ፋኖ ዘመነ ካሴ ማን ነው

June 22, 2024

 

 

ፋኖ ዘመነ ካሴ ማን ነው

 

 

1 Comment

  1. ፋኖ ዘመነ ካሴ በትምህርቱ ትጉህ ተማሪ መሆኑ ይወራል ብርሃኑ ነጋን ተከትሎም ወደ ኤርትራ በረሃ ወርዶ ምክንያቱ ባልታወቀና እነሱም ባልነገረን ሁኔታ ወደ ጎጃም ተመልሶ ትግሉን ተቀላቅሎ በኋላም መላ ቅጡ በጠፋ ሁኔታ ታስሮና ተፈትቶ አይተናል። የትግል ቆራጥነቱን ወደ ኋላ ብሎ ከብአዴን ዳረጎት ሳይጠብቅ ትግሉ ውስጥ መክረሙ መልካም ነው ነገር ግን አንድ የአማራን ትግል በትጋት እንደሚከታተል ዜጋ የሰውዬው አንዳንድ አካሄዱ አልተመቸኝም ብል በፍቅር የሰከረው ወገን ሊቀየመኝም ሆነ ሊጠረጥረኝ አይገባም። ግለሰቡ በእብሪት የተወጠረ እንደ ሌሎች የፋኖ መሪዎች ትህትና የጎደለውና ሁሉን አዋቂ መስሎ ስለሚታይ ካሁኑ ይህንን እብሪት ቢያጠራ ወደ ፊት ስልጣን ቢይዝ ከሚያደርሰው አደጋ ያቅበዋል የሚል እምነት አለ። አሁንማ ሂዶ ሂዶ የእሱ የእድሜ ጓደኞችና የትግሉ አጋሮቹ ቁንጮ ፋኖዎች እርሶ እያሉ መጥራት ጀምረዋል ይህ ሰው ጫካ እያለ መንግስቱ ሐይለ ሰይጣንን ከሆነ 4 ኪሎ ሲገባ ሊያደርስ የሚችለውን መገመት አይከብድም። ይህ ግለሰብ በዚህ አይነት አመራሩ ዳግም ክልሉን የትግሬ መጫወቻ እንዳያደርገው ጥንቃቄና ምክር ያስፈልጋል። መግለጫ በሚሰጥበት ጊዜ የዚህን ሰው የወደፊት አካሄድ ለመገመት አይከብድም “አዝዣለሁ” “ትእዛዝ ሰጥቻለሁ” እንዲህ ሁኛለሁ እንዲያ ሁኛለሁ የሚለው የእብሪት አካሄድ መልካም አይመስልም ይልቅስ “እኛ” ብሎ አድሬስ ቢያደርግ መልካም ይሆናል። ሌሎች የፋኖ መሪዎች ላይ የማናየውን እብሪት እሱ ላይ ማየት አግባብ አይሆንም። በእርግጥ በጫካ ሁኖ ሞቱን የሚጠባበቅ እንደሆነም ይገባኛል ይህ ደግሞ የትግሉ ጸባይ ስለሆነ ከምግባር የወጡ ነገሮች ይቀጥሉ ማለትም አግባብ አይሆንም። ይህ ቢታረም ለድርጅቱም ለርሱም መልካም ነው እላለሁ። ለድርጅቱ አባሎችና ለህዝቡ ትህትና ለጠላት ጦር ግን አምበሳ መሆን መልካም ነው የራስን ከልት መገንባት ግን ከጥፋት ወደ ጥፋት ያሸጋግረናል። አመሰግናለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

191454
Previous Story

አማራ ክልል በአንድ ዓመቱ የውጊያ ማሳረጊያ | “በፋኖ ምክኒያት ስራዬን ነጻ ሆኘ መስራት አልቻልኩም” አብይ

Beklu Emiru
Next Story

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

Go toTop