የኢትዮ ሱዳን የድንበር ፍጥጫ ወዴት? June 30, 2022 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የሱዳን ጦር በአርማጭሆ ወረዳ በኩል ከርቀት የመድፍ እና ከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት እየሰነዘረ ነው መባሉ ድንበር ላይ ውጥረት አንግሷል። ጦሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት አቅጣጫ ጥቃት ሰንዝሮ በአካባቢው ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ከተባረረ በኋላ የኢትዮጵያ ጦር ወደ አካባቢው መምጣቱን ነዋሪዎች ማክሰኞ ዕለት ለዶይቸ ቬለ ተናግረው ነበር። የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ በበኩላቸው፦ የሱዳን ጦር ከርቀት መድፍ እየተኮሰ መሆኑን ረቡዕ ዕለት ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል፡፡ አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ በድንበር ይገባኛል የሚወዛገቡት ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሰሞኑ ግጭት የተነሳ የዲፕሎማሲያዊ እሰጥ አገባ ውስጥ የገቡም ይመስላል። ሱዳን አዲስ አበባ የሚገኙ አምባሳደሯን ወደ ካርቱም ጠርታለች። የኢትዮጵያ መከላከያም አስፈላጊ ከኾነ ምላሽ ለመዝጠት በጥሩ አቋም ላይ እንደሚገኝ ዐስታውቆ አስጠንቅቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ጦር ከአወዛጋቢዉ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አጠገብ የሚገኘዉን ጀበል ካላ አል-ለበን የተባለዉን ሥፍራ መቆጣጠሩን ማሳወቁን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ኢትዮጵያ በውስጣዊ የፖለቲካ ውጥረት፤ ግጭት እና የበርካቶችን ሕይወት በቀጠፉ ጥቃቶች ተሰቅዛ ባለችበት ወቅት የሱዳን ሠራዊት ጥቃት ሰነዘረ መባሉ ምንን ያመለክታል? ውስጣዊ የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በራሷ በተለያየ ጊዜ በተቃውሞ ሰልፎች ትታመሳለች። ሱዳን ውስጥ ለዛሬ መጠነ ሰፊ የተቃውሞ ሰልፍ የተጠራ ሲሆን፤ በዋና ከተማዪቱ ካርቱም የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋቱን ሮይተርስ ዘግቧል። የሱዳን ሠራዊት ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት የሰነዘረው ውስጣዊ ውጥረቱን ለማርገብ እና ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ነው የሚሉ አሉ። የ«ታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ሰአታት ስለቀሩትም ጊዜ ጠብቆ የተሰነዘረ ነው የሚሉ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል። በእናንተ ዕይታ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ወረራ እና ጥቃቱን ዳግም ያጠናከረበት ምክንያቱ ምንድን ነው ትላላችሁ? አስተያየታችሁን ፃፉልን። DW Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story አሜሪካ መንግሥት በወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ላይ የያዘውን የተዛባ አቋም አጥብቀን እንቃወማለን! Next Story የአስራ አምስት ቀን ህፃን! – በላይነህ አባተ