January 30, 2016
16 mins read

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት:- ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ – መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ

ሐሙስ ጥር ፲፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. (Thursday January 28, 2016)                                                                

ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት፣ 

 ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ

በያሉበት

 

ጉዳዩ፦ መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ፦ እስከ አንድነት ለመድረስ የሚያስችል ውጤታማ ትብብር ለማድረግ መከተል ስለሚገባን አካሄድ፤ 

 

ማናችንም እንደምንገነዘበው፣ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ስንደራጅ የኖርነው በልዩነቶቻችን ላይ ባተኮሩ ዓላማዎች ዙሪያ ነው።ልዩነቶቻችን ደግሞ ከርዕዮተ-ዓለም ባሻገር፣ በነገድ፣ በጎጥ እና በኃይማኖት ጭምር ያጠነጠኑ በመሆናቸው፣ አንድነታችንን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ከሁሉም በላይ፣ የትግሬ-ወያኔ በባዕዳን ድጋፍ ተበረታትቶ፣ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ሲጨብጥ፣ ያስተጋባው የዲሞክራሲ ቀቢፀ-ተስፋ እውነት መስሏቸው የተከተሉት ወገኖች አይጠፉም። ሆኖም ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን በተግባር ሲያከናውን የሚታየው፥ የቋንቋ ፣ የነገድ ፣ የጎሣ ፣ የዘር ፣ የኃይማኖት ፣ ወዘተርፈ ልዩነቶችን መሠረት አድርጎ ሕዝቡ ለዘመናት ገንብቶት በኖረው ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ግልጽ የጥፋት ዘመቻ ማካሄድን ነው። የትግሬ-ወያኔ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በአካሄደው የዘር ልዩነት ፖለቲካ ግፊት፣ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ችላ እያለ፣ በቋንቋ ማንነቱ ዙሪያ ብቻ እንዲያስብ እና እንዲደራጅ አድርጓል። በዚህም ምክንያት ለሕዝቡ አንድነት ጌጥ እና ውበት፣ ጥንካሬ እና ልዩ መታወቂያ የሆኑት ነባራዊ ልዩነቶች የጠብ እና የብጥብጥ መነሻዎች ሆነዋል። በዚህ ረገድ የአያሌ ዜጎች ሕይዎት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን እናውቃለን። በተለይም ኢትዮጵያውያን ዐማሮች የአማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ተለይተው ሀብት ንብረታቸውን እየተዘረፉ መባረራቸውን ማስታወስ ይበቃል።  በዐማራ፣ በአኙዋክ ፣ በሶማሌ እና በሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሊገታ አለመቻሉ  የአደባባይ ምስጢር ነው። ስለዚህ ይህ ድርጊት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ስለሆነ፣ አፋጣኝ እና መሠረታዊ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው።

የትግሬ ወያኔው አገዛዝ በሥልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን በማራመድ ሳይሆን፣ የጀመረውን  የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን እያራቀቀ በመሄድ ብቻ መሆኑ ከእንግዲህ ሊያጠያይቅአይችልም። ስለሆነም፣ ይህን  የትግሬ ወያኔውን አገዛዝ በጠመንጃ ኃይል ከጨበጠው የፖለቲካ ሥልጣን በእርግጠኝነት በማላቀቅ አሽቀንጥሮ  ለመጣል ከኢትዮጵያውያን አንድነት የተሻለ አስተማማኝ መሣሪያ አይኖርም። ለዚህ ደግሞ፣ እስካሁን የተጓዝንበትን የልዩነት ጉዞ መተው፣  በኢትዮጵያዊነት አገራዊ ስሜት በአንድነት መቆም ያስፈልጋል። ስለሆነም ከልዩነቶቻችን ይልቅ በአንድነታችን ላይ አትኩረን በኅብረት መንቀሳቀስ አማራጭ አይኖረውም  አንድነት ኃይል ነው፤ ጥንካሬ ነው፤ የማድረግ ብቃት ማረጋገጫ ነው።

 ሰሞኑን ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ«እንተባበር» እና የ«አንድነት» ጥሪዎች ወቅታዊ ስለሆኑ አዎንታዊ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል። ለተግባራዊነታቸው አስተማማኝ መሠረት ለመጣል ደግሞ፣  «በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል» የሚሉ ወገኖችን ሁሉ አካትቶ፣ ለሚታሰበው አንድነት ጉዞ ፈር ቀዳጅ የሆነ የምክክር መድረክ ይዋል ይደር ሳይባል መፈጠር ይኖርበታል። ለዚህ ሂደት ውጤታማነት ተሞክረው ለግብ ካልበቁ የስምምነት ሙከራዎች ትምህርት ሊቀሰም ይገባል። እንዳለፉት ስምምነቶች ሁሉ የተፈረመባቸው ቀለም ሳይደርቅ ወደ ነበሩበት የመመለስ ሁኔታ እንዳይገጥም፣ የተስማሚ ወገኖችን ይሁንታ ያገኘ የመግባቢያ ሰነድ ሊዘጋጅ ይገባል። ይህ ሰነድ ወደ ዋናዎቹ የስምምነት ጉዳዮች ለመግባት ተስማሚዎቹ ወገኖች አምነውና ዐውቀው፣ የውዴታ ግዴታ የሚገቡበት አስገዳጅ እና ተፈጻሚነት ያለው ይዘት ሊኖረው ይገባል። ሰነዱ ከተዘጋጀ እና ሁሉም አንድነት ፈላጊዎች ተስማምተው ከፈረሙበት በኋላ፣ ለሕዝብ ይፋ ሆኖ ሂደቱን ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲከታተለው እና ተስማሚ ወገኖችም የተጠያቂነትና የኃላፊነት ስሜት እንዲያድርባቸው  ማድረግ ይገባል። 

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ እና በአስቸኳይ ቢወሰድ አደጋውን ሊያስወግድ ይችላል ብሎ ያመነበትን የመፍትሔ ኃሣብ በመጠቆም ከዚህ በላይ የሰፈረውን አቅርቧል። ለአፈጻጸም ይረዳ ዘንድም፣ ከዚህ በታች የተመለከቱት አስፈላጊ እርምጃዎች በውል እየተጤኑ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያሳስባል።

1.         ስምምነቱን የሚመራ ኮሚቴ ሊመሠርት የሚችል የጋራ መድረክ መፍጠር

(ሀ)        ይህ መድረክ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መጠራት ይኖርበታል። 

(ለ)        መድረኩ ኃላፊነት በወሰዱ ወይም በሚወስዱ ድርጅቶች አማካኝነት ይጠራል።  

(ሐ)       ለመድረኩ እያንዳንዱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ፣ የሲቪክ ና የሙያ ማኅበራት በአምስት በአምስት ሰዎች ይወከላሉ፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኃይማኖት ድርጅቶች እያንዳንዳቸው በአንድ  ሰው የሚወከሉ ይሆናል።

(መ)       የመድረኩ ኃላፊነትም ለቀረበው የአንድነት ጥሪ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስችል አስማሚ ኮሚቴ መመሥረት እና አስማሚ ኮሚቴው ሊያተኩርባቸው በሚገባቸው የመግባቢያ ሰነዶች ይዘት ላይ ለመወሰን ይሆናል።

2          የአስማሚ ኮሚቴ አባሎች አመራረጥ

(ሀ)        በተዘጋጀው መድረክ በተገኙ አባሎች አማካኝነት በሚደረግ ውይይት ቁጥራቸው ከአሥራ አምስት እስከ ሃያ አንድ የሚሆኑ የኮሚቴ አባሎችን የያዘ ኮሚቴ መመሥረት ።  

(ለ)        የኮሚቴ አባላቱም ከሚከተሉት አንዱን ወይም ከሁሉም በማቀላቀል መመሥረት ይቻላል። 

3        የኮሚቴው አባላት ይዘት

(ሀ)        በሁሉም ተስማሚዎች አመኔታና አክብሮት የተቸራቸው ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች፣ 

(ለ)        በኢትዮጵያ ካሉት ነገዶች እና ጎሣዎች ከአምስት መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው የነገድ እና የጎሳ ተወካዮች፤

(ሐ)       ከኢትዮጵያ ታላላቅ ኃይማኖቶች ታዋቂ አባቶች ፤፤ 

 

4        የቴክኒክ የሥራ ቡድን ስለ ማቋቋም

(ሀ)        ለሚቋቋመው አስማሚ ኮሚቴ ሥራ መቃናት እና መቀላጠፍ የሚያግዙ በሁሉም ተስማሚ ወገኖች ይሁንታ ያገኙ፣ ወይም ከተስማሚ ወገኖች ተመጣጣኝ ውክልና ያላቸው የቴክኒክ የሥራ ቡድኖች መቋቋም አለባቸው።

(ለ)        የእነዚህ የሥራ ቡድኖች ተግባርና ኃላፊነታነታው በግልጽ የሰፈረ፣ ከአስማሚ ኮሚቴው ጋር ሊኖራቸው የሚችለው የሥራ ግንኙነት በማያሻማ መንገድ የተገለጸ መሆን ይኖርበታል። 

5          የኮሚቴው የሥራ ጊዜ እና የአፈጻጸም ጉዳዮች

(ሀ)        አስማሚ ኮሚቴው በሥራ ላይ የሚቆይበት ጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል። 

(ለ)        ኮሚቴው ዝርዝር የሥራ አፈጻጸም መመሪያዎችን ያዘጋጃል።

(ሐ)       ኮሚቴው የተሳታፊ ድርጅቶችን እና ና ግለሰቦችን አመራረጥ መስፈርት ያዘጋጃል።

(መ)       የስምምነቱ ሥነሥርዓት የሚገዛበት ደንብ እና  የአሠራር ቅደም ተከተል መመሪያዎች በኮሚቴው ይዘጋጃሉ።     

6          ትኩረት የሚጠይቁ ሌሎች ጉዳዮች

(ሀ)        ተስማሚዎቹ ወገኖች ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ማከናወን ያለባቸውን አንኳር አገራዊ ጉዳዮችን ለይቶ ማስቀመጥ፣

(ለ)        ከወያኔ ውድቀት በኋላ ኢትዮጵያ ልትከተለው ስለሚገባ የአስተዳደር እና የፖለቲካ ሥርዓት በአገር አንድነት ከተስማሙ ወገኖች  የቀረቡ ኃሣቦችን  ማቀናጀት፤

(ሐ)       ስምምነቱ የሚካሄድበት አገር፣ ከተማ እና ጊዜ መወሰን፤

(መ)       በመግባቢያ ሰነዱ የተስማሙ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችን፣ ስብስቦችን እና ማኅበሮችን ማንነትና የሚወክሏቸውን ሰዎች ማንነት ለይቶ መመዝገብ፤

(ሠ)       የስምምነቱ ሂደት እና ውጤት የሚገለጽባቸውን ቋንቋዎች መወሰን፤

(ረ)        ስምምነቱ በሚገለጽባቸው ቋንቋዎች መካከል የትርጉም ልዩነት ቢከሰት፣ በዋናነት የሚወሰደውን ቋንቋ ለይቶ መወሰን፤

7            ተጨማሪ ማሳሰቢያ

(ሀ)        አንድነት የሚፈጥሩ ቡድኖች የሚለያዩባቸው አቋሞች ቢኖሯቸውም የአገር አንድነትን በተመለከተ የሚጋሯቸው እሴቶች ምን እንደሆኑ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።

(ለ)        በመስማሚያው ወይም መግባቢያው ሰነዱ እና በአሠራሩም ቅደም ተከተል ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ ወደ ዋናው ጉዳይ ሲገባ፣ ስምምነቱ በቀና እና በታሰበው ጊዜ እንዲከናወን፣ ተሳታፊዎች «አሉኝ» የሚሏቸውን የአቋም ጥያቄዎች በክብደታቸው ቅደም ተከተል መሠረት አስማሚው ኮሚቴው በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ማድረግ ሥራን ያቀላጥፋል። ከዚህ በተጨማሪ ስምምነቱም በእነዚያ ነጥቦች ዙሪያ ብቻ እንዲያተኩር መወሰኑ በውይይቱ ወቅት ሰጥቶ ለመቀበልም ሆነ፣ «ይህ ካልሆነ» ብሎ አቋምን አጠንክሮ ለመጓዝ ይረዳል።

እነዚህና መሰል ጉዳዮችን የሚያካትት ሰነድ መዘጋጀት ለሚታሰበው አንድነትና የትብብር ጥሪ ውጤታማነት ያገለግላል ብሎ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል።

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop