December 5, 2024
6 mins read

“በህይወቴ እንደዚህ አይነት ጭካኔ አይቼ አላውቅም” አማራ ክልል የነበራትን ቆይታ ፋኖን በማድነቅ ያሰፈረችው የኒውዮርክ ታይምሷ ዘጋቢ

መስጋናው ዕንዳልክ X

unnamed 31የ Moonless and Starless sky (የጨረቃና ክዋክብት አልባ ሰማይ) መፅሀፍ ደራሲ፣ በበርካታው የዓለም ክፍል እየተዘዋወረች የጦርነትና ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በሰራችበት ተግባሯ ”the best travel writter award” አሸናፊዋ፣ የኒውዮርክ ታይምሷ ሰው የፋኖ የተጋድሎ ውሎና የአማራ ህዝብ ከአገዛዙ ሀይል ጋር እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተመልክታዋለች። የኒውዮርክ ታይምሷ አሌክሲስ ኦኪኦዎ ቀልቧን ስለሳቡት፣ ልቧን ስለገዙት ፋኖዎች ጥፋት ስለታወጀበት የአማራ ህዝብ በስርዓቱ ታፍሰው በማይገባና በማያገባቸው ጉዳይ እየገቡ ስለሚያልቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካሰፈረችው ሀሳብ እነሆ በጥቂቱ።

”ከላሊበላ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ፋኖ ኬላ ላይ አስቆመንና ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠን። እንድናወራቸው እንደምፈልግ በነገርናቸው ወቅት ዩኒፎርም የለበሱ የፋኖ አባላት አስፖልት ዳር በሚገኝ ሆቴል ይዘውን ሄደው በረንዳ ላይ ቁጭ አልን፡፡” እያለች የአይን ምስክርነት ትንተናዋን የምትቀጥለው ጋዜጠኛዋ።

የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በፋኖ ኬላ ላይ ለፍተሻ በሚቆምበት ወቅት ባስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ከፋኖ አባላት ጋር ፎቶ ለመነሳት ይጋፉ ነበር፤ መሳርያም ይዘው ፎቶ ለመነሳት ይጠይቁ እንደነበር ጋዜጠኛዋ ህዝቡ ለፋኖ ያለውን ፍቅር በግልፅ የተመለከተችበትን ሁነት አስፍራዋለች።

ብዙዎቹ የፋኖ ተዋጊዎች ወጣቶች እንደሆኑ የምትናገረው ጋዜጠኛዋ ፈንታ እና ላስታ የሚባሉ ሁለት የ18 እና የ19 ዓመት ሴት የፋኖ ተዋጊዎችን እንዳገኘችና አማራና በሰላም እንዳይኖር ስለተደረገ ወደ ፋኖ እንደተቀላቀሉ ትናገራለች፡፡

Fano

ስለ ውጊያ ውሎዎቻቸው ሲገልፅም “ የጠላት ሰራዊቶች በብዛት ይሞታሉ ፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ ጦርነት ስንገጥም የዕውር ድንብር ነው የሚተኩሱት ፣ በቁጥር ብዙ ቢሆኑም እግሬ አውጪኝ ብለው ይሮጣሉ እንጂ ቆመው አይዋጉንም። በጣም ነው የሚፈሩን ፤ በዛው በመከላከያ ውስጥ ያሉት አማራዎች እንደውም በጭራሽ ሊዋጉን አይፈልጉም” ስትል መግለጧን ጠቅሳ የአገዛዙን ሀይል ወታደሮች ፍርሀት ሽንፈትና ውርደት በኒውዮርክ ጋዜጣ ላይ በዝርዝር አስቀምጣዋለች።

በላሊበላ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ፋኖ መሪ ዋኘው ሀምሳ አመቱ ሲሆን ፋኖን ከመቀላቀሉ በፊት ፖሊስ የነበረ ከዛም በኃላ ትራንስፖርት ላይና ኮንስትራክሽን ላይ ይሰራ የነበር ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም የሆነው ሰው የመንግስት ሀይሎች በአማራ ሕዝብ። ላይ የሚፈጽሙትን ድርጊት ተመልክቶና የአማራን የህልውና ስጋት ተመልክቶ ፋኖን መቀላቀሉን ያነሳና ባደረገችለት ቃለ ምልልስም ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት መከላከያ ብሎ የሚያመጣቸውን ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያስማረከና እያስገደለ መሆኑን ፅፋለች።

ጋዜጠኛዋ ከዋኘው ቃለምልልስ በወሰደችውና ባሰፈረችው ሃሳብ በሚካሄደው ጦርነት የአማራ ተወላጅ እናቶችና ሴት ልጆች ይደፈራሉ፣ በከባድ መሳሪያ ይደበደባሉ፤ የፋኖ ትግልም ለመገንጠል ሳይሆን ስርዓታዊና መዋቅራዊ በደልና ጥቃቶች እየተፈፀሙ ህልውናውም አደጋ ላይ በመውደቁ ላለመጥፋት የሚደረግ የህልውና ትግል ነው ስትል አስፍራዋለች።

ጋዜጠኛዋ ”ለታ” የተባለ የመከላከያ ሰራዊት የነበረና በፋኖዎች የተማረከን የኦሮሞ ተወላጅ ወጣት አናግራ ባሰፈረችው ፅሁፍ ”ከአንድ ዓመት ተኩል በላቀ ጊዜ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና መጠጥ እጅግ አሰልቺና አድካሚም በሆነ ሂደት ውስጥ በመቆየቴ ለፋኖዎች እጅ ብሰጥ ምንም እንደማልሆን አውቃለሁና እጄን ሰጠሁ። ፋኖዎችም ተቀብለው ወታደራዊ የምርኮኞች መብቴን ጠብቀው ይዘውኛል። በዚህ በምርኮ ሁነት ውስጥ እያለሁም ለቤተሰቦቼም ገንዘብ እልካለሁ” አለኝ ስትል አስፍራለች። ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ የጠየቀችው ጋዜጠኛዋ ምርኮኛው የኦሮሞ ተወላጁ የመከላከያ አባል መሳሪያውን ሸጦ እንደሆነ ሲያስረዳኝም እሱን ጨምሮ ፋኖዎችም ሁሉ በሳቅ ታጀቡ ስትልም አስፍራለች።

 

Civil War Never Ended in Ethiopia: I Have Never Seen this Kind of Cruelty in My Life’

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop