April 16, 2022
11 mins read

በሬ በማረድ ከመታረቅ ወደ አማራ በማረድ መታረቅ  (ፍርዱ ዘገየ)

ጽንፈኛ የኦሮሞ ድርጅቶች በሬ በማረድ ከመታረቅ፣ ወደ  አማራ በማረድ መታረቅ ተሸጋገሩ?

የኦፌኮ መግለጫ? ? ለጫ?

Merera Gudina AFP photo

ያመኑት ሲከዳ በሚባለው አገላለጽ አቢይ አህመድ እንኳን የኦፌኮን ያህል ካስቀመጡበት ልኬት ወርዶ የተከሰከሰ አይመስለኝም። ሕወሃት በዋናነት በኢትዮጵያ ወጣቶች ትግል (ከድምጻችን ይሰማ እስከ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ) ከሥልጣን በተወገደች ማግሥት ሥልጣን ላይ ጉብ ያለው ኦህዴድና የሥልጣን ተስፈኞቹ ጽንፈኛ የኦሮሞ ድርጅቶች በሬ እያረዱ ሲታረቁ፣ ሲማማሉ ከርመዋል። አልሠራም። ኦህዴድ “ጥያቄ ያላችሁትን እኔ ብቻዬን እመልሰዋለሁ፣ ሥልጣኑን ግን እርሱት” ብሎ ገገመ። “ቱ! ከኔም ወዲያ ኦነግ ለአሳር” ሳይላቸውም አልቀረም።

አሁን ኦፌኮ ሌላ አዲስ ስልት ይዞ ብቅ ብሏል። 

በዚህ ሁሉ ደም መፋሰስና ድግሥ ጊዜ ዳር ላይ ተወሽቆ ምራቁን እየዋጠ ሲቁለጨለጭ የከረመው ኦፌኮ የጄኖሳይድ መቀስቀሻ የቃላት ገጀራውን እያብለጨለጨ በቦምብ መግለጫዎች ተከሥቷል። በዚሁ ‘አስታውሱኝ አትርሱኝ ከዝርፊያውም ከሥልጣኑም እንካፈል’ ጥሪው ከባለጊዜውና ከባለጫካው ለመታረቂያ ያቀረበው እጅ መንሻ የአማራን እርድ ነው።

እንዴት አንድ የኦሮሞን ሕዝብ እወክላለሁ የሚል ድርጅት ይቅርና አንድ የኦሮሞ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ሰው በዚህ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በጅምላ የሚጨፈጨፈውን፣ ገላው የሚከተፈውን፣ ቆዳው የሚገፈፈውን፣ ጽንሱ የሚበላውን፣ በገፍ የሚፈናቀለውን አማራ በደል እውቅና በመስጠት በኦሮሞ ስም ይህ ግፍ መፈጸሙ እንዳሳዘነው ሳይገልጽ በፊት ሌላ መግለጫ ሊሰጥ ይቻለዋል?

ኦፌኮ ጭራሽ አማራውን በኦሮሞ መሬት ላይ ወረራ እና የተስፋፊነት ጦርነት እንደከፈተ አድርጎ የፈጠራ ክሱን ያዥጎደጉዳል። ከኦህዴድ እና ኦነግ ሸኔ ተብዬዎች ጋር የመታረቂያ እጅ መንሻ ማቅረቡ ነው። አራጆቹ፣ ተስፋፊዎቹ፣ አፈናቃዮቹ እነሱ መሆናቸውን ያውቃልና። ጥቅለላው በስኬት ይጠናቀቃል ብሎ ስላመነ የድል አጥቢያ አርበኛ ተብሎ ነገም ከገበታው እንዳይገፋ ከወዲሁ የተሳትፎ ማመልከቻ ማስገባቱ ነው። ኦፌኮ።

አንድ በቡድን የምትደፈርን ሴት አይቶ ራሷን ሴቲቱን በአጋችነት እንደመክሰስ ያለ አስጸያፊ ድርጊት ነው። ኦፌኮ የፈጸመው።  ሱዳን፣ ሕወሃት፣ ኦነግ፣ የቤንሻንጉል ታጣቂዎች ወረራና ጥቃት እያካሄዱበት፣ በወረራ የተያዙ ቀበሌዎቹ ዛሬም ተይዘው፣ የወደሙ ንብረቶቹ እንደወደሙ ቀርተው፣ የተዘረፉት ተቋማቱ እንደተዘረፉ ባዶ እያሉ፣ የተፈናቀሉት ሚሊዮኖች ያለ እርዳታ በየታዛው እየተንጓለሉ ይህንን በሁለንተናው የተዳከመ በውስጥም በኦህዴድ ደንገጡሮች ተቀስፎ የተያዘ ክልል በአጥቂና በወራሪነት መክሰስ ከነውር ያለፈ የፖለቲካ ሽርሙጥና ነው። ይቅርታ ለዚህ ቀፋፊ ወንጀል ከበድ ያለ ገላጭ ስድብ ስላላገኘሁለት። ኦፌኮ በዚህ መግለጫው ለኦሮሞም ሆነ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ጭላንጭል ተስፋ የሚፈነጥቅ ድርጅት ሳይሆን የጽንፈኝነት ውድድር ከያዙት በኦሮሞ ስም ከሚንቀሳቀሱ ፋሺስታዊ ድርጅቶች ግንባር ቀደሙ መሆኑን ብቻ ነው ያሳየው።

ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ግን እጅግ የሚደነቅ ነው። እንደዚህ ዓይነት በስሙ የሚምሉ የለየላቸው ናዚስቶች ያለመታከት ለጭፍጨፋ እየቀሰቀሱት፤ ሕወሃትም የተመቻቸ የእልቂት ሥርዐት ዘርግታ ሄዳ፣ በተወጠነለት የሩዋንዳ መሰል ጭፍጭፋ ለመሳተፍ አለመነሳቱ በእውነት እጅግ የሚያስደምም ነው። እነዚህ ናዚስቶችማ እንኳን እስካሁን ለሚያልቀው ደሃ ሊያዝኑ የደም ጥማታቸው በበረሃ ጠብታም ውሃ እንዳልቀመሰች ምላስ አንገብግቧቸዋል። እንዴት ተማርኩ የሚል ሰው፣ ሰው የሆነ ሰው እነዚህ ሁሉ ንጹሐን ሲጨፈጨፉ ትንሽ የፀፀት ወይም የሐዝን ስሜት አይኖረውም? ጭራሽ ወፊቱ ገልብጣ ነፋች?

“የፖለቲካ ዓይነ ሥውር ነኝ። ምንም ብርሃን (ራእይ) የለኝም። የምታፋፍሙባቸውንን አፋፍሙባቸውና ለኔ ከሥልጣኑ ፍርፋሪ ጣል ጣል እንድታደርጉልኝ” አይነት የለማኝ ፖለቲካ ነው። ኦፌኮ የያዘው ፖለቲካ። ራእይ አልባ የጨካኝ ተስፈኞች አድማ ብሎ ስሙን ቢለውጥ ይመጥነዋል። እስኪ ዝረፈው! ቀማው! ግደለው! አስወጣና ውረሰው! ከሚለው የወንበዴ መመሪያ ውጭ ለልማትና ለዲሞክራሲ የምትሆን አንዲት ነገር ጠብ ያድርግ! የኦሮሞ ወጣቶች ሠርተው የሚበሉበትን አንድ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮጄክት ይንገረን። “ገለህ፣ አፈናቅለህ ውረሰው” የሚለው ጅልነት በኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ነገ ጠዋት ከአማራ፣ ጉራጌ፣ ጌዴኦ፣ ሲዳማ፣ ጋሞ፣ ጋምቤላ፣ ጉምዝ የተቀማ የተወረሰው ያልቅና እርስ በእርስ “አርሲ ወለጋን፤ ጂማ ኢሉአባቦራን” ጨፍጨፍህ ውረስ ወደሚል ይዛወራል። ሥራ ፈጠራው፣ የኢኮኖሚ እድገት ራእዩ ነበር ቀጣይነት ያለው መፍትሔ ወላጁ። ግን በቅሎ ስትወፍር አይቶ ልጅ እንድትወልድ እንደመጠበቅ ዐይነት ከንቱ ሕልም ነው። ያላት አበርክቶ እርግጫ ብቻ ነው። እና ደግሞ የተሸከመችውን ባእድ ኮተት ይዛ መዞር።

በርቱ ኦፌኮውች። መንገዳችሁ በታሪክ ተተፍተው፣ እንዳተላ ተደፍተው ከቀሩት ከናዚ እና ከፋሺስት ፓርቲ ጋር የተስተካከለ ነው። የኢትዮጵያ አምላክ የነሱን አይነት ጉዳት ሳታመጡ የነሱን ፍጻሜ ይስጣችሁ።

ለማንኛውም before we were rudely interrupted ምን እየተባባልን ነበር? ብለን ይቺን የኦፌኮ ማደናገሪያ የጄኖሳይድ ተኩስ ከዚህ በላይም ትኩረት ሳንሰጣት ወደ ዋናው አጀንዳችን እንመለስ።

ምን ነበር የሃይብሪድ ዋር አዝማቾቹ እነ አምኔስቲ በጭቃ አድበልብለው የወረወሩበን ፈንጂ?

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop