July 29, 2024
7 mins read

መንግሥት ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ

National Bank of Ethiopia Mamoሪፖርተር
– በስምምነቱ መሠረት ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ይተገበራል
መንግሥት ለቀረጸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ትግበራ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘትከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር ሲያደርግ የነበረው ድርድር
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስጠብቅ እና መንግሥት ያስቀመጣቸውን ዋና ዋና የማከሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ቅደም ተከተል መሠረት በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጸሕፈት ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋ ባደረገው መረጃ ፣ መንግሥት ለሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ትግበራ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥረቶችና ድርድሮችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።
ድርድሮቹ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆኑን ለማረጋገጥ በዕውቀትና በብስለት እንዲመሩ መደረጉን የገለጸው መግለጫው ፣ “በዚህም መንግሥት ባስቀመጣቸው ዋና ዋና የማከሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ቅደም ተከተል መሠረት ስምምነት ላይ ለመድረስ ተችሏል” ብሏል።
ይህ የማከሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምም በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ በዓለም ባንክ እና በሌሎች ወሳኝ የልማት አጋሮቻችን የሚደገፍ መሆኑን አመልክቷል። የማከሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምና በመካከለኛው ዘመን የኢንቨስትመንትና የልማት ዕቅድ ላይ የተመሠረተ መሆኑንም ገልጿል።
መግለጫው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎቹን ዋና ዋና የፖሊሲ ርምጃዎች እና የሚጠበቁ ሀገራዊ ፋይዳዎች የዘረዘረ ሲሆን በግንባር ቀድምነት የተጠቀሰውም በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓትን መተግበር የሚለው ነው።
ይህ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት መሆኑን መግለጫው ያስረዳል።
ይህንን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ የሚያስገኘው ፋይዳን ሲዘረዝርም ፣ ” በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል የሚረዳ ፣ የገቢ እና የወጪ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም የሚያስችል እና በክፍያ ሚዛን ላይ ያለውን አለመመጣጠንም ለማስተካከል ይረዳል” ብሏል።
ሌላኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተብሎ የተጠቀሰው በቅርቡ በብሔራዊ ባንክ ይፋ የተደረገውና ወደ ትግረበራ የገባው በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት ነው።
በቀመጠል የተጠቀሰው ቁልፍ ማሻሻያ የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያ ሲሆን ፣ የዚህም ዋና ዋና ትኩረቶች የመንግሥት ገቢን ማሳደግ፤ የመንግሥት ወጪንና የድጎማ ሥርዓትን ውጤታማ ማድረግ፣ በጡረታ ፈንድ ሥርዓቶች ላይ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን መተግበር፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ እና የመንግሥት ብድር አስተዳደር ውጤታማና ዘላቂ እንዲሆን ማረጋገጥ መሆናቸውን መግለጫው ያመለክታል።
ቁልፍ ተብለው ከተዘረዘሩት መካካል በስተመጨረሻ ላይ የተጠቀሰው የልማት ፋይናንስ ዕድሎች እና የመንግሥት ዕዳ አስታዳደር ማሻሻያ ነው። ይህም ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ከተለያዩ አበዳሪዎቻችን ጋር በመነጋገር ከፍተኛ የዕዳ ማሻሻያ ርምጃዎችን ለመውሰድ ያለመ መሆኑን መግለጫው
ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ፣ ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ ኢትዮጵያ አዳዲስ የልማት ፋይናንስ አቅርቦቶችን ፤ በተለይም ከዓለም ባንከ፣ ከሌሎች የልማት ፋይናንስ አቅራቢ ባንኮች እና ከሁለትዮሽ አበዳሪ ድርጅቶች እንድታገኝ መንገድ እንደሚከፍት አመልክቷል።
ከላይ የተዘረዘሩትን ጨምሮ በአጠቃላይ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ብዙ ቢልዮን ዶላር የምታገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ ፣ ይህንን የማከሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየጠበቁ ካሉ ከሌሎች የልማት አጋሮች ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ የሚያግዛት መሆኑን አመልክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

192524
Previous Story

ኢትዮጵያዊነት፡ የአብሮነትና የጥንካሬ ምሥጢር – ቪድዮ

192533
Next Story

የጦር አዛዦች ተመቱ “በአስቸኳይ ይጀመር” አዲሱ የአብይ ዕቅድ አፈትልኮ ወጣ | የአረጋ ደህንነቶች ተያዙ “ምስጢር አወጡ” |

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop