬ ነው እንጂ ዝርዝሩን ማፍረጥረጥ ይቻላል። ላሁን ግን የዚህ ጽሁፍ አላማ ስላልሆን ቁስሉን አንካው።
ሃሳብህን ስታጠቃልል “አንድነት የሚሰብኩት ወገኖች ጃዋርያውያንን በመሳደብ ፣ በማውገዝ ፣ በማግለል ወይም ፎቶግራፋቸውን በማበላሸት ማሸነፍ እንደማይቻል ልብ ሊሉት ይገባል። እንድህ አይነቱን አስተሳሰብ ማሸነፍ የሚቻለው የተሻለ አስተሳሰብ በማምጣትና በመሞገት ነው” ብለሃል። በሃሳብደርጃ እስማማለሁ። ግን ታድያ ያንተ አይነት ፍልስፈና የሚሰራ ከሆነ ለምን ጀዋር የጥግ ፖለቲካ አራማጅ ሊሆን ቻለ? ወይንስ በቲቪ ስታሰድቡን ስለነበር ሃፍረትህን ለመሸፈን ምታደርገው መርበድበድ ነው? ሆነም ቀራም ጀዋር በገጀራ እንደማይመለስልን ነግሮናል። አቶፋሲል ደሞ ወረቀት ላይ ታሪክእየዘረዘርን መምዋገቱ ያዋጣናል ነው ምትለን። የፖለቲካ ተንታኝ ተብዬው የዘላበደው የተወሰነ ያፍ ወለምታ ቢሆን ኖሮ አቶ ፋሲል ያለው ይሰራ ይሆናል። ግን ግለሰቡ ጅማቱን ገትሮ በሜጫ አንገታችንን እንደሚለን እየነገረን ታድያ እንዴት ነው የታሪክ እና የፖለቲካ ፍልስፍና በማንጋጋት የምንወጣው?ፈረንጆች ለንደዚ አይነቱ ቀልድ ሲተርቱ “Don’t bring a knife to a gun fight” ይላሉ። ጠመንጃ ለሚያስፈልገው ውግያ ቢላዋ አታምጣ እንደማለት ነው።
እንደውም አቶ ፋሲል አልሰማውም ይሆናል እንጂ ባለፈው ሰይፈ ነበልባል በሚባል ሬድዮ ላይ ጀዋር ቀርቦ ካንድነት ሃይሎች ጋር መስራት እንደማይቻል ሲናገር ነበር። እናም እንዴት አድርገህ ነው ታድያ እሱንና መሰሉን የምታክማቸው? ያንተ ፕለቲካዊና ታሪካው ትንታኔ እንከን ማይወጣለት ሆኖ ሳለ ፣አንተን ከመሰለ የበሰለ ፖለቲካኛ የዚህን ግለሰብ ድብቅ አላማ ለማወቅ ይከብድሃል ብዬ አላምንም። እናም ልቦናህ እያወቀው ለምን እኔንም ግዜዬን ትገድላለህ አንባቢንም ታደክማለህ። እስከመቼ ነው እንደዚ አይነት አመለካከትን ተሽክመን እንድንሄድ ምንደረገው? አደባብሶና አለባብሶ የታለፈው ሁሉግዜውን እየጠበቀ ሲፈነዳ ፍንጣሪው አካላችንን እያሰናከለው ይገኝኛል። አንገታችንንም እያስደፋን ነው።
የሆነ የፖለቲካ ነውጥ በመጣ ቁጥር ተስፋዬ ገ/አብ ጋር ተሩጦ ትንታኔ መጠየቅ ምን አመጣው? የቡርቃ ዝምታን ጨምሮ ሌሎችንም መርዛማ መጽሃፎችንና መጣጥፎችን በማምረት የሚታወቀውን ግለሰብ እግር ስር መርመስመስንስ ምን ይሉታል? ደሞ ሌላ ነገር ሲመጣ በብሄርና በሃይማኖት የሰከሩግለሰቦችን ካሉበት በሻማ እየፈለጉ ባደባባይ እኛን ማሰደቡ አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? ዳዊትም ቢሆን ቀኑን ጠብቆ ተናከሰ። ይሄ ሁሉ ትልቅ ትምህርት ሊሆንህ ይገባል። የሚናደፍ እባብን ለምድዋል ብለህ ኪሳህ ውስጥ ጨምረህ ስቴድ ነደፈህ። ጀዋር ላንተ አዲስ ሆነብህ እንጂ ድሮም አሁንም ያው ነው።ደሞ ያንያክል ወረቀትና ግዜ ፈጅቶ የፖለቲካና የታሪክ ጋጋታ ሚያስፈልገው ጉዳይ አልነበረም።
አሁን የፖለቲካው ትንተና ጅብ ከሄደ በህዋላ ምን ጮህች ነው ሚያስብለው። ያለፈው አልፍዋል ግን ኪኒንህን ዋጥ አድርገህ ለመወደድ ሳይሆን ላላማህ መስራት ይጠበቅብሃል። ይሄ እንደምክር ቢጤ ይሁንህ። አልሰማም ካልክ ደሞ ለጀዋር ያቀድነው ድግስ ላይ አናንተን እንሞሽርበታለን። ላሁኑ በሁለትብጫ አልፈንሃል። በተጨማሪ ደሞ ለኛ ወጣቶች ስትል ሃሳብህን አጠር አድርገህ ጻፈው። ያንሁሉ ለማንበብ ግዜ የለንም። የኦቶዋን ኢምባዬር ቱርኮች ይጨነቁበት እኛ በፊልም ካየነው ይበቃናል። በቸር እንሰንብት

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop