October 2, 2024
15 mins read

ጦርነቱ አማራ ክልል ብቻ ከመሰለን ተሳስተናል!

ይነጋል በላቸው

የኦሮሙማ መንጋ ኢትዮጵያን በአጠቃላይ፣ አማራን ደግሞ በተለይ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የአራት ኪሎን ቤተ መንግሥት ከተቆጣጠረ ስድስተኛውን ዓመት አጠናቆ የሰባተኛው እኩሌታ ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ የጥፋት ጉዞው ብዙ ነገር ተምረናል፡፡ ዋናውና ትልቁ ትምህርት – ለማልማት ከሚወስደው ጊዜ ለማጥፋት ወይም ለማውደም የሚወስደው ጊዜ እጅግ አጭር መሆኑን ነው፡፡ በስድስት ዓመታት ተኩል አማራና ኢትዮጵያ ከየት ወዴት እንደተሻገሩ ተመልክተናል – ዕድሜ ለወፈፌው ጭቅላ አሻግሬ፡፡ (ይህ ልጅ የበቃኝ እኮ ምርኮኛ አሥር አለቃን ፊልድ ማርሻል ሲል ነው – ሊያውም ከመቀሌ ሸኖ ድረስ ስለሮጠ፡፡)

“ለሰው ጉድጓድ አትቆፍር – ከቆፈርክም አታርቀው፤ ቀድሞ የሚገባበትን አታውቀውምና” የሚለውን ነባር ብሂል መረዳት የተሣናቸው የአእምሮ ድኩማኑ ሕወሓቶች በአባታቸው በአቶ ስብሃት ነጋ በኩል ለኢትዮጵያ ቃል የገቡላትን ቃል – እጠቅሳለሁ – “እኛ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻልን ሥልጣኑን ለኦሮሞ አስረክበን ወደ ትግራይ እንገባለን”  እውን መሆን ማረጋገጥ ከጀመርን ዓመታትን አስቆጠርን፡፡ ግን እነሱም የዘሩትን አጨዱና ብዙ የጮህንበት የሰላምና የፍቅር አማራጭ ገደል ገብቶ ሀገራችን ለማንም ሳትሆን በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ልትገኝ ቻለች፡፡ በጥላቻና በበቀል ተኮትኩቶ ያደገው የትግራይ ወያኔና የኦሮሞ ኦነግ/ኦህዲድ ተራ በተራ ኢትዮጵያን አነደዷት፡፡ በነዚህ የጅል ብልጦች ምክንያት ሁሉም ነገር ያላት ሀገራችን ሁሉንም እንድታጣና ዜጎቿ ተንከራታች እንዲሆኑ ተፈረደባት፡፡ የዘረኝነትና የጎጠኝነት፣ የድንቁርናና የድህነት፣ የሙስናና የንቅዘት፣ የስደትና የጦርነት፣ የክፋትና የምቀኝነት፣ የአጋንንታዊ ሥርዓተ መንግሥትና የሊቀ ሣጥናኤል ንግሥና ምሣሌና የልጅ ማስፈራሪያ ጭራቅ ሆና አረፈችው፡፡

ትግራይ ልታንሰራራ በሚያዳግታት የውድቀት ደረጃ ላይ ትገኛለች፤ ነገሩ “ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ” ቢሆንም ያሣዝናል፡፡ አሁንም ድረስ ዘረኞች ልጆቿ ወጉ አይቅርብን ብለው በልማት ሥራ ከመጠመድ ይልቅ ልክ እንደዱሮው ለወራት በሚዘልቁ ስብሰባዎች ተጠምደው አሉ፡፡ አለመለከፍ ነው፡፡ ሠላሣ ክልል ተፈጥሮ፣ ሠላሣ ምክር ቤት ተዋቅሮ፣ ሠላሣ ቦታ ልዩ ኃይልና የክልል ፖሊስ ተመድቦ … ለዕድገትና ለልማት መዋል የነበረበት ወጣት ኃይልና ውሱን ሀብት እርስ በርስ ለመዋጋት ሲውል እንደማየት መፈጠርን የሚያስጠላ ነገር የለም፡፡ ዐርባና ሃምሣ ሚሊዮን ሕዝብ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቶ በጠኔ እየተንጠራወዘ የሀገር ሀብት ተሟጦ በትሪሊዮን ለሚገመት ቅንጡ ቤተ መንግሥትና ለገዛ ወገን መግደያ ጦርነት ሲውል እንደማየት ሰው መሆንን የሚያስጠላ ክስተት የለም፡፡

ብዙ የአዲስ አበባ ሰው አማራው ላይ ብቻ ይመስለዋል ጦርነት የታወጀው፡፡ የአቢይ ሰይጣናዊ የኢሉሚናቲ መንግሥት አማራን ብቻ ለማጥፋት አይደለም ጦርነቱን በአማራ ክልል እያካሄደ የሚገኘው፡፡ አማራን ለመጨረስ በወለጋም፣ በኢሉባቦርም፣ በሐረርም፣ በአዋሣና ሻሸመኔም ካካሄደው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ቀጥሎ አማራ ክልል በሚባለው ሥፍራ ባለፈው ዓመት በግልጽ ጄኖሣይድ ማወጁ በይፋ የሚታወቅ ሆኖ በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ በተለይ የሚያራምደው ዘር ተኮር የቤት ፈረሳና ዜጎችን ሜዳ የማስቀረት ኦሮሙማዊ ዕኩይ ተግባር ብዙው ዜጋ የተረዳው አይመስልም፡፡

በመሠረቱ ጦርነት ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ዜጎችን ከነባር ይዞታቸው ማፈናቀልና በዚያም ሰበብ ራሣቸውን እንዲያጠፉና ጨርቃቸውን ጥለው እንዲያብዱ ማድረግ ትልቅ የጦርነት ሥልት ነው፡፡ በዚህ ኦሮሙማዊ የዘር ማጽዳት “ጥበብ” እጅግ ብዙ አማሮች ከአዲስ አበባና አካባቢዋ እየተወገዱ ነው፡፡ በኮሪደር ልማት ሰበብ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ አማሮች ከአዲስ አበባ እምብርት ተባርረዋል፤ መግቢያም አጥተው አብደዋል ወይም በገመድና በመሳሰሉ ራስን የማጥፊያ ዘዴዎች ወደዚያኛው ዓለም ሄደዋል – ሁለት ኪሣራ፡፡ አዲስ አበባ ቤት አለኝ ማለት የሚችል በግልጽ ቋንቋ  ለመናገር ኦሮሞ የሆነና ኦሮሞነቱንም ማስመስከር የሚችል ነው፡፡ ማንኛውም አማራ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ብቻ ሣይሆን አዲስ አበባ ውስጥ ለመኖርም የኦሮሙማ ቡራኬና ፈቃድ ያስፈልገዋል፡፡ ደግነቱ ያኛው እንዳለፈ ሁሉ ይህም በቅርቡ ያልፋል፡፡ ችግሩ ነገን ከትናንት የማያገናዝቡ ደናቁርት አራት ኪሎን መቆጣጠራቸው ነው፡፡

ሌላውና ትልቁ ጦርነት የኑሮ ውድነቱን በብርሃን ፍጥነት እንደኳስ ሽቅብ ማጓን ነው፡፡ የዛሬ ሰባት ዓመት በኪሎ አምስት ብር የገዛኸው ቀይ ሽንኩርት አሁን 170 ብር ብትባል ለውጥ የሚባል በማያውቃት የሀበሻ መጽናኛ “ይብስ አታምጣ” ብለህ ከመግዛት በቀር ሌላ ምርጫ የለህም፡፡ ጤፍ አይነሣ፡፡ ሥጋም አይታሰብ፡፡ አትክልት በሆድ ይፍጀው ይቅር፡፡ ንዑስ ከበርቴ ይባል የነበረው የመንግሥት ሠራተኛ ዛሬ በቀን አንዲት ዳቦ በሻይ እልፍ ሲልም አንዲት የመንገድ ዳር ሽሮ ካገኘ ብዙ ሰው የሚቀናበት ባለፀጋ ነው፡፡ እንደኢትዮጵያዊ ግፈኛ መንግሥትንና አምባገነን መሪን የሚሸከም በሌላ ሀገር ካለ አግራሞቴ መለኪያ አይኖረውም፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ የጦርነቱ አካል መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

የመንግሥት የአገልግሎትና የቀረጥ/የግብር ክፍያዎች ሰማየ ሰማያትን አልፈዋል፡፡ በአንድ ምሰሶ በዘጠና ብር የገባልህና በወር ብር 15 ትከፍልበት የነበረው የመብራት ዋጋ በየደረጃው ከአለቃ እስከምንዝር ሠራተኛ የምትወታትፈው መቁሽሽ ሳይጨመር ዛሬ በስምንት ሽህ ብር ገደማ አስገብተህ በወር ለአነስተኛ የአንድ ቤተሰብ ፍጆታ ሰባት ሽህ ብር ድረስ ልትጠየቅ ትችላለህ፡፡ እንደምንሰማው ለመንጃ ፈቃድ ዕድሣት፣ ለቴሌ፣ ለንግድ ባንክ፣ ለሰነዶች ማረጋገጫ፣ ለመታወቂያ ማደሻና ማውጫ … ምን አለፋህ ለማንኛውም አገልግሎትና አቅርቦት የሚጠበቅብህ ክፍያ እጅግ ንሯል፡፡ ነገሩ ሁሉ “የበላችው ያስገሳታል፤ በላይ በላዩ ያጎርሳታል” እንዲሉ ነው፡፡ ይህ ነገር ሆን ተብሎም ይመስላል፡፡ “ምን ያመጣሉ?” ከሚል ዕብሪትና የሀገርና ሕዝብ ጥላቻቸውን ለመወጣት፡፡ አማራንና የኢትዮጵያን የቀድሞ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እንዴት እንደሚጠሉ ደግሞ አትጠይቁኝ፡፡ እነዚህን በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ ሲያዩ ሊያስታውካቸው ይደርሳል፤ ሊያስታውኩም ይችላሉ አላውቅም፡፡ እንዴትና በማንስ ቢረገሙ ይሆን?

ይህ ፈርጀ ብዙ ጦርነት በቅርብ እንደሚጠናቀቅ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳች መንፈሣዊ ኃይል ሹክ ይለኛል፡፡ እነዚህ ደደቦችና የአጋንንቱ ዓለም አጋፋሪዎች የሚሠሩት ሁሉ ሲታይ ውኃ ውስጥ እየሰመጠ ያለ ሰው የሚያድነው መስሎት ውኃው ላይ የሚንሳፈፍን ገለባ ወይም አረፋ እንደሚጨብጥ ዓይነት ነው፡፡ ሥራቸው ሁሉ የመቃብራቸውን መቃረብ የሚጠቁም ከመሆኑም ባሻገር ብዙዎቹ የጅል ተግባሮቻቸው የሚያሳዩን ሥርዓተ ቀብራቸው ራሱ ቅጥ ያለውና የማይታዘንላቸው መሆኑን ነው፡፡

በመጨረሻም ለነጌትነት አዳነና ለመንገሻ ማንትስ የሚባሉ የብአዴን ኮንዶማውያን የትሮይ ፈረሶች  የምለው አለኝ፡፡ ብአዴናውያን የብልግና “ባለሥልጣናት” በጣም እየመሸባቸው ነው፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም በሚባል ደረጃ ልክ እንደጌቶቻቸው ማይማን ደናቁርት ናቸው – አማራን የሚያሰድቡ ጋብቻ ከልክል ማፈሪያዎች፡፡ በአማራ ስም ኦሮምያ የምትባል የህልምና የቅዠት ሀገር በምሥራቅ አፍሪቃ ሊያውጅ የተቃረበውን ብልጽግና የተባለ ቡድን በመደገፍ የአማራን ዕልቂት የምታራምዱ ብአዴኖችና ሆዳም ባንዳዎች በቶሎ ወደየኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ የፋኖን ትግል ባታግዙ እንኳን እጃችሁንና አንደበታችሁን በመሰብሰብ ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን አድኑ፡፡ የእስካሁኑ ጥፋታችሁ ይበቃል፡፡ በኦሮሙማ እንደቆረባችሁ የመቀጠል መብታችሁ ግን የተጠበቀ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በዳንዴል ክብረት ብዔልዘቡላዊ ትዕቢትና በአቢይ አህመድ የ666 ፊታውራሪነት የሚቀለበስ አይደለም፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ቢሆኑም የዘረኝነትንና የጎጠኝነትን ቋንቋን ማዕከል ያደረገ የሚከረፋ ጎራ ተፀይፈው ከአማራ የነፃነት ትግል ጎን የተሰለፉ ትግሬዎችና ኦሮሞዎች፣ የውጪውና የሀገር ውስጡ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማ የወለዳቸውን ሸሮችና የተንኮል ሤራዎች ተረድተው እየተደረገ ያለውን የነጻነት ትግል ከአማራዎችም በበለጠ ሲደግፉ እያየን አማራ ሆናችሁ የአማራን ዕልቂት ማስተባበራችሁ ለእናንተም ብቻ ሣይሆን ለቀጣይ ሰባት ትውልዳችሁ የምታተርፉት የሀፍረት ማቅና ሸማ ከሞታችሁና አሟሟታችሁም በላይ የከፋ መሆኑን ልትገገነዘቡ ይገባል፡፡ የታወረው ዐይነ ኅሊናችሁ ይብራ፤ የተደፈነው ዕዝነ ልቦናችሁም ይከፈት፡፡ በየ30 ደቂቃ ለሚሸና መጠጥና በየ4 ሰዓት ዕዳሪ ለሚሆን እህል ብላችሁ ታሪክ ይቅር የማይለውን ስህተት ከመሥራት ተቆጠቡ፡፡ በእናንተ ምክንያት ነፃነት ልትዘገይ ትችል ይሆናል እንጂ አትቀርም፡፡ እሳት እየመጣባችሁ ነው፡፡ እናንተ ግን በትዕቢት ስለተወጠራችሁ እሳቱ ሊታያችሁ አይችልም፡፡ …

 

3 Comments

  1. ሰላም ይልቃል ልክ ነህ የአጋንንት አለቃን ስብሃት ነጋን ፈትቶ ጠግበው ያልበሉትን አቶ ታድዮስ ታንቱን ያስራል ስብሃት ነጋ እንደዛ ተበለሻሽቶ ከዋሻ ያወጡትን የመከላከያ ልጆች ፈሪዎች ናቸው የኤርትራ ወታደር ነው ጀግና ብሎ በድፍረት ቃለ መጠይቅ ይሰጣል። እንግዲህ ትግሬዎች ደግሞ የኤርትራ ወታደር በምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰቆቃ አድርሶብናል ይላሉ የተወሰደባቸውን የኢሮብ መሬት ግን አንድ ቀን ሲያነሱት አትሰማም መርቀውለታል ማለት ነው። የሚይስቀው የራሳቸውን ኢሮብ፤ዛላንበሳ…. አስረክበው የራሳቸው ያልሆነውን መውሰድ ይፈልጋሉ።
    ነብሱን ይማረው ስዩም መስፍን የወሰነው ውሳኔ በስጋ አእምሮው ስለሆነ ብየ ነው ። በአልጄርሱ ስምምነት ያልጠበቅነው ሁሉ ተሰጠን ብሎ ትግሬን አስጨብጭቦ ድፍን ጦብያን አስፈንጥዞ ዶሴው ሲፈትሽ ጉዳዩ ሌላ ሁኖ ተገኘ። እነ መስከረም አበራ ስለጻፉ እነ ክርስቲያን ታደለ በተሰጣቸው መብት በመጠቀማቸው ዘብጥያ ሲወርዱ ሲደበደቡ ጻድቃን 700 ሚሊዮን ብር በአብይ እውቅና አጥቁሮ መውጣቱን አንዳርጋቸው ባለፈው ጽፎ አይቻለሁ አቦይ ስብሃት በቀን 3 ጊዜ እየታሸ አብይን እያመሰገነ ሙቀት ወዳለው አካባቢ እየትዝናና ፎቶ ይልካል።ሳሞራም ኢትዮጵያንን ስለፈጀ በኢትዮጵያውያን ታክስ ይጦራል ለነገሩ እሱስ ምን አጥቶ? እንግዲህ ከላይ ፍርድ ካልመጣ አዲሶቹ ገዥዎችም ልጓም በጥሰዋል ምሁር ተብየዎቻቸው የሚያወሩት ጆሮ ጭው ያደርጋል። አንድ በጣም እውቀት የገባው የኦሮም ምሁር ሃይማኖቶች ሁሉ የተቀዱት ከኢሬቻ ነው ይልሃል(ገመቺስ፤ህዝቄል ጋቢሳ እረ ስንቱ። ለማንኛውም ለዛች ጀግና ልጅ ሰላምታ አቅርብልኝ።

    • ለየትኛዋ ጀግና ሠመረዋ? ስሜንስ ይልቃል ያልከኝ አውቀህ ይሆን ወይንስ ዘንግተኸው?

  2. ትግሉ ይቀጥላል፣ ባንዳ ቅጥረኛው ተለይቶዋል!
    አረበኛ እስክንድር ነጋ ለምን ተመረጠ፣ ከ ”ዐማራ ክልል” ይዉጣ! የሚሉት፣ የዐፋሕድ መመሥረት መጋኛ የሆነባቸዉ የብአዴን፣ የጋላ ኦነግና የወያኔ ትግሬ-ቤጃ መጤዎች ናቸዉ። ያማራ ሕዝብ የሕልዉና ትግል መቃብራቸዉን ሰለማሰዉና ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ እነዚሁ የዐማራዉን ከ45 በመቶ በላይ ሕዝብ አግልለዉ፣ በጎሣ መለያ ሽፋን በምዕራባዉያን የአሜሪካና እንግሊዝ መንግሥታት ዋና ርዳታና ትብብር በኢትዮጵያ ያዋቀሩት የባንቱስታን አፓርታይድ የአናሳ ጎሣ አምባገነን ገዥ ሥርዓትን ለማስቀጠል፣ የተቀራመቱትን ያማራ ለም ምደር ይዘዉ ለመቆየት፣ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ዐማራዉን በዘሩ ለይተው የጨፈጨፉት፣ ያስጨፈጬፉት፣ ከቤት ንብረቱ መኖሪያ ቀበሌዉ ያፈናቀሉትና የዘረፉት፣ የዘር ማጥፋና ማጽዳት ወንጀለኞች ለፍርድ እንዳይቀርቡ ታስቦ ነዉ ያማራ ፋኖን የሕልዉና ትግል ለማስቆም ኦነጋዉያኑ እነ አቢይ አሕመድ መከላከያ ተብዬ የኦሮሙማ ፋሽስት ገዥ ሥልጣን አስጠባቂዉን ወራሪ ባማራ ክፍለ ሃገራት አስገብተዉ ንጹሐን ገበሬዎችን፣ አዛዉንቶና ሕፃናትን በከባድ የጦር መሣሪያና በአየር ኃይል ሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጨምሮ የጨፈጨፈዉ። “በሳምንት ዉስጥ ያማራ ፋኖን ትጥቁን ቀርቶ ቀበቶዉን አስፈታዋለሁ” ብሎ ከ15 ወራቶች በፊት በድንፋታ የገባዉ አረመኔ የጋላ ወራሪ ሠራዊት በያለበት ድባቅ ተመቷል፣ ተማርኮዋል። ሥንቅና ትጥቁን ለፋኖ አስረክቦ ሲፈረጥ በከተማ ዉስጥ ያሉ ስላማዊ ሰዎችን፣ በአዉራ ጎዳና ላይ ተጉዋዦችን፣ በቤተ ክርስቲያን ለቀስተኞችን፣ ምእመናንና ካህናተን፣ የአብነት ተማሪዎችንና አስተማሪዎቻቸዉን በያለበት በገፍ ጨፍጭፈዋል፣ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል። የፋኖን ቅጽበታዊ የማጥቃትና ጠላትን የመደምሰስ ስልትና ችሎታ መቁዋቁዋም በፍጹም የማይችለው ግብስብሱ የነ አቢይ አሕመድ፣ ብርሃኑ ጁላ ፣ ይልማ መርዳሳ ወዘተ ኦነግ/ኦሕዴድ መከላከያ ሰዉ አልባ የጦር አዉሮፕላንና ከባድ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ ያማራ ሰላማዊ ሰዎችን በገበያ፣ በእርሻ ማሳ፣ በቤተ ክርስቲያንና በመስጊድ፣ በትምህርትን በሃኪም ቤት ወዘተረፈ ጨፍጭፎዋል፣ አካለ ስንኩል አድርጎዋል። ይህም ሆኖ ግን ያማራ ሕዝብ የሕልዉና ትግሉ በአሁኑ ጊዜ ባራቱም ክፍለ ሃገራት እጅግ በጣም ተጠናክሮ በድል ዋዜማዉ ላይ ይገኛል።የብአዴን አጋሰስ እስከ ሰባት ቤት ዘር ማንዘሩ ይመነጠራል። ባማራ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅትና ማጽዳት ያደረጉና ያስደረጉ ታድነዉ ለፍርድ ቀርበዉ መቀጣጫ ይሆናሉ። በፀረ ዐማራ ቅጥረኞች መቃብር ላይ ብቻ የአዲሷ ነፃና ደሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትንሣኤ ይረጋገጣል!
    ዲያስፖራ/ ፈላሲ ሰደተኛ/ የተባላችሁ የሴራ ፖለቲካ ዉርንጭላዎችና ጡረተኞች ሁሉ ባማራ ሕዝብ ኪሳራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ልክ እንደ ቅጥረኞቹ ትሕነግና ሻዕቢያ ለሥልጣን ወንበር እንዲያበቁዋችሁ ስትሞዳሞዱ ዛሬም እንበለ እፍረት ስላማዊ ትግል ነዉ እንጂ የፋኖ የትጥቅ ትግል አያስፈልግም እያላችሁ የባንቱስታን አፓርታይድ የጎሣ ፌደራሊዝም ባማራ ሕዝብ ዉድመትና ፍጅት ላይ እንዲቀጥል ፈላጊ የቀበሮ ባሕታዉያን ጥርቅሞ ሰላም፣ ድርድር፣ ጦርነት ይቁም ወዘተረፈ እያላችሁ ታሽቃብጣላችሁ። ባሕር ማዶ ተደንሽራችሁ ፋኖ አንድ ማዕከላዊ መዋቅር ክልፈጠረ ብላችሁ ያዞ ዕንባ ታለቅሳላችሁ። በሌላ በኩልም ፋኖን በጎጥና በመንደር ከፋፍላችሁ አዛዥ ናዛዥ፣ የጦሩ ሜዳ አድራጊ ፈጣሪ፣ የፋኖ አንድነት ተቁዋም መራጭ አስመራጭ ሆናችሁ የሕልዉና ትግሉን ጠልፎ ለማክሰም ከቶ ምን ያልፈነቃላችሁት ድንጋይ አለ? ምንም ጊዜ አይሳካላችሁም። ትግሉ ይቀጥላል!
    ፋኖ ድል ይነሳል! ዐፋሕድ በፍጥነት ወደ አዲስ አበባ! ወደ ሐረርጌ ድሬዳዋ ሐረር ፣ ፈንታሌ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት፣ ዟይ፣ ወደ ጉራጌና ጬቦ፣ ሃድያ ከምባታ፣ ወደ ጋሞ ጎፋ፣ ከፋ፣ ወደ ወላይታ፣ ወደ ወለጋ፣ ወደ ጋምቤላ!
    ዘላለማዊ ክብር ለፋኖ ሰማዕታት!
    ሞት ለኦነግ/ኦሕዴድ ፣ ለብአዴን ብልጽግና፣ ለወያኔ ትግሬ
    ለኢዜማ፣ ለአብን!
    ሸሕድ
    መስከረም 25 ቀን 2017ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

6667uuhhjjjj
Previous Story

የ17 ጀኔራሎቹ አዲስ ዘመቻ ምን ይጨምራል? አስደንጋጩ የአማራ ክልል መረጃ

Eskinder
Next Story

ኳሷ ያላችው እስክንድር ነጋ ጋር ነው – ግርማ ካሳ

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

Eskinder

የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ለፋኖ የህልዉና ትግል መቅሰፍት ነዉ!!

አንተነህ ሽፈራዉ (ኢ/ር) October 15, 2024 መርህ አልባዉ እክንድር ነጋ
amhara

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