August 18, 2024
9 mins read

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቀዳሚው የቦይንግ ባለቤት ያደረጉት የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ፅታን በጨረፍታ

Karibu Africa 10 12 16 edited

  1. እንደ መንደርደሪያ፤

ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የ98ኛ ዓመት ልደታቸውን ከማክበራቸው ጥቂት ሳምንታት በፊት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመስብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው፤ ‹የአፍሪካ ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ› ላይ በመገኘት ያስተላለፉት መልእክት ብዙዎችን የስብሰባውን ተሳታፊዎችን ያሰደነቀ ነበር። በኮንፈረንሱ  ላይ ልዑልነታቸውን ያገኟቸውና ኑሮአቸውን በመዲናችን አዲስ አበባ ያደረጉ ሁለት አፍሪካውያን ወዳጆቼ፤ በልዑልነታቸው ታላቅ ሰብእና፣ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ባበረከቷቸው ሥራዎች እጅግ በመደነቃቸው ልዑል ራስ መንገሻን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ሊጎበኟቸው እንደሚፈልጉ ነገሩኝ፡፡

እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኖ ከሳምንት በኋላ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የ 98ኛ ዓመት ልደታቸውን ያከብሩ ነበርና ልደታቸውን ምክንያት በማድረግ ‹እንኳን አደረስዎ!› ለማለት ከአፍሪካውያን ወዳጆቻችን ጋር በመሆን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኘን፡፡ ልዑልነታቸው በ98 ዓመታቸውም እንደ 50 እና 60 ዓመት ጎልማሳ ብርቱ፣ ጠንካራ፣ ወግ አዋቂ፣ በዕድሜ ዘመናቸው ያለፉበትን ትዝታዎቻቸውንና እያንዳንዱን ነገር የሚያስታውሱ ናቸው፡፡ ሕያው የታሪክ ምስክር!!

IMG 20240816 163758 035

  1. የመጀመሪያው ቦይንግና የልዑል ራስ መንገሻ ትዝታ፤

ራስ መንገሻ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የሥራና የመገናኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሊቀመንበር ነበሩ፡  እናም ከልዑልነታቸው ጋር በነበረን ቆይታ ከነገሩን ታሪክ መካከልም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ቀድሞ የቦይንግ አይሮፕላን ባለቤት ያደረጉበት ታሪክ አንዱ ነው፡፡ ልዑልነታቸው ትዝታቸውን እንዲህ አወጉን፤

‹‹ሀገራችን ኢትዮጵያ የሺሕ ዘመናት ታሪክና የገናና ሥልጣኔ ባለቤት፤ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ኩራት ትእምርት/ሲምቦል የሆነች ሀገር ናት፡፡ ስለሆነም አየር መንገዳችን በዓለም ከሚገኙ አየር መንገዶች ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆን ከተፈለገ የቦይንግ አውሮፕላን ባለቤት ሊሆን ይገባዋል!›› በማለት ይህን ሐሳብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቀረቡ፡፡ ይህን ሐሳባቸውን የሰሙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ ይልማ ደሬሳና ጠቅላይ ሚ/ር ልጅ አክሊሉ ሀብተወልድ ለልዑል ራስ መንገሻ እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤

‹‹ሐሳቡ ግሩም ነው፤ ግና የቦይንግ አውሮፕላን ለመግዛት የሚያስፈልገውን 45 ሚሊዮን ዶላር ሀገራችን የላትም፡፡ ብድርም ማግኘት የሚቻል አይደለም። ስለዚህ ልዑልነትዎ የሚኒስትሮች ም ቤት ይህን የቦይንግ ግዢ ሐሳብዎትን ለጊዜውም ቢሆን ውድቅ ለማድረግ ይገደዳል፤››

ራስ መንገሻ በሚኒስትሮቹ ሐሳብ አልተስማሙም ‹‹አገራችን፣ አየር መንገዳችን ቦይንግ አውሮፕላን ያስፈልገዋል፤ እናም ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃ ሥላሴ ይግባኝ እላለሁ!›› በማለት ለአቤቱታ ወደ ጃንሆይ ገቡ፡፡ ነገሩን ለጃንሆይ አስረዷቸው፡፡ ግርማዊነታቸውም፤ ‹‹ይህን ያህል ገንዘብ የሚገኝበት መላ ካለህ ወዲህ በል፤›› በል ሲሉ ልዑልነታቸውን ይጠይቋቸዋል፡

ልዑል ራስ መንገሻም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ ‹‹የአሜሪካ ቦይንግ ካምፓኒ በብድር እንድንገዛ እንዲፈቅድልን  የአሜሪካን መንግሥት እንጠይቃለን፤ ለዚህም እኔ ሙሉ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ፤›› አሉ፡፡

ሁለት ቦይንግ አውሮፕላን በብድር እንዲገዛ ከጃንሆይ ፈቃድ ያገኙት ራስ መንገሻ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከአሜሪካ ባልሥልጣናት ጋር ንግግር ጀመሩ፤ ይሁን እንጂ ለቦይንግ አውሮፕላን መግዣ የሚሆነውን የ45 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘት የገጠማቸው ውጣ ውረድ ቀላል አልነበረም፡፡ ብድሩን ለማግኘት በነበረው ድርድር ወቅት አሉን ራስ መንገሻ- አንድ የአሜሪካ የኮንግረስ አባል፤ ‹‹ንጉሥዎ በቅርቡ ወደ ሩሲያ ጉዞ አድርገው ነበር፤ እና ለምን የሩሲያ መንግሥት አያበድራችሁም?!›› በማለት የሀገራቸውን የገለልተኝነት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አጣብቂኝ ውስጥ የሚያስገባ ጥያቄ አነሳባቸው፡፡

ልዑልነታቸው ሀገራቸው ከሩሲያም ሆነ ከአሜሪካና ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያ ግንኙነት የገለልተኝነት መርሕን የተከተለ መሆኑን በመግለጽ የአሜሪካ መንግሥት ብድሩን እንዲፈቅድላቸው ድርድሩን አስቀጠሉ፡፡  በመጨረሻም ከእልህ አስጨራሽ ድርድር በኋላ ብድሩ ተፈቅዶላቸው ኢትዮጵያ የሁለት ቦይንግ አውሮፕላን ባለቤት ለመሆን በቃች፡፡

  1. እንደ መውጫ፤

ባለፈው ሰሞን ደግሞ የቦይንግ ካምፓኒ በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያ ጽ/ቤቱን በኢትዮጵያ ለመክፈት ስምምነት ላይ የመድረሱን መልካም ዜና ሰማን፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በጽኑ የዐለት መሠረት ላይ እንዲቆም ያደረጉት የእነ ራስ መንገሻና ከእርሳቸውም በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በኃላፊነት የመሩ ኢትዮጵያውያን በሳልና አመራርና በሥራቸው ያስመዘገቡት ስኬት ውጤት ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ስኬቱን፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱንና ተመራጭነቱን  በማስቀጠል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ ምርጥና ተሸላሚ አየር መንገድ ለመሆን በቅቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከመሩት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን መካከል የሆኑት አቶ ግርማ ዋቄ- ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ለኢትዮጵያ አየር

ተረፈ ወርቁ ደስታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop