February 2, 2024
14 mins read

ጌዲዮን ጢሞቲወስ እና ዘረኛው መንግስት ሕግ በኢትዮጵያ እና ጀኖሳይድ እንደ የናዚ ፓርቲ

መንግስቱ ሙሴ (ዶ/ር)/ዳላስ

download 1

ሒትለር ወደስልጣን ሲወጣ አላማው አንድ እና አንድ ብቻ ነበር። ዘረኝነት!

ዘረኝነት በሕግ ተደግፎ የናዚ ጀርመንን ሕገመንግስት የበላይነት እንዲይዝ ታዋቂው የህግ ፈላስፋ Carl Schmitt ያለ የሌለ እውቀቱን ተጠቅሞ እነ Emanuel Kant የመሰሉ ስለፍትህ እና ግብረገብነት አጥብቀው የሰሩ ሕብረተሰብን ያስተማሩ በተፈጠሩባት ሐገር እነ Carl Schmitt አይነት የሰውልጅ ነፍስን ከሚዛን ያወጡ እና ከይሁዳውያን እስከ ለናዚው ፓርቲ የፖለቲካ ልዩነት የነበራቸውን ሶሻሊስቶች እና የሰራተኛ ማህበራት መሪወችን ጨምሮ የማጥፋት ህግ በ Carl Schmitt እና በናዚ የህግ ምሁራን ተደግፎ Franz Gurtner የህግ ሚኒስቴር በማድረግ የይሁዳውያንን extermination ጀኖሳይድ ህጋዊ ልባስ በመስጠት ስድስት ሚሊዮን ንጹሐንን አስጨፍጭፏል።

ልክ እንደ ጌዲዮን ጢሞቲወስ ጎበዝ ተማሪ የነበረው እና ከህግ ትምህርትቤት በውጤት የተመረቀው ሁሉ Franz Gurtner በዘመኑ ከሙኒክ የታወቀ የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ በኋላ የጋዝ ችማበር የሰውን ልጅ በቁም የሚያነድ ህግን ያጸደቀ። በርሐብ እና በጠኔ ማጎሪያ ቦታወች ተከፍተው የሰው ልጅ በቁሙ ተሰቃይቶ እንዲሞት የፈቀደ ወዘተ የናዚ ፓርቲ ሚኒስቴር እንደነበር ሁሉ እድላሙ Franz Gurtner የናዚ መጨረሻን ሳያይ፤ በኑረምበርግ የህግ ሂደት በወንጀለኝነት ቆሞ ለፍርድ ከመብቃቱ አራት አመታት በፊት 1941 ሞቷል። ጌዲዮን ጢሞቲወስ የ Franz Gurtner እድል እና እጣ የሚያገኝ ሳይሆን በዚህ በመካከለኛ እድሜ ሚሊዮኖችን ያስጨረሰ እና አሁንም ቀጣይ ሚሊዮን ዜጎችን አስጨራሽ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን አውጥቶ ለፋሽስት አሳልፎ ዜጎችን የሰጠ የንግዴህ ልጅ እና የአረመኔ ዘረኛው አብይ አህመድ የህግ ሚኒስቴር ነው። ግን ይህ ሰው የአዋቂ አጥፊ ወነጀለኝነት ደረጃው ከአብይ አህመድ፤ ከብርሐኑ ጁላ፤ ከአበባው ታደሰ የበለጠ መሆኑ እያሳዘነንም ቢሆን እውነት ነው።

ጌዲዮን ጢሞቲወስ ልክ እንደ Franz Gurtner የሰው ፍጡራን ይሁዳዊ በመሆናቸው ብቻ በጋዝ ቻምበር በቁማቸው እንዲቃጠሉ፤ በማጎሪያ እና ማሰቃያ ካምፖች በርሐብ፤ በበሽታ ተሰቃይተው እንዲያልቁ የህግ ድጋፍ እንደሰጠ ሁሉ። ይህ የዘመናችን የህግ ምሁር ጌዲዮን ጢሞቲወስ የተባለ እና የህግ ሚኒስቴር ላለፉት አመታት ኢትዮጵያውያን በዘር እየተመረጡ እና እየታፈኑ ወደ አዋሽ አርባ የበርሐ የማጎሪያ ካምፖች ያለፍርድ እንዲጋዙ አስቸኳይ አዋጅ በሚባል የኢፍትሐዊ ህግ አውጥቶ እና በስራ አውሎ ለፋሽስት አረመኔወች የህግ ሽፋን እየሰጠ ሰው መሆኑ ለአፍታ ሊዘነጋ አይገባም።

