ስንፈራው የነበረ፣ስንሰጋው የከረመ
ግዘፍ ነስቶ፣ሥጋ ለብሶ
ጥርሱን አግጦ፣ዐይኑን አፍጦ
ክንዱን አፈርጥሞ፣ቀንዱን አሹሎ
ሾተል ጦሩን፣ሰብቆ ስሎ
ተገትሯል ከደጃችን::
የመጨረሻው፣መጨረሻ
የዕውር ጉዞ መዳረሻ
ድንበር ዳሩን፣ለመገመት
ፍጻሜውን፣ለመተንበይ
ብዙም አይከብድ::
ባይሆን ተብሎ የሚፈራው
ሁሉን ነገር ተቆጣጥሮ
መሪ ሲሆን፣ስፍራ ሲይዝ
ጠፍቶ እርጋታ፣ሀገር ሲያብድ::
ቀድመው ላወቁ ለነቁ
ላሳሰቡ፣ላስጠነቀቁ
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
መጋቢት ፳፬/፳፻፲፭ ዓ.ም
April 2/2023
እሁድ)2:01(ሚኪ.ላ/አ.አ
©ያመጌዕ