June 6, 2013
11 mins read

ከልማት መጋረጃው በስተጀርባ

‘To encourage world leaders to become part of a vast network, that promotes our commercial interests.

In the end, those leaders become ensnared in a web of debt that ensures their loyalty. We can draw on them whenever we desire to satisfy our political, economic, or military needs. In turn, they bolster their political positions by bringing industrial parks, power plants, and airports to their people. The owners of engineering /construction companies become fabulously wealthy.

(የእኛን የንግድ ጥቅሞችን የሚያስጠብቀው የሰፊው መረብ አካል እንዲሆኑ የአለም መሪዎችን ማበረታታት።

በመጨረሻም እነዚህ መሪዎች በዕዳ ስለሚተበተቡ ለእኛ ”ታማኝ” /ታዛዥ/ ይሆናሉ።የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ ወይም የወታደራዊ ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት እንዳስፈላጊነቱ እንጠቀምባቸዋለን።በተቃራኒው ለህዝባቸው ኢንደስትሪዎችን፣የኃይል ማመንጫዎችንና የአውሮፕላን ጣቢያዎችን በማሰራታቸው የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ያጠናክሩበታል።የእኛ የምህንድስናና የግንባታ ተቋማት ባለቤቶችም እጅግ ሀብታም ይሆናሉ።”)

/Excerpted from the Confession of an Economic Hitman/

የዮም ኪፑር /Yom Kippur/ ጦርነት በእስራኤልና በአረቦች መካከል ሲካሄድ የሪቻርድ ኒክሰን አስተዳደር ለእስራኤል ወገንተኝነቱን ከማሣየቱም በላይ የ2 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ማድረጉን ተከትሎ ነዳጅ አምራች የአረብ ሀገራት በነዳጅ ዋጋና አቅርቦት ላይ ማዕቀብ በማድረጋቸው የአሜሪካ ኢኮኖሚ ለወራት የዘለቀ መናጋት ገጥሞት ነበር።እናም በወቅቱ የነበሩ ፖሊሲ አውጪዎች ከእንደዚህ አይነት ቀውስ በዘላቂነት ራሳቸውን ለመከላከል ያዘጋጁት መንገድ ሀገራትን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ጥገኛ ማድረግ ሲሆን ይህንንም ተፈፃሚ የሚያደርጉ ”ኢኮኖሚክ ሂትማን” በመባል የሚታወቁ ሃይሎችን አሰማርተው በርካታ ሀገራትን ከማይወጡት ዕዳ ውስጥ እንዲዘፈቁ በማድረግ ያለምንም መገዳደር ለአበዳሪ ሀገራት ተንበርካኪ እና የሃብት ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ ችለዋል።

በተመሳሳይ የኢኮኖሚ አቅሟ እየፈረጠመ የመጣው ቻይና ኤክሲም ባንክ ኦፍ ቻይና /Export-Import Bank of China/ በሚባለው እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋሞቿ በኩል የበርካታ አፍሪካ ሀገራትን ጓዳ ባዶ ያስቀረች ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በልማት ስም በወያኔ ፊታውራሪነት የዚህ ዘረፋ ግንባር ቀደም ሰላባ ሆናለች፤ እየሆነችም ነው።

የኢትዮጵያ እና የቻይና የግንኙነት መስመር ባለሁለት እርከን (Double Standard) ሲሆን ይኸውም፦

1ኛ. የቻይናና የኢትዮጵያ ህዝብ ግንኙነት፤

2ኛ. የቻይናና የወያኔ ግንኙነት ሲሆን የግንኙነት ዑደቱን አጠቃላይ ገፅታ ማየት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት በቀላሉ እንድንገነዘብ ይረዳናል።

አንድ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት የቻይና መንግስት በከፍተኛ ወለድና በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ያበድራል። ከብድሩ መፈቀድ ጎን ለጎን ፕሮጀክቱን በዋናነት እንዲሰራ ያለጨረታ ለቻይና ኩባንያ ይሰጣል።ይህ ማለት አብዛኛው ብር እዚያው ቻይና የሚቀር ሲሆን በንዑስ ኮንትራት /Sub-Contract/ ለወያኔ ድርጅቶች ከፕሮጀክቱ ውስጥ ትናንሽ ሥራዎች ይሰጣቸዋል።በዚህ ሳይወሰን ፕሮጀክቱን በዋናነት የያዘው የቻይና ካምፓኒ የሰው ኃይል ሳይቀር ከቻይና የሚያመጣ በመሆኑ ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል የሚፈጠርለት የሥራ ዕድል ከጥበቃ እና ከሹፍርና የዘለለ አይሆንም ያውም በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች ብቻ። በፕሮጀክቱ መጠናቀቅና ርክክብ ወቅት የጥራት ጉዳይ እንዳይነሳ አስቀድመው ከላይ ያሉትን የወያኔ መሪዎች በሙስና የተበተቧቸው በመሆኑ ከደረጃ በታች የተገነቡ መንገዶች፣ድልድዮችና የኃይል ማመንጫዎች ባለቤት መሆን ችለናል።በዚህ የተዛነፈ የግንኙነት መስመር ትልቁን የተጠቃሚነት ድርሻ የቻይና የፋይናንስና የግንባታ ተቋማት የሚይዙ ሲሆን የወያኔ ተቋማት /ለምሳሌ ሱር ኮንስትራክሽን፣መሰቦ ሲሚንቶ ……..ወዘተ የመሳሰሉት/ በሁለተኛ ደረጃ ተጠቃሚነት ላይ ይገኛሉ። በሦስተኛ ደረጃ ተጠቃሚነት የሚገኙት ባንዳዎቹ የህወሃት ባለሥልጣናት ሲሆኑ የጥራት ጉዳይ እንዳይነሣ እንዲሁም ገና ከጅማሬው እንደዚህ አይነት ዕዳው የበዛ የንግድ ግንኙነት ምንዳ ምክንያት ሦስተኛ ደረጃ ተጠቃሚዎች ናቸው።

በተቃራኒው የኢትዮጵያ ህዝብ ትውልድን ተሻግሮ በሚዘልቅ ትልቅ ሀገራዊ ዕዳ /National Debt/ ውስጥ የተዘፈቀ ሲሆን ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ልክ እንደቆላ ፍየል ዝናብ ሲያይ ”አስጠልሉኝ” የሚል የአስፋልት መንገድ ባለቤት ሆናለች።በእርግጥም ዛሬ በሀገራችን የሚገኙ አውራ ጎዳናዎች፣ቻይና ሰራሾቹ የአዲስ አበባ ጎዳናዎችና ድልድዮች ሁለት ክረምት መሻገር ተስኗቸው ከተገነቡበት ዋጋ በላይ ለጥገና በርካታ ወጪ እየወጣባቸው ይገኛል።

”የአበዳሪ እጅ ከላይ ነው” እንደሚባለው ዛሬ ”በዕዳ እንቀንስላችኋለን” ስም የጥራት ደረጃቸው ለጤንነት አስጊ የሆኑ የቻይና የፋብሪካ ምርቶች መዳረሻ ኢትዮጵያ ከሆነች ሰነባብቷል።

በሌላ በኩል የወያኔ መንግስት እነዚህን የመሳሰሉ ስንኩል ፕሮጀክቶችን የልማት ስኬት በማስመሰል በፕሮፓጋንዳ ማሽኖቹ ማለትም ኢ.ቲቪ፣ሬድዮ ፋና እና የኢትዮጵያ ሬድዮ በኩል በማሳየትና በማስነገር ራሱን ”ልማታዊ” ለማስመሰል በመጣሩ ”’ኢህአዴግ አምባገነን ቢሆንም ልማትን አምጥቷል” የሚሉ ጭፍን ግን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ”ምስክሮችን” እና ደጋፊዎችን ማፍራት ችሏል።ነገር ግን በሀገራችን ለሙ የተባሉት ፕሮጀክቶች፦

1ኛ. ከወጣባቸው ወጪ አንፃር ጥራታቸው ከደረጃ በታች እጅግ የወረደ መሆኑ፤

2ኛ. የተባሉት የ”ልማት” ሥራዎች ምን ያህል የሥራ ዕድል እና የቀጥታ ተጠቃሚነትን ለኢትዮጵያውያን ፈጠሩ?

3ኛ. የአበዳሪ እና ተበዳሪ ውሎች ለሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሳይቀር ምስጢራዊ የሆኑ ይልቁንም በጣት በሚቆጠሩ የህወሃት ባለሥልጣናት መዳፍ ስር ብቻ የሚዘወሩ መሆናቸውና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተን ስንፈትሸው በእርግጥም ሀገራችንና ህዝቦቿ እየለሙ ሳይሆን እየተበዘበዙ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

ዛሬ ዜጎቻችን በሀገራቸው ባዕድ ሆነው በምድራቸው ላይ በሚደረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ባይተዋር እንዲሆኑ ከመደረጋቸውም ባሻገር የሀገራችን የተፈጥሮ ሀብት በጥቂቶች እጅ እየተበዘበዘ የቻይናን ኢንደስትሪዎች እየመገበ ይገኛል። ለሀገራችንና ህዝቦቿ ከተረፋቸው ትውልድን ተሻጋሪ ሀገራዊ ዕዳ በተጨማሪ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ጡጫ ተደፍጥጠው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ደረጃ በወያኔ ቅኝ አገዛዝ ሥር ይገኛሉ።

በመሆኑም ሀገራችንና ህዝቦቿ ለህወሃትና ጋሻጃግሬዎቹ የሀብት ምንጭ የሆነበትን የብዝበዛ ሥርዓት እንዲሁም በብረት ኃይል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነውን የቅኝ አገዛዝ ማጋለጥ፣መቃወም እንዲሁም ይህን ሥርዓት ለማስወገድ በሚደረግ ትግል ውስጥ በንቃት መሳተፍ የዜግነትና የሞራል ግዴታችን ነው።

 

By: Beyene Mesfin.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop