September 30, 2024
13 mins read

የፋኖ መንፈስ በውስጡ የሌለን ደስኳሪ የአማራ ምሁር አትስሙ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Fano fighter

የፋኖን ሺህ ዘመናት የነፃነት፣ የሥነምግባርና የፍትህ ተጋዶሎ ያልተረዳው የዓለም ክፍል “ፋኖ ምንድነው?” ብሎ እየጠየቀ ነው፡፡ ያልተረደው የዓለም ክፍል ስለ ፋኖ ምንነት ቢጠይቅ ተገቢ  ነው፡፡ እጅግ የሚያሳፍረው ፋኖ የተለመደውን ተጋድሎ በጀመረበት ወራት ፋኖን ከብልት ቆራጭና  ህፃናት ጨፍጫፊ ጭራቆች ጋር ደምረው ባገኙት የሕዝብ መገናኛ ሁሉ ሲያብጠለጥሉ የነበሩ ዛሬ ደሞ ይቅርታ እንኳን ሳይጠይቁ ከመቅጽበት ደጋፊ ሆነው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉ ምሁራን ተብዬ ባለዲግሪዎች ማየት ነው፡፡ አነዚህ አብዛኞች እንዳለቀ የጥርስ ሳሙና ቱቦ ቢጨምቋቸው የአማርኛ ጽሑፍ የማይወጣቸው ነገር ግን በተውሶ ቋንቋ የባጡን የቆጡን የሚያወርዱና የፋኖነንት መንፈስ ተአካላቸው ብን ብሎ የጠፋ ድስኩራሞች ቢረሱስትም ፋኖነት የአማራ መንፈስ ነው፡፡

ፋኖነት አማራ በዚህች ምድር ብቅ ታለበት ጀምሮ ከአዳባራቸው እንደ ሃይማኖት ካሉ መንፈሳዊ ቀርሶች አንዱ ነው፡፡ ፋኖነት የጀግንነት፣ የነፃነት፣ የፍትህና የሥነምግብር ሥርዓት ነው፡፡ ታሪክ እንደሚመሰክረው እነዚህ የፋኖነነት መገለጫ ባህርያት ደሞ የአማራ ባህርያትና የኑሮ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ ፋኖነት በውስጡ የሌለ አማራ አማራነቱ የት ላይ ነው? የፋኖ መንፈስ በውስጡ የሌለ አማራ ነኝ ባይ የባህል የጅን ለውጥ (ጂን ሙቴሽን) ክፉኛ የደቆሰው የውሸት አማራ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ባንዳዎችና ፋኖዎችን ሲያጣጥሉ የነበሩ ጣት አፍተልታይ ምሁራን እጅግ የከፋ የባህል ጅን ለውጥ ደዌ የጎዳቸው በሽተኞች ናቸው፡፡

አማራ በፋኖነት ፀበል የሚጠመቀው ገና  በእናቱ ማህፀን አያለ ቀረርቶውን፣ ፉከራውን፣ የጀግንነት ዘፈኑን፣ ዋሽንቱን፣ ክራሩን፣ መሰንቆውን፣ በገናውን፣ ከበሮውን፣ ወረቡን ወዘተ ሲሰማ ጀምሮ ነው፡፡ የለገሰ ዜናዊ የትግሬ ነፃ አውጪ በውጪ ሀይሎች ትከሻ ወንበር ቁጢጥ ታለባት ቀን ጀምሮ  ፉከራ፣ ሽለላና የጀግንነት ዘፈን በአገሪቱ ሳይሆን በእያንዳንዱ አማራ ቤት እንዳይሰማ የከለከለው ይኸንን እውነታ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ለሃያ አምስት ዓመታት ተከልክሎም የዛሬ የአማራ ወጣቶች በፋኖነት ቅዱስ ጸበል ተጠምቀው ፉከራውን፣ ሽለላውንና የጀግንነት ዘፈኑን ሲያንቆረቁሩት መስማት የሚያሳዬው አንድም የመለኮትን ቸርነት ሁለትም አማራ የፋኖነትን በረከት በባህሉ ብቻ ሳይሆን በጂኑ ሰንሰለትም ማስተላለፍ መቻሉን ነው፡፡

ኢትዮጵያን ከአምስት ሺ ዓመታት በላይ በነጻነት ጠብቋት የኖረ የፋኖነት መንፈስ ነው፡፡ የፋኖነት መንፈስ በዋሽንት በሚታጀብ ሽለላና ፉከራ የብረት ካስማዎች የቆመ ነው፡፡ ሽለላና ፉከራ የሰለጠነ ሕዝብ ባህል ነው፡፡ ያልሰለጠነ ሕዝብ የነፃነት ትርጉም እንደማይገባው የታወቀ ነው፡፡ የነፃነንት ትርጉም የማይገባውም ነፃ እንደማይወጣ በብዙ አገራት የታዬ ነው፡፡ ነፃ ያልወጣ ሕዝብ ደሞ የመሸለልም ሆነ የመፎከር የመንፈስ ልእልና አይኖረው፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ራሳቸው የሸጡ ወለፈንዲዎች እንደሚሉት ፉከራና ሽለላ ኋላቀር ባህሎች ሳይሆኑ የስልጡንና የነፃ ሕዝብ ጸጋዎች ናቸው፡፡

በስልጣኔና በነፃናት የኖሩት ቅደመ አያቶቻችን  ጀግና አፍላቂ የሆኑ ፉከራና ሽለላን ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገሩ በአለት ላይ መስርተው አለፉ፡፡ ይኸንን ምስጢር የተገነዘቡ ቅደመ አያቶቻችን ወገባቸውን የሰበሯችው ወራሪዎች ጀግና አብቃይ ባህላችንን ሊቀይሩ ምድር የያዘችውን ድንጋይ ሁሉ ፈነቀሉ፡፡ ለዚህም እንዲረዳቸው ተማርን የሚሉ ጎፈሬ አበጣሪዎችን በወጥመዳቸው አስገቡ፡፡ እነዚህ ሰተት ብለው ተወጥመድ የገቡ ጎፈሬ አበጣሪ ድስኩራም ምሁራንም እንደ ድረስ አንተነህ ያሉ ሽለላና ፉከራዎችን ያልሰለጠነ ሰው ባህሪ አድርገው በምዕራባውያን ዳንስ እንደ ጥንዚዛ መፈናጠርን የስልጣኔ መለኪያ አድርገውት አረፉ፡፡

“በደንባራ በቅሎ ቃጪል ተደምሮ” እንደሚባለው ተዚህ የረጅም ዘመን የወራሪዎች ተንኮል ተጨማሪ በአማራ መቀብር ሪፐብሊክ ለመመስረት ተማምለው የተነሱት የሰይጣን መልክተኞች የጀግንነት ዜማዎች፣ ሽለላና ፉከራ በአገሪቱ እንዳይሰሙ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በቀጥታየም ሆነ በተዘዋዋሪ ከልክለው የወራሪዎችን ተንኮል ተዳር ለማድረስና በእነሱ ላይም ጀግና እንዳይነሳ ለማድረግ ሞከሩ፡፡  ዳሩ ግን ይህን ማድረግ እንዳልቻሉና ወደፊትም እንዳማይችሉ የዚህ ዘመን ፋኖዎች ዳግም አስመሰከሩ፡፡ ወጣቱ የጀግነንት ባህሉን ለመጠበቅ የሚያሳዬው ትጋት የፋኖነት መንፈስ ከአማራ ባህል አልፎ ተጅኑ ውስጥም ተቀርጿል የሚያሰኝ ነው፡፡

አማራ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ከደረሰበት መከራ ትምህርት ቀስሞ እስከ ዳግም ምጣት ተመሳሳይ አደጋ እንዳይደነቀንምበት እቅድ ማውጣትና ራሱን ማዘጋጀበት የነበረበት ከሃምሳ ዓመታት በፊት ነበር፡፡ አርቆ ማሰብ በተሳናቸው፣ ቀጣፊዎችና ወንበዴዎች እንደ አልበሰለች ልጃገርድ በስብከት በሚያታልሏቸው ድስኩራም ምሁራን ምክንያት ይህ ዝግጅት ሳይደረግ ቀርቶ አማራ በመላ አገሪቱ ታርዶ መንገድ ላይ ተጎትቷል፡፡ ይኸንን ግፍ የተመለከተ ፋኖ ሕዝቡን ከመጥፋት ለማዳን እንደ ቅድመ አያቶቹ መስዋእትነት እየከፈለ ይገኛል፡፡ አብዛኛው የአማራ ምሁርን ግን አሁንም ድምጡን አጥፍቶ ሆዱን ሲቆዝር ኖሮ ወደ መቃብር ለመሄድ የመረጠ ይመስላል፡፡ አንዳንዱ “ዓለም አቀፋዊ ነኝ” እያለ እንደ ወጠጤ የሚወጣጠር እንዲያውም አማራ ነኝ ለማለትም ወደል ባቄላ እንደ ጎረሰ ዶሮ ያንቀዋል፡፡ እንደዚህ አይነቱን አስመሳይ ወጠጤ ቅዱሱ መጽሐፍ “ከራሱ በላይ ክርስቶስን እወዳለሁ የሚል ቀጣፊና አጭበራባሪ ነው!” ሲል ይገስጠዋል፡፡  አብዛኛው የአማራ ምሁራኖች ከራሳቸው ሌላውን የወደዱ ለመመስል ወይም ዓለም አቀፋዊ ሰዎች ተብለው እንዲመሰገኑ ለአማራ ሕዝብ እልቂት ጩሁ ሲባሉ እንደ ቀበሮ ተጉድጓዳቸው ይወሸቁና ስለሌላው ተናገሩ ሲባሉ ምላሳቸውን አስልተውና ላንቃቸውን ወልውለው ሲቀርቡ ታይተዋል፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እንደዚህ ዓይነቱን አድር ባይና አስመሳይ መለኮት ቀጣፊ ይለዋል፡፡

እነዚህ የመለኮትን ቃልም ሆነ የዓለም ሁኔታ የካዱ ምሁራን የአማራን ሕዝብ አዘናግተው ሲያስፈጁት እንደኖሩ ዛሬም የህልውናውን ትግል ለማዘናጋት ሌላ ሌላ አጀንዳ እያመጡና ድጓ የሚያካክል ዝባዝንኪ ስለልማት፣ ግድብ፣ ሽምግልና ጂኒ ጃንካ እየለቀለቁ ሲያወናብዱ ይታያል፡፡ የአያቶቻችንን የፋኖነት መንፈስ እንደ ቆሻሻ ከገላቸው አውጥተው እንደጣሉ መሰሪ የማዘናጊያ ሥራቸው ይመሰክራል፡፡

በታሪካችን በወረራ ወቅት  ባንዳ ያልሆነ አማራ ሁሉ ፋኖ ነው፡፡ በአማራ ባህል ወራሪን የረዳ ብቻ ሳይሆን ወራሪን አሜን ብሎ የተቀበለ ሁሉ ባንዳ ነው፡፡ ባንዳነት ለሌሎች ሎሌ መሆን ብቻ ሳይሆን በህልውና ትግል አለመሳተፍ ወይም የህልውናውን ትግል በእንቶ ፈንቶ ድስኩር ማደናቀፍ ሁሉ ባንዳነት ነው፡፡  ለህልውናን፡ ለፃነትንና ለፍትህ የሚደረገውን ተጋድሎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚረዳ ሁሉ ፋኖ ነው፡፡

ፋኖ ዛሬ የሚፈልገው ቃልን ቦጫጭቆ ተሚበላ ጭራቅ ጋር የድርድርና የሽምግልና አለዚያም የልማት፣ የግድብና ሌላም ሌላም ድስኩር ሳይሆን አማራን ከመጥፋት ለማዳን ለሚደረገው ተጋድሎ የቁሳቁስ፣ የወኔ ቀስቃሽ መንፈስና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ማዘናጊያ ድሪቶውን ጥፎ በሕዝብ መገናኛ እየለጠፈ ወይም ድስኩሩን እየነዛ የአማራን ሕዝብ የህልውና ትግል ለማደናቀፍ የሚሞክር የአማራ ምሁር ፋኖነንት ተአካሉ ሙልጭ ብሎ የጠፋ ባንዳ ነው፡፡ ፋኖው የአማራ ሕዝብም የፋኖ መንፈስ በውስጡ የሌለን “ምሁር ነኝ” ባይ ደስኳሪ ሁሉ ለሰንከንድም ባይሰማ፤ በባንዳነትም ቢመዘግበው መልካም ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

መስከረም ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

193794
Previous Story

በአማራ የክልሉ አመራች ታሰሩ | በጎንደር ለመጀመሪያ ጊዜ በሂሊኮፍተር የታገዘ ው*ጊያ ተከፍቶብናል

be649390 7cd7 11ef bf4b ef19cfbf3842.jpg
Next Story

 የረሃብተኞች የጣር ድምጽና የሠማዕታት ደም ጩኸት ለፍትህ ያልቆሙትን ሁሉ ያውዳል – ከበየነ

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop