August 2, 2024
13 mins read

የምን መነሻ! የምን መድረሻ!

አንዱ ዓለም ተፈራ

አርብ፣ ሐምሌ ፳ ፮ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ፮ ዓ. ም. (8/2/2024)

Economic Consequences of Ethiopian Birr Devaluation in Foreign Marketsበማንኛውም መነፅር ቢመለከቱት ወይንም ሚዛን ቢሰፍሩት፤ ዛሬ የዐማሮች ትግላችን አንድና አንድ ብቻ ነው! ነገን ለመኖር ዛሬ መታገልና አቸንፎ መውጣት! ለዐማሮች ነጋችን ዛሬ ነው! የህልውና ትግል የዛሬ ትግል ነው! ስለ ትናንት ወይንም ስለነገ አይደለም! የምንታገለው ለዛሬ ነው!

ዐማሮች የትም አንነሳም! የትም አንሄድም! የትም አንደርስም! ባለንበት፣ በማንነታችን፣ እንኑርበት! ነው ያልነው! ዐማሮች ነበርን! ነንም! እንሆናለንም! ዐማሮች ኢትዮጵያዊ ነበርን! ኢትዮጵያዊ ነን! ኢትዮጵያዊ ሆነንም እንቀጥላለን! ማንነታችን ዐማራነት፣ አገራችን ኢትዮጵያ ናት!!! በቃ!!! ከዚህ ውጪ፤ ዐማሮች የት ተነስተን ነው የት የምንደርሰው? አሁን ያልሆንነውን ሄደን ሌላ የምንሆነው በምን ሂሳብ ነው?

ውድ አንባቢ፤

አንደኛ፤ በማንኛውም ትግል መመሪያ የሚሆን መርኅ እና አቅጣጫ አመልካች ራዕይ ይኖራል። ርዕዩተ ዓለም እንበለው የፖለቲካ ፍልስፍና፤ ታጋዩ ክፍል ትግሉን የሚያስኬድበት እና ፍላጎቱን የሚናገርበት መሳሪያ አለው። የዐማሮች የህልውና ትግላችን መሳሪያ አለን። ያንን መረዳት ያቃታቸው፤ የትግል መርኅ ያስፈልገዋል ብለው፤ “መነሻችን ዐማራ! መድረሻችን ኢትዮጵያ!” ብለው ብቅ አሉ። በርግጥ ይሄን አባባል እስክንድር ከማቀንቀኑ በፊት አንድ የኢኮኖሚክስ ምሁር አንስቶታል፤ ከሱም ቀደም ብሎ ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ያገር ሊቅ ቀምረውታል። ያለቦታው እዚህ ገባና፤ ዝብርቅርቅ ያለ ትርምስ ፈጠረ።

ዐማሮች ከዚህ ተነስተን እዚህ እንድረስ! ብለን አይደለም ትግል የገባነው። ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ዐማራም ኢትዮጵያዊም ነን!!! ይሄ ያልገባው ካለ፤ ሐኪም ያማክር!!! ለምንድን  ነው መነሻችን ዐማራነት የሚሆነው? ዐማራነትኮ ማንነታችን ነው። ኢትዮጵያዊነትም ማንነታችን ነው። ካንዱ ተነስተን ወደሌላው የምንሄደው በምን ሂሳብ ነው?

ሁለተኛ፤ ይሄ ስለተፈጠረ፤ ለዚህ መሞገቻ፤ “መነሻችን ዐማራነት፣ መድረሻችን ዐማራነት!” የሚል ተፈጠረ። በርግጥ ይገባኛል፤ ይሄ የተፈጠረው፤ ዐማሮች የያዝነው ትግል እንዳይጠለፍ፤ ከዐማራነታችን ንቅንቅ አንልም! ለማለት ነው። ይሄ ግን የመታገያ ራዕይ አይደለም። ሁለቱም ለመከፋፈያና ውዥንብር ለመፍጠር የተፈጠሩ እንጂ፤ ትርጉም ሆነ ይዘት ያላቸው የትግል መመሪያዎች አይደሉም። ችግር ግን ፈጥረዋል። ይሄ የህልውና ትግሉን ጎድቶታል። ይሄን መነሻና መድረሻ የፈጠሩት፤ የህልውና ትግሉን ያልተረዱ ናቸው። ትግሉ ከዚህ ወደዚያ እንሂድ አይደለም። ትግሉ የህልውና ትግል ነው ስንል፤ ለመኖር እየታገልን ነው! ለዚህ ወይንም ለዚያ ርዕዩተ ዓለም አይደለም። ሁሉም ዐማሮች በዐማራነታችን ስለተዘመተብን፤ ራሳችንን ለመጠበቅ ተነሳን። ርዕዩተ ዓለማችን፣ ራዕያችን፣ የትግሉ መመሪያችን፤ “ራሳችንን ዛሬን አውለን፤ ለነገ ማሳደር አለብን!” ነው። ይህ ከየትኛውም ሊቀርብ ከሚችል ራዕይና የትግል መመሪያ ሁሉ፤ የበለጠና ጠንካራ የትግል መርኅ ነው።

ሶስተኛ፤ በተመቻቸው ቦታ ተቀምጠውና አንዲት ጣት ለትግሉ ሳያነሱ፣ አንዲት ቅንጣት ሳይሠሩ፤ በትግሉ የተጠመዱትን ለምን እንዲህ አደረጉ! ለምን እንዲያ አያደርጉም! እያሉ የትግሉ ሾፌር የሆኑ ብዙዎች ናቸው። አስተዋጿቸው ነቀፌታ፣ ለቅሶ፣ ፍርሃት መዛቅና ማላዘን ብቻ ነው። ይህ ትግሉን ወደፊት አይወስድም። በሆነ ባለሆነው በመካከላችን ስንጥቅ ለማበጀት የሚናውዙትን ቦታ አንሥጣቸው።

በርግጥ የህልውና ትግላችንን በደንብ ያልተረዱ ብዙ አሉ። እኒህ ትግሉን ሆነ የትግሉ መንገድ ብለው የሚያስቡትና የሚያቀርቡት መፍትሔ፤ ብዙ እንደሚጎድለው ዕውቅ ነው። እኒህ በትግሉ ውስጥ ሲገቡም ሊያቀርቡት የሚችሉት አስተዋፅዖ ውስን ነው። አሁን ዐማሮች በያዝነው ትግል፤ ጥንካሬዎቻችንን ደማምረናቸው፣ ደካማ ጎኖቻችንን አርመናቸው፣ መነሳት መውደቅ መኖሩን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን። በፋኖዎች ትግል ሳትጠመድ ከሩቅ ለነቀፋ ከተቁነጠነጥክ፤ ረጋ በል፣ ያንተን ነቀፋ ወደ ኪስህ መልሰው።

የፋኖዎች ጥንካሬ የሚመነጨው፤ በየራሳቸው ሆነው ከያዙት መሳሪያ ወይንም ከያዙት ጎጥ አይደለም። የሚመነጨው ተሰባስበው በሚያቅዱት፣ በሚያሰማሩት ኃይልና በአንድነታቸው ነው። በመካከላቸው ያለውን ሁኔታ ለመረዳትና መፍትሔ ለማስገኘት፤ እርስ በርሳቸው መደማመጥና መቻቻል አለባቸው። በመካከላቸው መግባባት የሚኖረው፤ ቀስ በቀስ መተማመን አድጎ፤ የጋራ የሆነውን ጉዳይ፤ የጋራችን ነው ብለው ሲቀበሉት ነው።

እኛም እያንዳንዳችን የወገናችን የዐማሮች ጠበቆች እንሁን። ሁሉን ነገር በትክክል ለመረዳት እንሞክር። ሁላችን በአንድ የግንዛቤ ደረጃ ላይ እንቁም። ሁላችንም የየራሳችን መዝገብ ይኑረን። በትክክል አንድ ደረጃ ላይ መቆማችንን እንተዋወቅ። ሁሉም ቦታ ገብተን ከመገኘት፤ በትክክል ልንረዳንዳ ለውጥ ልናስከትልበት የምንችለው ጉዳይ ላይ እናተኩር። ለኒህም ቅደም ተከተል ይኑረን። የተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ሁሉን ነገር መጫን የተለመደ አሠራራችን ነው። ይሄንን እናስወግድ። ተደጋጋሚ ኃላፊነት በአንድ ሰው ላይ ጭኖ፤ “ተሠራ! አልተሠራ!” እያሉ ወሬ አዳማጭ መሆን መቅረት አለበት። ሁላችን በትክክል ሁኔታውን ተረድተን እና ተናበን፤ ትክክለኛ እርዳታ ማድረግ አለብን።

በማውራትና በመሥራት፣ በሌሎች ላይ ኃላፊነትን በመጫንና ራስን ኃላፊ ማድረግ፣ በመውቀስና ሁኔታዎችን በትክክል ተረድቶ ትምህርት በመውሰድ፣ ሁሉን ነገር አዋቂ ነኝ በማለትና ሌሎች ከኔ የበለጠ እውቀት ሊኖራቸው ይችላል ብሎ ለመማር ፈቃደኛ በመሆን፣ ሌሎች ይሄን ወይንም ያንን አላደረጉም ብሎ በመነሳት እና የሌሎችን ችግር በመረዳት መካከል ትልቅ ግንብ አለ። ያ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም። ራስን መርምሮ ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ ግን የግለሰቦች ኃላፊነት ነው። ለነገሩ ከላይ የዘረዘርኳቸው በሙሉ መጠናቸው የተለያዬ ይሁን እንጂ፤ በሁላችንም ውስጥ አሉ። እስኪ ለጋራ እምነታችን ቅድሚያ እንሥጥ። ለኛ በደፈናው ፋኖ ያቸንፋል! ማለት አንድ ነገር ነው። እንዲያቸንፍ ዝግጅቶችን፣ እርዳታዎችን፣ አሰፈላጊ ሁኔታዎችን ማዘጋጀት ሌላ ነገር ነው። እኒህ በሌሉበት፤ ዝም ብሎ ፋኖ ያቸንፋል! ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።

መፈክር መወርወር ቀላል ነው። መፈክሩን በተግባር ለመተርጎም ባለው ሂደት መሳተፍ ከባድ ነው። በያለንበት፤ እስኪ፤ መፈክር ከመወርወር አልፈን፤ “እኔ ኃላፊነቴ ምንድን ነው?” ብለን እንጠይቅ። ይሄ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፤ ሁሌም በሁሉ ቦታ ልንጠይቀው የሚገባ ጉዳይ ነው። ለትንሹም ይሁን ለትልቁ፣ ለዛሬም ይሁን ለነገ፣ በየተገኘንበት ቦታ፤ እኔ እዚህ ምን አደርጋለሁ? እዚህ ኃላፊነቴ ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ። ይሄን ጉዳይ ራሳቸውን የማይጠይቁ፤ በስብሰባውም ሆነ በስብስቡ መገኘት የሌለባቸው ናቸው! ለምን ቢባል፤ መልሱን ራሳቸው አያውቁትምና!! በማንኛውም ቦታ ሆነ ሁኔታ ስንገኝ፤ ከምቾትና ሌሎችን አላስቀይምም ከማለት ይልቅ፤ የመጣሁት ለዚህ ነው! ብሎ ተገቢውን አስተዋፅዖ ማድረግ ተገቢ ነው። ከባድ ጉዳይ አጋጠመንም ከባድ ያልሆነ፤ በትክክል ጉዳዩን መርምሮ ለመሳተፍ ካልሆነ፤ ወደዚያ አንሂድ። ሌሎች ያሉበትን ሁኔታ፣ የሚያስቡትን እንዲያስቡ ያደረጋቸውን ዙሪያ ገብ፣ የወሰዱትን እርምጃ እንዲወስዱ የጋበዛቸውን ሀቅ መረዳት ያስፈልጋል። ያ ካልሆነና ዝም ብለን ለመጓዝ ከቀረብን፤ የሌሎችን ጊዜና ንብረት ነው የምናባክነው።

የሚገርመው ነገር፤ ውጥረት ሲበዛብን፤ ጭልጥ ያለ ብዥታ እንገባና፤ ሁሉን እርግፋ ድርገን ለመተው እጆቻችንን አናነሳለን። ተስፋ ብልጭ ሲል ደግሞ፤ ሁሉ ነገር ተሳካ፣ አለቀ ደቀቀ፣ ብለን ለመፈንጠዝ እግሮቻችንን እናነሳለን። እውነታ ይግዛን! ተጨናጩን እንረዳ! ዐማሮች እናቸንፋለን

 

192735
Previous Story

ፊ/ማ ብርሃኑ ጁላ ለአብይ ቁርጡን ነገሩ | የሰራዊቱ አዛዥ በጄ/ል ተፈራ እጅ ወደቀ | ፋኖ ባልታሰበ ሁኔታ ወልድያ እና ደሴ ገባ | 4ተኛ ቀን ያስቆጠረው ከባዱ የጎንደር ትንቅንቅ

e188b5e18898e18a98e18
Next Story

የፋኖ መሪ ተሰዋ – ባልታሰበ ሁኔታ ፋኖ ደብርታቦርን ተቆጣጠረ | የጎጃም ፣ የጎንደር ፣ የወሎና የሸዋ ፋኖዎች የጋራ መግለጫ! |

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

192896

የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ | የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

https://youtu.be/GMjaXoaAvho?si=JHLNavMjxMse3KFg https://youtu.be/zsnYsJHwmfg?si=MZnzCl3JpShe5ByK የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | የአማራ
454309311 886587770167778 1682362902833604793 n

አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አስገኘች

ፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በ800 ሜትር በታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አስገኘች በ33ኛው