የአማራን ሕዝብ ትግል ለመጥለፍ መሞከር በአጥንትና በደማችን ላይ መቀለድ ነው!!! የአማራን ሕዝብ ትግል የሚከፍል ወይም የሚያወናብድ ሀሳብ ጊዜው ያለፈበት ቁማር ሲሆን ሀሳቡና አሳቢውም የሞቱ ናቸው።
ባለፉት አምሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የሚሠራው ፖለቲካ መሠረቱን፣ አዕማዱንና ጣራውን አማራን መጥላት ላይ ያደረገ እና አርክቴክቶቹም የአማራ ጠልነት ትርክት ያሰባብሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች ናቸው። ይህን የፖለቲካ ሴራ የተረዱ የአማራ ልጆች በጊዜው በአማራነታቸው ተሰባብስበው የአማራ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመው የተሰራውን ሴራ ለመታገል ቢሞክሩም በወቅቱ ከነበረው የወቅቱን ፖለቲካ የመረዳት ንቃተ ኅሊና ማነስ – ከጠላት ብርቱ ጉልበት ጋር ተደምሮ ማሸነፍ ቀርቶ ተገዳዳሪም መሆን አልተቻላቸውም ነበር፤ በዚህም የተነሳ የአማራ ሕዝብ በእውነተኛ ወኪሎቹ ከመመራት ይልቅ በተፈጠረለት የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል ሲመራ ቆይቷል።
በሕወሓትና በኢህዴን ውላጅ ድርጅቶች በጠላትነት ተፈርጆ የኖረው ሕዝባችን የጠላቶቹን ጥምረት በሕዝባዊ ትግል አሸንፎ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባርን (ኢሕአዴግ) በ2010ዓ/ም ከመንበረ ሥልጣኑ መገርሰስ ችሏል። በሕዝባዊ ትግል የተገኘው ድል በማንኛውም መልኩ መተኪያ ያልነበረው ድል ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ግን በሕዝባዊ ትግል የተገኘውን ድል በፖለቲካዊ ትግል ለመድገም ሳይቻል ቀርቶ የሕወሓት አገልጋይ የነበረው ብአዴን በሕዝብ ትግል ነጻ ወጥቶ አዴፓ ሆኖ የነበረ ቢሆንም በፖለቲካ ትግል ተሸንፎ ለኦነግ-ብልጽግና በመገበር “የአማራ” ብልጽግና የሚል የዳቦ ስም በመቀበል ወደቀደመ ፀረ-አማራነት ግብሩ ተመልሷል። በመሆኑም የኦነግ-ብልጽግና የፖለቲካ ኃይሎች፣ “የአማራ” ብልጽግና እና የኦነግ-ብልጽግና ፓርቲ የጦር ኃይል ፀረ-አማራነትን እና ፀረ-አማራ ትርክትን በማስቀጠል የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችንና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም፣ በመደበኛና ኢ-መደበኛ ኃይሎች በመታገዝ በሕዝባችን ላይ ጦርነት ከከፈተ ከአምስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።
የአማራ ሕዝብም ደም በተጠሙ የፋሽስት ኃይሎች የተከፈተበትን ጦርነት ምንም እንኳ የማይፈልገው ጦርነት ቢሆንም የሕልውና ጉዳይ ስለሆነ ራሱን እየተከላከለና አምባገነኑን ሥርዓት እየተዋጋ ሕልውናውን ለማስጠበቅ የሕልውና ጦርነት ውስጥ ይገኛል። ሕዝባችን የሕልውና ጦርነት ውስጥ የገባው በቅድሚያ ሕልውናውን ለመታደግ ሲሆን በመቀጠልም የአምባገነኑን የፀረ-አማራ ኃይሎች ጥምረት የሆነውን መንግሥት ለመገርሰስ እና የአማራ ሕዝብ የራሱን ዕጣ ፈንታ በራሱ እጆች የመጻፍ ተፈጥሯዊ መብቱን ለማንበር ነው። የአማራ ሕዝብ ተፈጥሮ የቸረችውን የመኖር መብቱን ሳያረጋግጥ፣ የተስተካከለ ሕዝባዊ መንግሥታዊ ሥርዓት ሳይተክል እና ጥቅሞቹን ሳያስከብር ከትግል ሜዳ በፍፁም የሚያፈገፍግ አይሆንም።
እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት ነገር ሕዝባችን በትግሉ ዕጣ ፈንታውን ይወስናል ማለት ትግላችን የሕዝባችንን ዕጣ ፈንታ ይወስንበታል ማለት አይደለም፤ በሕዝባችን የሚወሰን ትግልና የሕዝብ ዕጣ ፈንታ እንጂ ዕጣ ፈንታው በትግሉ የሚወሰንበት ሕዝብ የለም። በተያያዘም ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ልናሳውቅ የምንፈልገው ጉዳይ በትግላችን ዕጣ ፈንታውን ልንሰጠውም ሆነ ልንነሳው የምንፈልገው ሌላ ኢትዮጵያዊ ብሔርም አለመኖሩን ጭምር ነው።
በመሆኑም በተለያዩ ሚዲያዎች የምንሰማው “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” ዓይነት መፈክሮች የተከበረውን የአማራን ሕዝብ ዕጣ ፈንታም ሆነ የተከበሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሔሮችንም ዕጣ ፈንታ በራሳቸው የመወሰን ሥልጣን የሚጋፋ ስለሆነ የሕዝብ ይሁንታ እስኪሰጠው ድረስ በማንኛውም ድርጅት ሆነ ታጋይ መነገር የሌለበት ሲሆን ሊታርምም የሚገባው ሀሳብ ነው።
በተለይ 1 ከዚህ ቀደም በሕዝባዊ ግንባር፣ አሁን ደግሞ ሕዝባዊ ሠራዊት አመራር ነን በሚሉ መሬት ላይ ግን በግለሰብነታቸው ብቻ በምናውቃቸው ግለሰብ እና በደቀ መዛሙርቱ እየተነሱ ያሉ እንደዚህ ዓይነት መፎክሮች የትግላችንን ታማኝነት በሕዝባችንም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ዘንድ ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥል ነው።
በመሆኑም ሕዝባችንም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሊረዱት የሚገባው ጉዳይ ይህ ሀሳብ በትግላችን ውስጥ ቦታ የሌለው ሀሳብ መሆኑን እና የትግላችንን ፍትሓዊነትና እውነተኝነት ለማጠልሸት የተነሳ አጉል መፈክር መሆኑን ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያየ ጊዜ የልዩ ልዩ ድርጅቶች መሪ የነበረው እና በነበረው ግለ-ስብእና የምናከብረው አቶ እስክድር ነጋ በ06/07/2016 ዓ/ም “የሕዝባዊ ግንባር” መሪነታቸውን አጠናቀው እንደአዲስ የመሰረቱት “የሕዝባዊ ሠራዊት” መሪ መሆናቸውን በመግለጽ መግለጫ አውጥተዋል።
በመግለጫውም እታገለዋለሁ የሚለውን መንግሥት “ደም መጣጭ” ሲለው የአማራ ፋኖ ታጋዮችን ደግሞ “የደም ነጋዴዎች” በማለት ተሳልቋል። ስለሆነም በአራቱ የአማራ ግዛቶች ያለን የአማራ ፋኖ ዕዞች የሚከተለውን የግለሰቡን ሥራዎችና ምድር ላይ ያለውን እውነት ለሕዝባችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ እንወዳለን።
1. የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ታጋዮች ባደራጁት ሕቡዕ አደርጃጀትና ልዩ ልዩ የአማራ ፋኖ መዋቅሮች በጥምረት ባደረጉት የትግል እንቅስቃሴ የመጀመሪያውን የትግል ምዕራፍ በመጋቢት 24/2015 ዓ/ም በሕዝባዊ አመጽ ሲያስጀምሩ ትግላችን ያለምንም መከፋፈል የተሳካ ሕዝባዊ ትግልን በማስጀመር የተቀመጠለትን ግብ መትቶ ነበር። በአራቱም ግዛቶች የነበሩ የፋኖ መዋቅሮችም በአማራ ፋኖ አስተባባሪነትና በአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች መሪነት ከሕዝባዊ አመጹ ቀጥሎ በትጥቅ ትግል የክልሉን ዋና ዋና የወርዳና የዞን ከተሞች በመቆጣጠር የጨቋኙን መንግሥት ክልላዊ መዋቅር ማፈራረስ ተችሎ ነበር። በዚህ ወቅት የነበረብንን የአቅም ክፍተት ለመድፈንና ትግላችንን ከአማራ ክልል በማስወጣት የአገዛዙ ቁንጮ ወዳለበት ወደሀገሪቱ ርዕሰ ከተማ ለመገስገስ በምንሞክርበት ወቅት ይህ ግለሰብ ለጠላቶቻችን በሚመች መንገድ የትግል ጓዶቹን በመክዳት፣ የነበረበትን ሕቡዕ አደረጃጀት በመተውና ከአማራ ፋኖ መዋቅር በማፈንገጥ ለሕዝባችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ሕዝባዊ ግንባር የሚባል ወታደር አልባ የትጥቅ ትግል የሚያደርግ ድርጅት ማቋቋሙን አሳወቀ።
በዚህ በተቋቋመ አዲስ ድርጅት ምክንያት በየዕለቱ በአማራነቱ የጅምላ ፍጅት እየተፈጸመበት ያለው ሕዝባችን እንዲወናበድ ያደረገ ሲሆን የአማራ ፋኖን ትግል ሲጀመር ጀምሮ ሲደግፉ የነበሩ ዓለም አቀፍ የአማራ ድርጅቶችንና የትግሉ የሀብት ምንጭ የሆነውን የአማራ ዲያስፖራን በብዙ መልኩ እንዲከፋፈል አድርጓል።
በተጨማሪም በወታደር አልባው ግንባር ስም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ገንዘብ በማሰባሰብ ለነጻነቱ የወጣን የፈነነ ወታደርና የፋኖ መዋቅር በገንዘብ ለመግዛት የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርግና ሲከፋፍል ቆይቷል። በዚህ ምክንያት ትግላችንን ወደርዕሰ ከተማው ከመግፋት ይልቅ የተፈጠረብንን አዲስ ክፍተት ለመድፈን ስንል በቁጥጥራችን ሥር የነበሩ የዞንና የወርዳ ከተሞችን በመልቀቅ አፈገፈግን።
በዚህ ግለሰብ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት ለመድፈን፣ የተደላደለና ከሌብነት የጸዳ የሀብት ምንጭ ለመፍጠር፣ ተስፋ የሚደረግበትና ብዙኃኑን ያቀፈ ፖለቲካ እንዲኖረን ለማድረግና የተማከለ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍጠር ስንል በጊዜው ያገኘነውን ድል ከማስጠበቅ ይልቅ የትግሉን ክፍተት ለመድፈን ወንድምን መያዝና ወንድምነትን ማስጠበቅ ይሻላል በማለት ከተሞቻችንንና ወገናችንን ለጠላት ለመልቀቅ ተገደድን። ስለሆነም በአማራዊ ጨዋነትና በሆደ ሰፊነት ወንድማማችነትን ለማጠንከር፣ የጋራ አመራርን ለመገንባት ስንል በታወቁ ሽማግሌዎች አወያይነት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ሲመቸው ከግለሰቡ ጋር ደስ ሳይለው ሲቀር ደግሞ ከተወካዮቹ ጋር አድርገናል።
በተለያዩ ጊዜያት በአማራ ብሔርተኝነት፣ የሕዝባችን ትግል የሕልውና ትግል መሆኑን በተመለከተ፣ የኃይል መከፋፈልና አደጋውን በተመለከተ፣ በሕዝባዊነቱና በጋራ አመራር አስፈላጊነት ጉዳይ ውይይቶችን አድርገን አዎንታዊ ስምምነት ላይ ብንደርስም ግለሰቡ ቃሉን የሚጠብቅ ሆኖ አልተገኘም። በቃሉ 2 መገኘትና አማራ ሆኖ መታገል የከበደው ግለሰቡ የሕዝብን ትግል የእሱ ትግል ለማድረግ ከተጓዘው ርቀት በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ችግሮችን በመፍጠር የልዩነት ምክንያት መሆንን ሥራዬ ብሎ ይዞታል። በዚህም ሥራው ለትግሉ፣ ለታጋዩና ለአማራ ሕዝብ ያለውን አለመታመን በተደጋጋሚ አሳይቷል።
ግለሰቡ በአማራ ሕዝብ ትግል ታዝሎ አራት ኪሎ የመግባት ፍላጎት እንጅ የአማራን ሕዝብ ጥያቄ ከአማራ ሕዝብ ታጋዮችና መሪዎች ጋር በመቀናጀት መመለስ የሚፈልግ አለመሆኑን በየጊዜው በሚያደርጋቸው ከፋፋይ አጀንዳዎች አስመስክሯል። ሰውየው የተወውና የናቀው ሕይወትም ካለው ለማይጠረቃ የመንገስ ፍላጎቱ እንጅ ለአማራ ሕዝብ ብሎ መስዋዕትነት እየከፈለ አለመሆኑን አሳይቶናል። በዓለም አቀፍ አስተባባሪነት የመደባቸው ግለሰቦችም ከግንባሩ ጋር አብሮ መሥራትን ያቆሙ ሲሆን በሀገር ውስጥም እምነት ጥለውበት የነበሩ ሁሉ ከእርሱና ከከፋፋይ አካሄዱ ተለይተዋል። በመሆኑም ሕዝባዊ ግንባሩ የአማራን ሕዝብ ትግል መሸከም ቀርቶ አብሮ መሄድ እንኳ የማይችል ስለሆነ ከገንዘብ ማሰባሰቢያነት ያለፈ ሥራ ሳይሠራ ሕዝባችንን እና የአማራን ዲያስፖራ አወናብዶ ትግላችንን አጓቶ ከስሟል።
2. የአማራ ሕዝብ በይፋ እንደሚያውቀው በአሁኑ ሰዓት በአራቱ ግዛቶች ያሉ የአማራ ፋኖዎች የጋራ አደረጃጀት፣ የጋራ አመራርና የጋራ የፋይናንስ ሥርዓት ያለው አንድ ወጥ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አደረጃጀት ለመፍጠር የዕዝ አደረጃጀቶች እየመሰረቱ መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ አደራጃጀቶች ወደአንድ የተማከለ የአማራ ፋኖ አደረጃጀት በመምጣት የሕዝባችንን ጥያቄ በአጭር ጊዜ ለመመልስ ታላቅ ሥራን እየሠሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ይህ አደረጃጀት ሊፈጥረው የሚችለው የአንድነት ኃይል ቦታ ሊያሳጣኝ ይችላል ብሎ የሰጋው የከሰመው ግንባር መሪ አቶ እስክንድር ነጋ የሚፈጥረውን አማራዊ አታጋይና ታጋይ ድርጅት (የአማራ ፋኖ) በሰው ኃይልና በፋይናንስ ለማዳከም አዲሱን የገንዘብ መሰብሰቢያ ፕሮጀክቱን በ06/07/2016 ዓ/ም ይፋ አድርጓዋል። ይህ የማይሳካ አጉል ምኞት የሆነ የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል ፕሮጀክት ከባልደራስና ከግንባሩ የተለየ ሥራ መሥራት እንደማይችል ሁሉም የአማራ ፋኖ ታጋይ ይገነዘባል። ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል አየር ላይ ያለ ቡድን መፍጠሩ ግንባሩን በመሠረተ ጊዜ እንዳደረገው ሕዝባችንን እና በውጭ የሚኖረውን የአማራ ዲያስፖራ ለማወናበድ እንዲሁም ትግላችንን ለመጎተት፣ ለመጥለፍ ካልሆነም ለመክፈል ያደረገውን ሙከራ ለመድገም አስቦ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም አሁን ባለንበት የትግል ምዕራፍ የአማራን ሕዝብ ትግል ለመጥለፍም ሆነ ለመክፈል የሚደረግን ሙከራ በአማራ ጠልነት ካበድውና ከፋሽስቱ የብልጽግና መንግሥት እኩል የምንታገለው ሀሳብና አሠራር መሆኑን እናሳውቃለን። ከሕዝባችን ሕልውና በላይ ግለሰባዊ ሕልውናው የሚገዝፍበት፣ ከሕዝባችን ክብር በላይ ግለሰባዊ ክብሩ የሚበልጥበት፣ የሕዝባችንን ትግል ለግልና ለቡድን ጥቅሙ የሚያውል፣ የሰማዕታትን የከበረ ለአማራ ሕዝብ የተከፈለ መስዋዕትነትን ለግለሰባዊ ክብሩ መወድስ ማቅረቢያ መስዋዕት አድርጎ የሚመለከትን ማንኛውንም ብአዴናዊ ኃይል፣ ግለሰብ ወይም ድርጅት በአማራ መሬት ላይ ብሎም በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር እያየን የምንታገስበት ጊዜ አልፏል። አቶ እስክንድር የሕዝባችንን የሕልውና ትግል ከተቻለው ለመጥለፍ ካልሆነ ለመክፈል እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በመንቀሳቀስ ላይ ነው። የብዙኃኑን የጀግንነት ታሪክ በመጠቅለል ጀግናው፣ ቆራጡ በመባል የሰከረው ግለሰቡ የሕዝባችንን ትግል መጥለፍ ወይም መክፈል የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ቀይ መስመር መሆኑን መረዳትና መስተካከል ካልሆነም የፖለቲካ አስተሳሰቡ ወርድና ቁመናው ሊመጥን ከማይችልበት የትግል ሜዳችን ራሱ ማግለል ይኖርበታል። የአማራ ሕዝብ ትግል አማራ ሆኖ አማራዊ ሥነ-ልቡና የሌለው ታጋይንም ሆነ ድርጅትን መሸከም አይችልም፤ የአማራ ሕዝብ ትግል የግለሰብ የፖለቲካ ሕልውና ማስቀጥያ አማራጭ ትግል ሳይሆን የሕዝባችንን የሕልውና ጥያቄ መመለሻ አማራጭ-አልባ ትግል ነው። ስለሆነም ሕዝባዊ ግንባር የሚባል ሕልውና የሌለው ፕሮጀክት የሕዝባችንን የሕልውና ትግል ዓላማው ያልሆነ፣ ከባልደራስ ወይም ከግንባሩ የተለየ ሥራ መሥራት የማይችል ፕሮጀክት መሆኑን ሁሉም ትግሉ ይመለከተኛል የሚል አካል ሁሉ እንዲረዳው እናሳስባለን።
3 አቶ እስክንድር ነጋ የአማራን ሕዝብ ታጋዮች “የደም ነጋዴዎች” ሲል ከመንግሥት ጎን እኩል የምንጠቀስ ጠላት መሆናችንን ገልጿል። በእርግጥ ሙገሳና ከንቱ ውዳሴ ሲበዛ የምትናገረውን ያሳጣሃል ይባላል። ባልነበረበትና በማያምንበት የአማራ ሕዝብ ትግል ድንገት ተገኝቶ የትግሉ ባለቤት አንተነህ ሲባል፣ ባላደራጀው የፋኖ መዋቅር መኃል ተግኝቶ ፎቶ ሲነሳ የፋኖ አደራጅና አዋጊ ካንተ ወዲያ ላሳር የሚል ውዳሴና ዜማ ሲቀርብለት ከሙገሳው ዝናብና ውሽንፍር የተነሳ ማየት በተሳነው ዓይኑ በትግል ሜዳ ውድ የሕይወት ዋጋ የከፈሉና ሲከፍሉ የሚውሉ ጀግኖችን የደም ነጋዴዎች ብሎ ቢሳደብ የሚገርም አይደለም። በእርግጥ የደም ነጋዴው ማን ነው? በማያምንበት የአማራ ብሔርተኝነትና የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መኃል ተቀምጦ የቀደመ ዝናውን በመጠቀም ትግልን የሚከፋፍል አይደለምን? አንድ ወታደር ሳይኖረው በየጊዜው በአማራ ስም አዳዲስ ድርጅቶችን በመመሥረት ዶላር የሚሰበስበው አይደለምን? ለነጻነቱ የፋነነን ወታደር በገንዝብ ለመግዛት የሚሠራ አይደለምን? የሕዝብ ትግል ሲከፋፈልና ሲጓተት አሻግሮ እንደማይመለከተው ሆኖ የሚመለከት ታጋይ ነኝ ባይ ከእሱ ወዲያ ማን አለ። በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ የደም ነጋዴዎች አሉ ከተባለ በእርግጥም ያሉት አቶ እስክንድርና ግብረ አበሮቹ ናቸው። በተጠጉበት ትግል ተቀጽላ ሆነው መውጣትና መውረስ ያማራቸው በገዳማት ለመነኮሳት መጨፍጨፍ ምክንያት የሆኑ (ምንም እንኳን በንጹሃን መጨፍጭፍ ተጠያቂው ጨፍጫፊው ሥርዓት ቢሆንም) በአራቱ የአማራ ግዛቶች ለነበረውና ለተፈጠረው የፋኖዎች መከፋፈል የመጀመሪያው ተጠቃሽና በአማራ ሕዝብ የነጻነት ታጋዮች ደም የሚነግዱ ከእርሱና ከግበረ አበሮቹ በላይ ማንም ሊጠቀስ አይችልም። ለሕዝባችን ካለን ክብር የተነሳ ጉዳዩን በውይይት ለመፍታትና ትግሉን ለማስፈንጠር ብንሞክርም ግለሰቡ በያዘው የፖለቲካ መሥመር ልዩነት የተነሳ ትግላችንን ለመጥለፍ ወይም ለመክፈል ካልሆነ በስተቀረ ሌላ የአንድነት ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ በሥራው አረጋግጦልናል። ስለዚህ በተጠጋበት ትግል አካል ሆኖ መሥራት ካልቻለ ትግላችንን መጥለፍም ሆነ መክፍል የማንታገሰው ቀይ መስመር መሆኑን እንዲገነዝብ እንወዳለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሚከተሉትን መልዕክቶች ለተከበረው ሕዝባችን፣ ለአማራ ዲያስፖራ እና ለሚዲያ አካላት ማስተላለፍ እንወዳለን።
1. የተከበረው የአማራ ሕዝብ በአማራ ጠል ኃይሎች ቅንጅት ሲፈጸምበት የኖረውን በደል ለመመከት ተደጋጋሚ ትግል ሲያደርግ ኖሯል። በመሆኑም በየጊዜው በትግሉ መኃል ወይም በጎን በሚፈጠሩ አፈንጋጭና ከሃዲ ኃይሎች ትግሉ ሲጠለፍ ወይም ሲከፈል በመኖሩ ሕዝባችን ብዙ የመከራ ዓመታትን አሳልፏዋል። በመሆኑም እነዚህን የመከራ ዓመታት ለመቋጨት በአራቱ ግዛቶች ያሉ የፋኖ ዕዞች ወደአንድ ወጥ ድርጅት ለመምጣት እየሰሩ መሆኑን እያበሰርን በጎን በሚፈጠሩ እንደሕዝባዊ ግንባርና ሕዝባዊ ሠራዊት ዓይነት አሳሳች አደረጃጀቶችን በመታግል የተጋረጠበትን የሕልውና ጦርነት በአካባቢው ካሉ የአማራ ፋኖ ዕዞች ጋር በመሆን ፋሽስቱንና ገዳዩን መንግሥት እንዲዋጋና ትግሉን እንዲደግፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
2. የአማራ ዲያስፖራ በሀገራችን ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እንዲመሠረት በፖለቲካ ትግሉ በግንባር ቀደምነት የተሰለፈ ኃይል መሆኑን እንገነዘባለን። በተለይ የአማራ ፋኖ የሚያደርገውን ትግል በሀሳብ፣ በፋይናንስና በዲፕሎማሲው ዘርፍ በመደገፍና በመምራት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል። ነገር ግን ይህን የዲያስፖራውን ጉጉት የተገነዘቡ እንደግንቦት ሰባት፣ ባልደራስና ሕዝባዊ ግንባር ዓይነት ድርጅቶች መሬት ላይ በሌለና ባልተጨበጠ የመድረክ ስብከት በማማለል የሚፈጽሙትን ማታለል በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል። አሁንም ቢሆን ፋኖነትንና ሕዝባችንን በናቀ ሕዝባዊ ሠራዊት በሚል በመጣው ፕሮጀክት ዲያስፖራው እንዳይወናበድ መልዕክታችንን እያስተላለፍን በግለሰቡ በአዲስ መልክ የተወከሉ ዓለም አቀፍ 4 አስተባባሪዎችም ከግንባሩ የቀድሞ አስተባባሪዎች በመማር ከትግላችን ላይ እጃችሁን እንድታነሱ እናሳስባለን።
3. ትግላችንን ትግላችሁ አድርጋችሁ የሚዲያ ተቋማትን አሠራርና መርህ አክብራችሁ የምትሠሩ ሐቀኛ የሚዲያ አካላት የአማራ ሕዝብን የህልውና ትግል በጊዜ እንዳይቋጭ፣ ከተሳካላቸው ትግሉን ለመጥለፍና የሥልጣን መቆናጠጫ ለማድረግ ካልተሳካላቸው ተቆረቋሪና ታጋይ በመምሰል ትግሉን ለመክፈል፣ በፋኖ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚንቀሳቀሱ፣ የህይወት ዋጋ የሚከፈልበትን ትግል እንደዋዛ በገንዘብ ታጋይ ለመግዛት የሚሞክሩ አስመሳይ የሕዝባችንን ጠላቶች በሙያችሁ በመመርመር ለሕዝባችን እንድታሳውቁ እንጠይቃችኋለን። በገሃድ ከታወቀው ፋሽስት ሥርዓት በማይተናነስ ደረጃ ትግላችንን ለንግድ ያቀረቡ ወንድም መሳይ ጠላቶችን ለሕዝባችን ካላጋለጣችሁ እናንተም ከጠላት ድርጎ የሚሰፈርላችሁ የጠላት ተባባሪ ጠላቶች በመሆን በገዛ ግብራችሁ ስለምትገለጹ ሕዝባችን ራሱን ከእናንተ እንዲጠብቅ በምናገኘው አጋጣሚ ሁሉ በማስተማርና በማንቃት ከጠላት እኩል ዒላማ እንደምትደረጉ ለመግለጽ እንወዳለን።
4. በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለጠላት አሠራር ማስፈፀሚያ በመሆን ለትግላችን መሰናክል እየሆናችሁ ያላችሁ ከዚህ በፊት ለሕዝባችን ትግል ባደረጋችሁት አስተዋጾ የምናከብራችሁ ግለሰቦችና አደረጃጀቶች (በተለይ ኢትዮ 360 ሚዲያ) ለሕዝባችን የሕልውና ትግል ከከፈላችሁትና እየከፈላችሁ ካላችሁት የመስዋዕትነት ዋጋ ጋር ፈጽሞ የሚቃረን በወገንተኝነትና በኢሚዛናዊነት ተግባር እያስቀመጣችሁ ያላችሁትን ጥቁር ጠባሳ በታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍር በመሆኑ እስከዛሬ ለሕዝባችን የከፈላችሁት በምንም የማይተመን አኩሪ አስተዋጿችሁ አሁን እያደረጋችሁ ባለው ተግባር ተገልብጦ የምትሸማቀቁበት ስለሚሆን ቆም ብላችሁ በማሰብ ሐቁን እንድትመረምሩ እንመክራለን። ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ በጎንደር የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ የአማራ ፋኖ በጎጃም የምስራቅ አማራ ፋኖ መጋቢት ፱/፳፻፲፮
——————————
አባታችን ይናገራሉ ስለ አማራ እውነት ነው አማራ ሰው ቢንቅ ኑሮ በኢትዮጵያ ትልቅ ቁጥር ያለው ህዘብ ሁኖ ሳለ በትንሾች ሳይንቃቸው ወያኔ የሚባል ተንከሲስ ነቀርሳ ተሸክሞ ኑሯል አማራው አምርሮ መጥላት ያለበት ወያኔ የሚባል መርዛም ነው /ኣጋመ/???? pic.twitter.com/iFwK1rGvDY
— Aster balcha (@AligazAster) May 24, 2024