ዛሬ ጌዲዮን ጢሞቲወስ የትናንቱ የህግ ምሁር የዛሬ ወንጀለኛ ላለፉት ስድስት ወራት በአማራ ክልል አረመኔው አብይ አህመድ እና የዘር ኩባንያው ታጣቂ ኃይል እንዲዘምት በማድረግ የህግ ልባስ የሰጠ ከመሆኑም በላይ። የአረመኔው አብይ አህመድ ዘመቻ መጠናቀቅ ቀርቶ ሰራዊቱ ተሸክሞት የሄደው መሳሪያ በሕዝብ እየተነጠቀ አራግፎ መመለሱንም እያየ ዳግም ለወንጀሉ መቀጠል ተጨማሪ ግዜ ፈርሞለታል።

አሳዛኙ ወንጀለኛው የፍርድ ሚኒስቴር ላለፉት ስድስት ወራት በአማራ ክልል ሰው አልባ የሆነች አውሮፕላን በሸዋ በተለያዩ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ከተሞች ደብረ ብርሐንን ጨምሮ። በወሎ በጎጃም ደብረማርቆስን ጨምሮ በጎንደር በተለያዩ ከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ሕዝብ በተሰበሰበበት የጸሎት ሰአትን እየመረጠ ጭፍጨፋ ሲካሄድ የህግ ልባስ የሰጠ ወንጀለኛ ነው። ይህ ሁሉ በሐገራችን ላለፉት 30 አመታ በተለይ ላለፉት አምስት አመታት የተካሄደ ዘግናኝ አለማቀፍ ወንጀሎች የተካሄዱት በዚህ በዘመናዊ አለም መሆኑ ያሳዝናል። አስገድዶ መድፈር፤ የጅምላ ጭፍጨፋ ወዘተ እጅግ ተምረው ጣራውን በነኩ በነ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲወስ የፍርድ ሚኒስቴር በሆኑበት መንግስት የተሰሩ ወንጀሎች መሆናቸው አሳዛኝ ያረገዋል።

የተገኙ ያለፉ ትምህርቶች የሚያሳዩት

የሰው ልጅ ታሪክ በባርነት ብቻ ሳይሆን በዘር ማጥፋት፣ “በዘር ማጥፋት”፣ በግዴታ የጉልበት ሥራ፣ በመከበብ በረሃብ፣ በጦርነት እስረኞች ላይ በደረሰበት እንግልት፣ በማሰቃየት፣ በግዳጅ ሃይማኖታዊ እምነቶችን በመርገጥ፣ በጅምላ አስገድዶ መድፈር፣ ሕፃናትን በማፈን እና በሌሎችም በርካታ ዓይነቶች ይገለጻል። ከባድ ኢፍትሃዊነት በተለያዩ ታሪካዊ ወቅቶች ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሥልጣኔዎች የተፈቀደላቸው ወይም የተከለከሉበትን ሁኔታዎች በመግለጽ በሕጋዊ መንገድ የሚመሩበትን ሁኔታ በመግለጽ የራሳቸው ግንዛቤ አዳብረዋል። አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እና እስላሞች ሁሉም ለባርነት፣ ለጦርነት ምግባር እና ለእስረኞች እና ለሲቪል ህዝቦች አያያዝ ደንቦችን አውጥተዋል። ዘመናችን የሰው ልጅ ለክፋት ካለው አቅም ጋር ለመታገል የመጀመሪያው አይደለም።

አንዳንድ ድርጊቶች በተፈጥሯቸው ህገወጥ ናቸው እና ምንም አይነት ሁኔታም ሆነ የተለየ ዒላማ ቡድን ቢሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ መከልከል አለባቸው የሚለው ሀሳብ በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ የህግ አስተሳሰብ ነው። የዚህ እምነት መነሻው የጋራ ሰብአዊነት እሳቤ ነው፣ ሁሉም የሰው ልጅ አንድ የጋራ ተፈጥሮ እንደሚካፈል ሁሉ የተወሰኑ መሰረታዊ መብቶችን እና ጥበቃዎችን የመካፈል መብት አለው የሚለው እምነት ሁላዊ እንደሆነ ይታወቃል ለዚህም ነው የተባበሩት መንግስታት የሰበአዊ መብቶች ህግጋት ያወጣው። የባሪያ ንግድን ለማስወገድ የቀደመውን እንቅስቃሴ ያነቃቃው ይህ የጥፋተኝነት ውሳኔ በአሜሪካ የነፃነት መግለጫ መግቢያ ላይ ስለ እኩልነት እና ስለ “ህይወት ፣ ነፃነት እና የማይገፉ መብቶች” “በራስ የተረጋገጠ” እውነቶችን በመጥራት ክላሲካል አገላለጹን አግኝቷል። ደስታን መፈለግ” በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው, እነዚህ መብቶች በሁሉም ጊዜ ለሁሉም ሰዎች አልተሰጡም. ቀደም ሲል እንዳየነው የአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ውጤት የሆነው የዘር ሃሳብ በተለይ የተወሰኑ ቡድኖችን ወደ ሙሉ እኩልነት በመምታት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ሆኖም ግን አጠቃላይ የአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን የሚያጠቃልለው የጋራ ሰብአዊነት ሀሳብ ታሪካዊ ጠቀሜታ ምንም ጥያቄ የለውም።

ወንጀልን ዲፋይን ማድረግ ባገራችን

እስካሁን ባገራችን መንግስታዊ ወንጀሎች ለፍርድ ቀርበው አልተወሰኑም። ወንጀለኞችም አልተፈረደባቸውም ለምሳሌ በ 1969 የነፃ እርምጃ የተባለው መንግስታዊ ወንጀል በሕዝብ ላይ ሲካሄድ ወንጀልነቱ ቀርቶ ተበዳዩ ሟቹን ወንጀለኛ የሚያደርግ ክስተት ተፈጠረ። አገራችንን ከአርበኝነት ጀምሮ ያገለገሉ ሚኒስቴሮች እና ወታደራዊ መኮንኖች በወታደሩ መንግስት በአንድ ምሽት ተጨፍጭፈው ሕዝብ በሬዲዮ መርዶ ሲነገረው ወንጀል ነው ተብሎ ለፍርድ አልቀረበም። የቤተክርስቲያኗ አባት ብፁዕ አቡነ ቴወፍሎስ ወደእስር ተወርውረው እና በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ የቤተክርስቲያኗ አባት ፀረ አብዮተኛ በሚል ተጠቂው ተወንጅለዋል። በኃይሌ ፊዳ የተቀነቀነው እና ከጆሴፍ እስታሊን የተቀዳው ቀይ ሽብር አንድ ትውልድን ሲጨርስ ወንጀለኛው መንግስቱ ሐይለማርያም እና ቀዩን ሽብር ያካሄዱት አድርባይ ባንዳወች ሳይሆኑ መንግስቱ የገደላቸው እና ቀዩ ሽብር የታወጀባቸው (ነጭ ሽብርተኛ) በሚል ስያሜ ሟቾች ወንጀለኛ ሆነው ፍትህ በጢሟ ተደፍታ ዛሬ ድርስ የቅምጥል ኑሮው ሳይጎድልበት ወንጀለኛው እድሜውን እየጨረሰ ነው።

ያሁሉ ሳያንስ ላለፉት 30 አመታት ዘረኞች እና ምስለኔወቻቸው በትረ መንግስቱን ይዘው ሰውን በሚናገረው ቋንቋ የኮድ ስም እየተሰጠው ሲታረድ ወንጀለኛው ዘረኛው መንግስት ሳይሆን አሁንም በየመንደሩ ጀኖሳይድ እየተካሄደ ያለባቸው ዜጎች ናቸው እንጅ መንግስት አይደለም ሟቾች እና ተፈናቃይ ዘጎች ናቸው ወንጀለኞች። ባጭሩ ፍትህ በሐገራችን ለቁልቁል ተደፍታ ከተሰቀለች ዘመናት አስቆጥሯል። ፍትህ መሳቂያ እና መሳለቂያ ከሆነች ጀምሮ ዜጎች በፍትሕ የሚዳኙበት ሐገር መሆን ካቆመ ትውልዶች ተላልፈዋል ጌዲዮን ጢሞቲወስም ያነኑ በቆሸሸ እና በገለማ መልኩ አስቀጥሏል። ፍትህ ግን አሁንም የምትጮኸው በእርሱ እና የፍትህ ልባሱን በሰጣቸው የአረመኔው መንግስት የበላይ ጠባቂወች እና አማራ መሬት ተቀምጠው በሚያስገድሉ ምስለኔውች ነው። ጌዲዮን ጢሞቲወስ ልክ እንደትናንቶቹ የደርግ እና የወያኔ ወንጀለኞች በባሰ እና እጥፍ ድርብ በሆነ መልኩ አንዱ እና ዋናው የወንጀለኖች የህግ ፊታውራሪ ነው!!

ፍትህ እየፈሰሰ ላለው የአማራ ሕዝብ ደም!!!

ፍትህ ለተናቀው፤ ለተዋረደው እና ሐገሩን በወሮበሎች ለተቀማው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

 

 


 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop