አስቂኝ ዜና! June 20, 2014 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email በናዕዴር ዓዴት (አክሱም ዙርያ) “ሰመማ” ተብሎ በሚጠራ የገጠር ከተማ የሚያስተምሩ መምህራን “የዓረና በራሪ ወረቀት ተቀብላቹ አንብባችኋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ወረቀት መቀበል ይሁን ማንበብ መብታችን ነው ብለው ቢከራከሩም ያከባቢው አስተዳዳሪዎች ግን ማስፈራራትን ተያይዘውታል። የዓረና ወረቀት አንብባችኋል ተብለው ከተከሰሱ መምህራን አስራ ስምንቱ (18) “እንዳውም ዓረና ነን። ለነፃነታችን እንታገላለን!” ብለው የዓረና አባላት ለመሆን ትናንት ፎርም መሙላታቸው ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ በስልክ ገልፆልኛል። የናዕዴር ወላጆች ልጆጃቹ ወደ ዴምህት ልካችኋል እየተባሉ ብዙ ግፍ እንደሚፈፀምባቸው ይታወቃል። አዎ! እንደነዚህ ቆራጥ መምህራንም አሉ። ዓረና ናችሁ ሲባሉ ዓረናን የሚቀበሉ። Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Previous Story የትግራይን መስቀል ስለመሸከም (ተመስገን ደሳለኝ) Next Story Health: በኢትዮጵያ ቪያግራ ገበያ ደርቷል፤ * የቪያግራ ተጠቃሚዎች ሊያውቁት የሚገቡ እውነታዎችና ጥንቃቄዎች