April 4, 2022
49 mins read

ፊሽካውን ማን ነፋውና? – አስቻለው ከበደ አበበ

Abiy Ahmedየቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ትራምፕ፣ እኔ ስልጣን ላይ ሆኜ ብሆን ኖሮ ራሺያ ዩክሬንን አትወርም ነበር አሉን፡፡ በቡሽ ግዜ ራሺያ ጆርጂያን ወረረች፡፡ በኦባማ ግዜ ክሬሚያን፣ አሁን በባይደን ግዜ ዩክሬን ወረረች፡፡ በእኔ ዘመነ መንግስት ግዜ ራሺያ ምንም አለደረገችም ሲሉ ለአለም ፖለቲካ መረጋጋት የነበራቸውን ሚና ይስማልኝ ብለዋል ፡፡

ከወር በፊት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በትግራይ ላይ የተከፈተውን የዘር ማጽዳት ጦርነትን መክተው የትግራይን ህልውና ማስቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በግርምቢጡ የአገዛዝ አራት አመት ግዜያቸው ስለ ሰከነ ፖለቲካ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ስርአተ አልባኝነትን አውግዘዋል፡፡ ሙሰኝነትን ተጠይፈዋል፡፡ በተቋም ደረጃ ስለ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ደጋግመው ገልጸዋል፡፡ አውነታው ግን ያለፉት አራት አመታት የፓርቲያቸውም ሆነ የጦር ጀነራሎቻቸው አካለ ስጋ በጋንግሪን ደዌ የተመታ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

በእሳቸው ዘመን ሦስትዮሽ ጫፎቹን፣ ነጩ ቤተመንግስት ዋሽንግተን፣ ሄሎፖሊስ ቤተምንግስት ካይሮና አራት ኪሎ ቤተምንግስት አዲስ አበባ ላይ ያደረገ ጢልማቆሳዊ መረብ ተዘርግቶ የሃገሪቱን ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያዘቀጠው ይገኛል፡፡ ይህ የትርምስ ትሪአንግልም ህዝባችንን የእሳት ገጀሞ ሲሳይ እያደረገው ነው፡፡ እንደ ሃገር ደግሞ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራናሱዳን በዚሁ ቀውስ እየተለቆጡ ናቸው፡፡

ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን ማብቂያቸው ላይ የሱዳኑን ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክንና የእስራኤልን ጠ/ሚ ቤንያሚን ናታናሁን በስልክ ኮንፍረንስ አግኝተው ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አናግረዋቸው ነበር፡፡ ተወያዩ ከሚባል ይልቅ ትራምፕ ስለ ኢትዮጵያ መጻኢ እድል እንዲሁም ለአለም ሁሉ የአካሄድ አቅጣጪያ አስቀመጡ ቢባል ተገቢ ይሆናል፡፡

ነገሩ፣ ግብጾች ለምን የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ በሚሳኤል አይመቱትም ነው ያሉት፡፡ እዩት፣ ተመልከቱት እራሳቸው አሸባሪ አይሲስ ሲሆኑ፡፡ በሌላ ሀገር ያለ ፕ/ት ሳይሆን አንድ ሚ/ር እንዲ ያለ ቃል ከአፉ ቢወጣ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስ፣ቢቢሲ… ኦሳማ ቢላደን ከሞት ተነሳ ይሉን ነበር፡፡ነገሩ ሁሉ እሳቸው ሲሉት ቅዱስ ነውና የሚዲያዎቹ እውነተኝነትን በትሪፕል ስታንዳርዳቸው እንድናልፈው ግድ ይለናል፡፡

አስቲ እሳቸው ለአለም ያስቀመጡትን አቅጣጫ  ውክልና በአለም አቀፍ ፖለቲካ መነጽር ለማየት የፖለቲካዊ ሃቆቹን እንዘርዝር፡፡  የህዳሴው ግድብ ከአባይ የውሃ ፖለቲካና ከአስዋን ግድብ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው፡፡ የግብጽ የአባይ ውሃ ይገባኛል የድልዳሌ መጠን፣ ቀኝ ገዢዋ እንግሊዝ የሰጠቻት መጠንና ግድቧን ደግሞ በገነባችላት ራሺያ ልክ ነው፡፡

እስራኤል ኢራን ሱዳን ውስጥ ገንብታዋለች የተባለውን የድሮን ፋብሪካ  በበንብ ካጋየችው ገና ስምንት አመቱ ነበር፡፡ አሜሪካ ከስልጣን በሃይል የተገለበጡት የቀድሞው የሱዳን ፕ/ት ኦማር አልበሽር ግዜ አልቃይዳ በኬንያና ታንዛኒያ የአሜሪካን ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃት ሲያደርስ፣ ሱዳን የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ብላ ታምን ስለ ነበር የሽግግሩን መንግስት ካሳ ጠየቀች፡፡ የሱዳን የሽግግር መንግስት 335 ሚሊዮን ዶላር ለአሜሪካ ከፍሎ ሀገሩን ከሽብረተኛ ደጋፊ ሃገሮች ዝርዝር ውስጥ ካሰረዘና  ከአሜሪካን ጋር ዲፕሎማሲያዊ እርቅ ከደረገ  ገና አንድ አመቱ ነበር የነትራምፕ የስልክ ውይይት ሲደረግ፡፡

አስተዋይ ልብ ካለ፣ የትራምፕ ንግግር ዝም ብሎ ከግል ባህሪ የሚመነጭ ሳይሆን ሁን ተብሎ ታቅዶ የተነገረ ነው፡፡ ንግግራቸው ብዙ ሃገሮችን ታሳቢ ያደረገም ነበር፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሃገሮች፣ በጠቅላላ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲና ሱማሊያ እንዲሁም ሱዳን፣ግብጽ፣እንግሊዝ፣ ራሺያና እራሷንም አሜሪካን ያካትታል፡፡ ንክኪው ግን ብዙ ነው፡፡ ራሺያ በሱዳን ግዙፍ የጦር ካምፕ ልትገነባ ብላ ኦማር አልበሽር ከስልጣን በመገልበጣቸው ቀርቷል ወይም እስከአሁን  ዘግይቷል፡፡

ፕ/ት ትራምፕ ጠ/ሚ አብይ ያገኘው የኖቬል ሽልማት ለኔ ይገባኝ ነበር ብለውናል፡፡ በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ሊካሄድ የነበረ ጦርነትን እንዳስቆሙም ነግረውናል፡፡ በህዳሴው ግድብ ላይ አሜሪካ ከታዛቢነት አልፋ አደራደሪ እንድትሆን ጠ/ሚሩ ራሺያ ሄደው በነበሩበሩበት ግዜ ተስማምተው ከመጡ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ እንድነት ድርጅት ስር ይሁልኝ ብለው ቃላቸውን አጥፈዋል፡፡ በዚህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ስህተት ሰርተዋል፡፡ ቱልቱላ የሚነፉ አንዳንድ የእሳቸው አክቲቪሰቶች እንደሚሉት፣ አሜሪካ መአቀብ ብታደርግብን ራሺያ አለችን የሚለው አባባል በአባት ሃገር ራሺያ ዜማ ሲታጀብ ሃገሪቱን ለወያኔ ዲፕሎማሲያዊ ድል  አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

ስልጣን በአፍሪካውያን ዘንድ ፕሮጀክት ነው፡፡ ገና ስልጣን ላይ ሳይወጣ፣ በተቃዋሚ ደረጃ ሳሉ ወደ አሜሪካ ወይም አውሮፓ ይጠሩና ለሃገረዎ፣ ለአፈሪካና አለምቀፍ ማህበረሰብ የለዎትን አተያይ ይገልጻሉ፡፡ የችግር አፈታት ዘዴንም ይተነትናሉ፡፡ የምዕራቡ አለም ጥቅምን እንዴት ማስቀጠል እንደሚችሉ ፍኖተ ካርታውን ያስቀምጣሉ፡፡ ከዚያም ለስልጣን የሚያበቃዎን ድጋፍ፣ ክትትልና ምዘና ይሟላልዎታል፡፡ ከዚህ አቅጣጫ ውልፍች ያሉ ግዜ ዝግጁ የሆኑ ጉች ጉች ያሉ ተቀዋሚዎችዎን መሳብ ይጀመራል፡፡ ይህ ለነበረው፣ላለውም ለሚመጣውም የሰራና የሚሰራ ነው፡፡

ስለ ራሺያ ከነሰሁ ላይቀር በዛሩ ዘመነ መንግስት ግዜ ስለነበሩት ከኢትዮጵያዊው ዳግማዊ ቴውድሮስ እስከ ራሺያዊው ቴውዶር አንዳንድ ነገር ልበል፡፡ አውሮፓ የኢንዱሰትሪ አብዮት በምታካሂድበት ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ ማሽኖችን እሰከነ ኃይል ምንጫቸውና በግዜው የነበረውን ቴክኖሎጂን እስከ ስነ ፈለክ እይታው ድረስ ለማስተዋወቅ ጥረት ያደረጉ ነገስታት ነበሩ፡፡ ንጉስ ሳህለስላሴ፣አጼ ቴውድሮስ፣አጼ ዬሐንስና አጼ ምንሊክ በግዜው አለም የደረሰበትን ስልጣኔ ለሃገራቸው ለማስተዋወቅ የቻሉትን ሁሉ ያደረጉ ነገስታት ናቸው፡፡ በምንሊክ ግዜ ግን ሁሉም ነገር ፈር መያዝ ጀመረ፡፡

አጼ ቴውድሮስ በወታደራዊው ሳይንስ ዘርፍ ወሎ መቅደላ አምባ ላይ የከሸፈውን ሴቫስቶቮል መድፍን ጨምሮ በመቶ የሚቆጠሩ አነስተኛ መድፎችን ማሰራት ችለው ነበር፡፡ በጎንደር – ጋፋት የነበረውን ፋብሪካ ሲያሳልጥላቸው የነበረው ሰው የሩሲያ ወታደር የነበረ ፖላንዳዊ አየሁድ ነበር፡፡ ይህ ሰው እ.ኤ.አ. በ1853ዓ.ም. በክርሚያ ወደብ ሴቫስቶቮል ላይ  በራሽያና ቱርክ መካከል በተደረገው ጦርነት የሩሲያ ወታደር ሆኖ እንደተዋጋ ታሪክ ያትታል፡፡

እኔ መዩ ቱርክ ባይ

የምሸሽ ነኝ ወይ?

መዩ ቴውድሮስ ሲሞት በለቅኔዎቹ ደግሞ፣ አርብ አርብ ይሸበራል እየሩሳሌም…ብለው ገጠሙለት፡፡ ቴውድሮስ-መዩ ሲፎክር ”የኢትዮጵያ ባል የእየሩሳሌም እጮኛ…“ ይል ነበር፡፡ ቴዲ የግብጽ-ቱርክ ጦርን በመዋጋት ነው የጎለመሰው፡፡ ራሺያ ክርሚያ- ሳቫስቴቮል ላይ ከቱርክ ጋር ጦርነት ስታደርግ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ከቱርክ ጎን ቆመው ወግተዋታል፡፡ በጦርነቱ  ራሺያ ተሸነፈች፡፡ መዩም መድፉን ሴቫስቶቮል ብሎ ጠራው፡፡ እንደሱ ሃሳብማ እይሩሳሌምን ከቱርክ አገዛዝ ነፃ ማውጣት ነበር ያሰበው፡፡

አሁን ወደ ራሺያው ቴውዶር ወይም ቴውድሮስ ልምጣ፡፡ ይህ ሰው ራሺያዊ ጆግራፈር እንደሆነ ይታመናል፡፡ የፓሪስ ኮሚዩን አባል ነበረም የሚሉ አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመጣ በኋላ እኔ በትንቢት ሲነገርለት የነበርኩት የኢትዮጵያው መሲሕ ቴውድሮስ ነኘ አለ፡፡ ዘመኑ የአጼ ዮሐንስ ዘመን ነበር፡፡ በሸዋ ብዙ የአማራና ኦሮሞ ተከታዮች አግኝቶ ነበር፡፡

አጼ ዮሐንስ ሰው ልከው አስያዙት፡፡ እሱ የነበረው በሸዋ ነበር፡፡ የረር(ሸዋ) ላይ ከትሞም እንደነበር ታሪክ ያወሳል፡፡ አማርኛናኦሮምኛን ጨምሮ ሰባት ቋንቋ ይናገራል፡፡ የቁራንም እውቀት ነበረው፡፡ የተያዘው አምቦ አካባቢ ይመስለኛል፡፡ አንገቱ ላይ የሚያንጠለጥለው ትልቅ የብር መስቀል ነበረው፡፡ ከሽዋ ተይዞ ወደ መቀሌ ሲሄድ ወሎ ወረሂመኑ ላይ ጠፋ፡፡ ስለዚህ ሰው “ሕዝቅኤል፣አይነ-መዓቱ” የሚለው ልብወለድ መጽሐፌ ላይ አካትቼ ጽፌለሁ፡፡

ሃገራችን ከሰላቭ ህዝቦች ጋር ይህን የመሰለም የታሪክ ግንኙነት አላት፡፡ የስላቭ ህዝቦች ለመጠፋፋት እነዴት ተነሳሱ ብለን ብንጠይቅ፣ያው እንደኘው  መልሱ ጉች ጉቼዎች ላይ ያርፋል፡፡ የጉቼ ጉች ፖለቲካ መሬታዊ አካል ሲነሳበአማራና ትግራይ መሃል ወልቃይትና ራያ ሊሆን ይችላል፣ በትግሬውና ኤርትራው መካከል ባደሜ፣ለህንድና ፓኪስታን ካሺሚር፣ ለቻይና ደግሞ ታይዋን ይቀጥላል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከመሃል እስከ ዙሪያው ገባው ብዙ ጉች ጉቼዎች አሉት፡፡ እነዚህ ጉች ጉቼ አናናስ ቦምቦች ተቀጣጥለው የፈነዱ ግዜ ምስራቅ አፍሪካ ትነዳለች፡፡ አያድርግብን ለወንድሞቻቸንም ልብ ይስጣቸው እንጂ፣ለተረኞቹ ማለቴ ነው፣ አያድርግብን ፡፡ ደግሞ ስንት ዘመን እንማቅቅ? ሰው ሃገሩንም፣ ሃጉሩንም አለም አቀፋዊም ሆኖ ሊኖር ይገባል፡፡ ብሔር ብቻ ነኝ ብሎ ከማቀቀ ግን እንዴት እኒህን መሆን ይቻለዋል?

ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ባለቤታቸው የስላቭ ዘር ቢኖርባቸውም፣ የይኩሬንን ጦርነት በማስነሳት በህዳሴው ግድብ ላይ ቦምብ አውሩዱበት በማለት፣ የሪፕል ኢፌክት ጡዘቱን ጀምረዋል ባይ ነኝ፡፡ ራሺያ በደምብ ነው ያዳመጠቻቸው፡፡ አባይ ወደ ግብጽ ፈሶ ሜዴትራኒያ ባህር ውስጥ ገብቶ ያበቃል ይላሉ፡፡ በጣና ሃይቅ ላይ አለፎ ሲሄድ የማይነካካው አባይ፣ ምናለባትም ሜደትራኒአን ባህርን እንከባበር ብሎ፣ ጥቁር ሲሉ ሰምቶ አቋርጦ በመሄድ ጥቁር ባህርን ነገር ሳይፈልግ የቀረ ይመስላችኋል?

በአሜሪካ ዲሞክራቶች ግዜ፣ አሜሪካና ናቶ በአንድ ላይ ሆነው  ዩጎዝላቪያን በመውጋት ቤልግሬድን ሁሉ በቦንብ ደብድበዋል፡ በቤልግሬድ የነበረው የቻይና ኤምባሲ የድብደባው ሰለባ ሆኖም ነበር፡፡ የዚያን ግዜ ራሺያ ደርጊቱን ከማውገዝ ውጭ ምንም መድረግ አልቻለችም፡፡ ያኔ የሰርቭ ብሄርተኝነት እዚያ ላይ ተሰበረ የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ በራሺያና ዩክሬን መካከል ጦረነቱ ከመካሔዱ በፊት የነበሩ ፖለቲካል ድቨሎፐመንቶችን ማየት ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ሰው መሳይ በሽነጎ የሆኑት ፕ/ት ትራምፕ ፣ እርሰዎ የጦርነቱን ፊሽካ ነፊ እነደነበሩ ማን ይንገርዎት?

የዩክሬን ግዛት አካል የነበረችውን ክርሚያ ራሺያ እ.ኤ.አ. 2014 ዓ.ም. ላይ  ወራ ስተይዝ ታሪካዊ ሃቅ አድርጋ ያስቀመጠችው ነገር በ1850ዎች ከቱርክ ጋር ስትዋጋ  ግዜ እንኳን የራሺያ አካል መሆኗንና ለአስተዳደር አመቺነት ሲባል ከዩክሬን ጋር በቀድሞዋ የተባበሩት የሶቪየት ሪፓፕሊክ ግዜ አብራ መሆኗን ነው፡፡ በዚያን ግዜ ዩክሬንና ሩሲያ አንድ ሃገር ነበሩ፡፡

ከትራምፕ ንግግር በኋላ አሁን ያለውን የስላቭ ወገኖች እርስ በእርስ ያጠፋፋው አባይ ወንዝ ውስጥ የተጣለው የፕ/ት ትራምፕ ምናባዊ ቦንብ  ክብዮሽ እየሰራ ጥቁር ባህር የደረሰ ይመስላል፡፡ በአለማችን ላይ አራት ወሳኝ የሆኑ መተላለፊያ  ቦዮች አሉ፡፡ እነዚህ መተላለፊያ ቦዮች አውሮፓ፣አፍሪካና ኢሲያን ያገናኛሉ፡፡ የእንግሊዝና ፈረንሳይ ቀኝ ገዢዎች በእነዚያ ቦታዎች ሁሉ ላይ በስላምም ይሁን በጦርነት ያደረጉትን ተሳትፎ ከታሪክ መገንዘብ ይቻላል፡፡

እነሱም በሞሮኮና ሰፔን መካከል መተላለፊያ የሆነውና ሜደተራንያን ባህር ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር የሚያገናኘው ጂብርአልታር፣ በእንግሊዝና ፈረንሳይ ጥምረት የተከፈተው ሜዴትራኒያን ከቀይ ባህር ጋር የሚያገናኘው የግብጹ ሲውዝ ካናል፣ በየመንና ጅቡቲ መካከል ያለውና ቀይ ባህርን ከህን ውቅያኖስ ጋር የሚያገናኘው ባብ አል መንደብ እንዲሁም ራሺያ ከጥቁር ባህር ወደ ሜዴትራኒያን ባህር የምትወጣበት በቱረክ ኢስታምቡል የሚገኘው ቦይ ነው፡፡

እንዴት ሆኖ ነው ታዲያ አባይ ላይ የተንቦጫረቀው ውሃ ራሺያ ጥቁር ባህር  ላይ ደርሷል ሲባል አመክኖዊ የማይሆነው? ነገሩ ለንግድም ይሁን ለወታደራዊ የበላይነት አራቱ መተላለፊያ ቦዮችን በችሮታ ለማግኘት ሳይሆን፣  በአለምአቀፍ ደረጃ ተጽእኖ መደረግ በሚቻልበት ቁመና ለመገኘት ሲባል ነው ኃያላኑን እርስ በእርስ የሚራኮቱት፡፡፡፡

እዚህ ላይ አጼ ኃይለሰላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን ንግግር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ጣሊያንና ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ሆነው ሳለ፣ በህጉ መሰረት ጣሊያን  ኢትዮጵያን መውረር አትችልም ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ግን ተወረረች፡፡ ንጉሱ በስደት በሊግ ኦፍ ኔሽን መደረክ ላይ ተገኝተው ታሪካዊ ብቻ ሳሆን ትንቢታዊ ንግግር አድርገው ነበር “ዛሬ እኛ ተወረርን… ነገ ደግሞ ተራው የናንተ ነው፡፡” እውነትም ሆነ፤ አውሮፓ በናዚዝምና ፋሺዝም ጠፋች፡፡ እንግዲህ ትራምፕ ምስራቅ አፍሪካ ላይ  ያስነሱት ንፋስ ማጣፊው ምን ይሆን?

አሁን ደግሞ ወደ ወገኖቻችን ትግሬዎች ስርወ መንግስት ልምጣ፡፡ መቼም ፋኖ መሳፍንትን ስለተናገረው ነገር ሁሌም አደንቀዋለሁ፡፡ እርሱ ባያውቀውም ደጀን ተራራ ነው፡፡ ልቡም በዚያው ልክ ነው የሚመታው፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር “እኛ ወያኔን ከዚህ ወርደን እንይዛላትን…ትግሬዎች ግን እኮ አጎቶቻችን አያቶቻችን ናቸው…”

ይገርማል ነገረኛ ወያኔዎች ስለ መጨበጥ ብቻ አወሩ፡፡ በዚያም ህዝብን ቀሰቀሱ፡፡ ትግሬ ልትያዝ ነው፣ ልትጨበጥና ልትጨፈለቅ ነው አሉ፡፡ ግን ስለ ዝምድና ስለተናገረው ምንም ያሉት የለም፡፡ ጥያቄ አለኝ፣በፌድራል መንግስቱና በትግራይ ክልል መካከል የተካሄደውን የአውዳሚውን ጦርነት ፊሽካ ማን ነፋው? ነገር በሶስት ይጸናል እንዲሉ በመጀመርያ ሴኩቱሬ ከዚያም ጀነራል ፃድቃን፣ ጀነራል ምግበይ እንዲሁም ገልቱው ጌቾ ጦርነቱን ህወሓት እንደጀመረው ተናግረዋል፡፡

እና የዘር ማጽዳቱን ጦርነት ከሰሜን እዝ እሰከ ማይካድራ ማን እንደ አስጀመረው፣ማንስ ፊሽካውን እንደነፋው፣ ዶ/ት ደብረጽዮን፣ እባኮቱን ስለ እናታችን ጽዮን ሲሉ ይንገሩን፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር ልጨምርልዎት፤ ትራምፕ ግድቡን ግብጽ ታውድም ካሉ በኋላ እናንት ሰሜን ዕዝን ለመምታት ስንት ሳምንት ነው የወሰደባችሁ? እናንት የሆናችሁት የፊሽካ- ፊሽካ ነፊ መሆን ብቻ ነው፡፡ የራሻችሁ የሆነ አንድም ፊሽካ ኖሯችው አያውቅም፡፡

መቼም የወንድም ጠ/ሚ አብይ አህምድ ዘመን ግርምቢጥ ነው፡፡ የዞረ የጦርነት ድምር ሰለባም ይመስላል፡፡ ችግሩ ግን የራሱንም የአስተዳደር ዘይቤና ወለፈንዴነት ያጠቃልላል፡፡ አጼ ኃይለስላሴ ሊፋጋሮ ከተባለ ጋዜጣ ጋር በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ ከኤርትራ እስከ መቋደሾ የተዘረጋ ፀረ ኢትዮጵያ መሰመር መኖሩን ንጉሱ ተናግረው አምብቤለሁ፡፡ ይህን ደግሞ ኤርትራና ሱማሌን በቀኝ ግዛት ከገዛችው ኢጣሊያን ሌላ ማን ሊሰራ ይችላል ብዬ እራሴን ስጠይቅ፣ የሞሶሎኒ ፋሺዝም ተሸነፈ ተባለ እንጂ አስተሳሰቡ በግዜው በነበሩ አዲሶቹ ኃያላን ዘንድም እንደቀጠለ ነው የሚያመላክተው፡፡

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ፣ ዲሞክራሲያዊ ወይም ቲዎክራሲያዊ(ሐይማኖታዊ) መሪ መሆን እንዳለባቸው ግራ የገባቸው ይመስላል፡፡ ይህን ለማለትም ምክንያት አለኝ፡፡ በትንቢት የተነገረልኝ ነኝ ምናምን የሚለውን ትቼ፣ የፌድራል መንግስቱ ከትግራይ ክልል ጋር ባደረገው ጦርነት ግዜ የተናገሩትን ልጥቀስ፡፡

የወያኔ መሪዎች ዱቄት ሆነው ተበትነዋል፣ከዚህ በኋላ ተሰብስበው ምንም አይሆኑም አሉን፡፡ ይህ እንግዲህ ከመዝሙር ወይም ዛቡር ላይ ያለ ጥቅስን ያመላክታል “ ጠላቶቼ በንፋስ ፊት እንደ ትቢያ ፈጭቼ እበትናችዋለሁ…”መዝ 18፣ 45- አሁን በመጨረሻው ወያኔ ከሰሜን ሸዋ ወደ ትግራይ በተመለሰበት ጦርነት ላይ ደግሞ ፣ከእርሳቸው ጋር አብሮ ወጥቶ ስለ ተዋጋው ፈጣሪ እርሳቸው ብቻ የሚያውቁትን ተአምር ሊያስገነዝቡን ከሞከሩ በኋላ እነ  ስብሃት ነጋን ፈጣርዬ በምህረትና ይቅርታ ፍታ ብሎ ጠይቆኛል… ብለውን አረፉት፡፡ እንግዲህ “የጌድዎንና የእግዛብሔር ሰይፍ …” እንበል እንዴ? መጽሓፈ መሳፍንት ም. 7 ቁ. 20

ወያኔን የጦርነት መለማመጃ እናደርገዋለን ብለውንም ነበር እኮ፡፡ ለዚህም ደግሞ እንግዲህ እግዚአብሔር በእያሱ ዘመን ጦርነት የማያውቁትን የእስራኤል ልጆችን ጦርነት እንዲለምዱ ከከንአን ሰዎችን በዚያ አሰቀረ…የሚለውን  ከመጽሐፈ መሳፍንት ም.3 ቁ. 1-4 ያለውን ጠቅሰን ላይ ተንተርሰን “ንሴብሆ ለአምለከ አብይ” እንድንል አስበው የተናገሩት ይመስላል፡፡

ይህን ያክል ያተትኩት ደሴና ኮምበልቻ እየተያዘ እያለ እርስዎ የማይሆን ጥቅስ ከወንጌል ሲጠቅሱ ሰምቼ ነው፡፡ ከመጽሓፍ ቅዱስ በመጥቀስዎ ሕዝበ ሞስሊሙን ይቅርታ ጠይቀዋል፣ ጥሩ አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ትልቅ ስህተት ስለሰሩ ሕዝበ ክርስቲያኑንም የበለጠ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል፡፡

አንድ ግዜ እየሱስ ከሐዋሪያቱ ጋር ሆኖ በታንኳ ሲጓዝ ማዕበል ተነሳና መርከቧ ልትሰምጥ ሰትል ተኝቶ የነበረውን እየሱስ ሐዋሪያቱ ቀስቅሰው ስንሰምጥ ግድ አይልህምን ብለው ጠየቁት፡፡ መጽሐፉ እነደሚለው ክርስቶስ መዕበሉን ገሰጸው፣ መዕበሉም ፀጥ አለ፡፡ እርስዎ ሃገር ሲጠፋ እነደክርሰቶስ  መተኛትዎን ባናውቅም፣ ታንኳዋ ውስጥ አብሬችሁ እኮ ነው ያለሁት አሉን፡፡ ነገሩን ወዴት? ወዴት?

እራስዎን በክርስቶስ ትርክት ውስጥ ወክለው መግለጽዎ፣ማለትም እየሱስ፣ እየሱስን መጭወትዎ  ሓሳዊ መሲህነት እንደሆነ አያውቁምን? የስነልቦና አዋቂዎች እኔ አዳኙ ነኝ ፣እኔ አሻጋሪው ነኝ …እያሉ እራሳቸውን በትንቢት የተነገረላቸው ከሚያደርጉት፣ መሲሃዊ የአእምሮ ነውጥ ተጠቂዎች(Meshanic complex) ጎራ እራስዎን እያደባለቁ እንዳይሆን ይጠንቀቁ፡፡ ይህ መቼም የአማካሪዎችዎ የዲያቆን ዳነኤል ክብረትና የዶ/ር ምህረት ደበበ ምክር ውጤት አይመስለኝም፡፡

በፖለቲካ ስነልቦና ላይ በደንብ ሳይንሳዊውን መንገድ ሲከተሉ እመለከታለሁ፡፡ ኢሬቻ በአልን አዲስ አበባ ላይ ያን ሁሉ ቄሮ አስገብተው የአዲስ አበባ ነዋሪን ኪሱን ሲያስበረብሩ ዋሉ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስንም ፎሪ አወጡት፡፡በእርሶም ይሁን በኦቦ ሽመልስ ንግግር የአዲስ አበባ ነዋሪን ለጥቃት የተከበበ ከተማ ነዋሪነት እንዲሰማዉ ፍርሃትን በላዩ ላይ በማንገስ ለእርስዎ እድሜ እየለመነ በጭንቀት እንዲኖር ተግተው ከመሰሎቾዎ ጋር ሰርተዋል፡፡ ፈረንጆቹ ፊር ፋክተር(Fear Factor) የሚሉትን ካርድ ነው የመዘዙት፡፡ የታቀደው ግብ ደግሞ አንደር ሴጅ ሜንታሊቲ(Under siege mentality) በአዲስ አበባ ነዋሪ ላይ መፍጠር ነው፡፡

በእዚህ አካሂዳቸው፣ እርሰዎና ጓደኞችዎ በፓርቲያችሁ ላይ እንኳን አንጸባራቂ ድል አግኝታችሁበታል፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብልጽግና ለእረስዎ ያለው ታማኘት እኒህን ሰው ብንገዳደራቸው በአስር ሚሊዮን የሚቆጠረው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ላይ ጄኖሳይድ ይፈጠራል ከሚል ፍርሃት ነው፡፡ ይንንም በዘመንዎ በሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ-ሻሸመኔ በሰርቶ ማሳያ ፕሮጀክት አረጋግጠውለታል፡፡ የወለጋና ቤኔሻንጉሉንስ ፣ አረ ስንቱ?

የስነ ልቦና ሊቃውንቱ እንደሚሉት እራስን ሁሌ እያኮሰሰ የሚሄድ ታማኝነት ተንበርካኪነት ነው፡፡ ብልጽግና ውስጥ ያሉ የክልል ድርጅቶች ሁሉ ተንበርካኪ ተደርገዋል፡፡ የደቡብ ክልለ ብልጽግና መሪ አቶ ርሰቱ ሰሜን አሜሪካ መጥተው  ለጉራጌመሐበረሰብ የደረጉት ንግግር የእርስዎን ቡድን ማንነት በደምብ ያጋለጠ ነው፡፡

እርስዎ ሲፈልጉ መገንጠል የሚፈልግ ይገንጠል፣ ክልል መሆን የሚፈልግም እንደዛው ይላሉ፡፡ የኦሮሞ ሊሂቃን ደግሞ ጉራጌ በሴም ቋንቋ ተናጋሪነቱ ከአማራ ጋር እንዳያብር እንደ አቶ ርስቱ ያሉ ጉምቱ የራሳችሁ ፖለቲከኞችን እየጠሩ ያስገነዝባሉ፡፡ አያችሁ ርሰቱ እንዳሉት ዲሞክራሲ ምናምን የሚባለው ነገር ውሸት ነው፡፡ ጉራጌው ከአዲስ አበባ ተቆርጧል፡፡ በሌላውም ክልል መነገድ አይችልም፡፡ ዜግነት ባዶ፡፡ ስለዚህም እንደ ሌሎቹ ብሔር ተብለው አንደተጠሩት ሁሉ “ሲርባ ግዲ” ጭፈራ በግድ ተፈርዶበታል፡፡ እንግዲህ ለጉራጌ “አለም ገበረ በዋሻ” ብለን የምናለቅስለት ዱላ በእጁ አዘቅዝቆ ይዞ ጉራጊኛ የጨፈረ እለት ነው፡፡

የጠ/ሚ አብይ አህመድ አገዛዝ ሰልፍ አስወጥቶና በመፈክር አጯጩሆ የጋለውን ህዝብ ስነ ልቦና በሞቀበት ቀጥቅጦና አጣሞ ጉዞ መቀጠልን ያምንበታል፡፡ የስነ ልቦና ሊቃውነት አንዴ ሰልፍ የወጣና መፈክር ጆሮው ላይ ሲጮህበት የዋለን ሰው፣ ይህን ሂደት ከደጋገምክበት በኋላ የማያምንበትን ነገር ብትሰራ እንኳን ወደ ፈለክበት መንገድ ትመራው ዘንድ መንጋነትን ይመርጣል እንጂ ለመገዳደር ይከብደዋል ይላሉ፡፡

የጠ/ሚ ነጯን ያየ፣ ጥቁሯን ያየ ጨዋታ ከትግራይ መካናይዝድ ሙሉ ጦሩን አስረክቦ ሲወጣ ይጀምራል፡፡ ልክ ምርጫው ከተካሄደ በኋላ፣ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላት ሆኗል ስለዚህ የጽሞና ግዜ እንስጠው ብሎ ወጣ፡፡ አይ ጽሞና? ጽሞና እኮ በሰላም ግዤ እራስህን አግልለህ የምታገኘው አካላዊ ሳይሆን መንፈሳዊ የልዕልና ጉዞ ነው፡፡ እንደምናየው በመፎክርና ሰልፍ የተቀጠቀጠው ጎጋው ጀሌ ገደል ማሚቱ ሆኖ ቀረ፡፡ ዲያሰፖራውን ለገና በዓል ወደ ኢትዮጵያ ግባ ያሉት የብልጽግና መሪ፣ ለአመት በዓሉ አቶ ስብሃት ነጋንና ቤተሰቡን ከእስር ለቀቀ፣ ያውም በአምላኩ ትእዛዝ፡፡

አያችሁ ይህ መንግስት ያስብ የነበረው ነገር? በኢትዮጵያዊነት ስም ሰልፍ አስወጥቶ ስለአስፎከራቸው ቅጥቅጦቹ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ አይደለም፡፡ ሔርሜላ አረጋዊ ታላቅ እንቅስቃሴን አድርጋ ነበር፡፡ እውነት ነው ለሁሉም ነገር ፈር አለው “በቃ!” እንቅስቃሴዋም አለም አቀፋዊ ሆነ፡፡ በቤተሰብ ደረጃ ተንቀሳቀሱ፡፡ ጠ/ሚ አብይ ግን እጇን ጨብጠው ጣቷን ቆርጥመው በሏት፡፡ ማነው ታዲያ የኮንፊውዝና ኮንቪስ ጨዋታ ደራሲ? የጠ/ሚ አብይ መጽሐፍ፣ ርካብና መንበርን፣ እስኪ ደግማችሁ አንብቡት፡፡ጠላትን እንዴት በገንዘብ አታሎ ገደል መክተት እንደሚቻል ይጽፋሉ ግን ሙስናን የተጠየፍኩ መሪ ነኝ ይላሉ፡፡

አሁን ደግሞ የትግራይ ተቆርቋሪ ሆነው ብቅ ብለዋል፡፡ ትግራይ ለምን አኮረፈ ብሎ ህዝቡ እንዲጠይቅም ያስገነዝባሉ፡፡ ነገሩ “አንቺ ታመጪው አንቺ ታሮጪው ” ነው፡፡ እርሶ መሰሉኝ ትግሬዎቹ ሲሉ ሰምተው “የቀን ጅብ ያሏቸው…“ ዘመንዎ ደግሞ የቀመሬ ጅብ ግዜ ነው፡፡ ይህ ጅብ የቆዳውን ቀለመ እያሳየ ነብር ነኝ ይላል፡ ነገሩ መጽሓፉ የሚለው “ነብር ዥንጉረጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር ይችላልን?” አይደል፡፡፡ እውነቱ  ግን ትንሽ ቆም ብለው እራስዎን ከአንገት በላይ ቢመረምሩ ይሻላል፡፡ ነገሩ በዚህ ሁሉ ወጀብ ውስጥ አልፈው ጤነኛ ቢሆኑ ነው የሚገርመው፡፡ ማለትም ከወያኔ የስለላ ድርጅት መሪ  ከመሆንዎ ግዜ ጀምሮ፡፡

ገና ከጅምሩም ምልክቶች ይታዩ ነበር፡፡ ዛሬ ራሺያ ተከበብኩ፣ መፈናፈኛ ላጣ ነው በሚል ስሜት ዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት እርስዎ ደግፈዋል፣ የሚሰጡትን የድጋፍ እጅ እስብሰባው ላለመገኘት እግርዎ እንዳይሄድ ከከለከሉት ያው ድጋፍ ነው፡፡ እርሰዎ ግን አዲስ አበቤው፣ ደቡብ ክልል፣ አፋሩ፣ ሱማሌው..የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ዙራዬን ተከብቤለሁ ብሎ እንዲያስብ ለሚያገለው ፖለቲካ በር ከፋቹ እንደነበሩ ማስታወስ የሚፈልጉ አይመስልም፡፡

ከቡራዩ የተነሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቤተመንግስት ሄደው እርሰዎን …ሊያደርጉ በነበረበት ግዜ፣ አንድ ነገር ተናገሩ፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለ ሁሉ(ኦሮሞ) ማለትዎ ነው፣ መንግሰታችን ተነካ ብሎ ወደ ከተማው በመግባት ለታላቅ ደም መፋሰስ ተዘጋጅቶ ነበር አሉ፡፡ ቀጥለው፣እስክንድር ነጋ  አዲስ አበቤዎች በሚል መርህ ባልደራስን ሲያቋቅም፣ ዘራፍ እንጋደላለን አሉ፡፡ ጀዋር ንግግርዎትን ተከትሎ ኮዬ ፈጬ ኮነዶሚኒየም ላይ ወጣቶቹን ሰብስቦ ዱላና ገጀራ በማሲያዝ ቄሮ አላችሁ ወይ ሲል ተሰማ ፡፡ ከተፈለገ በግብግብም እንደማይቻል አስታወቀ፡፡  የእሱ ንግግር ከእርስዎ የሚለየው፣ ንግግሩን ያደረገው አዲስ አበባን ከኦሮሚያ ክልል በሚያዋስነው ቦታ ላይ  መሆኑ ነው፡፡

ጀዋር አብዮቱን እኔ አምጥቼዋለው ብሎ ስለሚያስብና ከጅምሩም የለማ ደጋፊ ስለነበር ድምጾትን ነጥቆ ማስተጋባት ነበረበት፡፡ ዛሬ የነ ቲም ለማ፣ ገዱ ነገር ሁሉ ጠፍቶ እንደነገሩን  እርሶ አንድ ነገር ቢሆኑ በመቶ ሺህ ሰዎች እንደሚያለቁ ህዝቡ እያሰበ ፈርቶ እንዲኖር አድርገውታል፡፡

አሁን ለኢትዮጵያ አንድ ነገር ማድረግ የሚችሉ ይመስለኛል፡፡ በመጀመርያ ፀረ ዲፐሎማሲ አካሄድ የሚሄዱ ሰዎቸዎን ያስታግሱ፡፡ አንደ በደርግ ግዜ አሁን ኦሮሚያ ክልል ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የነበረ  ገበሬ መሐበር የአሜሪካ ኢምፔሪሊዝምን አስጠነቀቀ ፐሮፓጋንዳ ሲያስነግር በሬዲዮ ሰምቼለሁ፡፡ አሁን ደግሞ፣ ኮርማው የኦሮሚያ ፕ/ት የነቀዘ ስንዴቸውን አንፈልግም አንዳለው ነገሩ ቀላል አይደለም፡፡ እኛ በውጭ ያለንው፣ እንኳን የነቀዘውን፣ ያልነቀዘ ስንዴቸውንም ቢሆን አንፈልግም፡፡ እራሳችንን መቻል ነው የምንፈልገው፡፡ ግን እኮ አሁን ምስኪኑ የኦሮሞ ወገን አርሶም ይሁን አርብቶ አደሩ ህዝባችን እርሀብ ላይ ነው ያለው፡፡

ለባሌ ህዝብ ሄደው ብልጽግና የተመሰረተው  ወያኔን ለማባረር ነው ብለው ነግረውት ነበር፡፡ በርግጥ ንግግሩ ይመስላል እንጂ ግልጥ አይደለም፡፡ ግልጽ አይደለም ያለኩት “የሰበሩንን ሰብረናል…” ያለው የኦቦ ሽመልስን ንግግር ይዤ ነው፡፡ ትግሬውንም አማረውንም… ማለት ይመስላል፤ ያውም በደምብ፡፡ ከኢህአድግ ውስጥ መጀመሪያ ጌታችሁ ወያኔን፣ ቀጥሎ ብአዴንን ከዚያም ደቡብ…ማን ቀራችሁ ሁሉንም አገዳ አገዳዉን እያላቸሁ የወንበር ላይ ልምሽ አድርጋችሁታል፡፡

አንድ ወለዬ ዘመዴ ወሎ በተወረረበት ግዜ የነገረኝን ግጥም ፌስቡኬ ላይ እንዲህ ብዬ መጻፌን አስታውሳለሁ፡፡

አልሰሙም ንጉስ?                                                                    አልሰሙም ጌታ?                                                                      የኔ ዶሮ ሞታ፡፡                                                                   አንጀቴ ማረሩ ሆዴ መንጫረሩ፣                                                      የጎረቤት ዶሮች ከደጄ ሲጭሩ፣                                                           ስጤ ላይ ሲዳሩ፡፡

አሁን ደግሞ እንዲህ አለኘ፡፡ የዚህ  ሰው  መንጋ ተከታዮች፣ አብይን ማለቱ ነው፣ ፋጢማ ፋጤን ይመስሉኛል፡፡ ፋጢማ አደም የሚባል ባል ነበራት፡፡ አደም ሯጭ ነኝ ብሎ ደሴ እስታዲየም ገባ፡፡ ገና ፊሽካው እንደተነፋ ተፈትልኮ ወጣ፡፡ ፋጤ ምን ብትል ጥሩ ነው? አዴም ቀደመ፣ አዴም ቀዴመ… ከአራት ዙር በኋላ ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች  ደረሱበት፡፡ ፋጤም ቀጠለች አዴም ፈተናቸው፣ አዴም ፈተናቸው… አልፈውት ሲሄዱ ደግሞ፣ አዴም አሳዴዴ አዴም አሳዴዴ ሆነ ነገሩ፡፡

አሁን ደግሞ አንድ ወሎ ውስጥ ያለ ገብርኤል ቤ/ክ የሆነ ታሪክ ላካፍላችሁ፡፡ አቃቢቷ የመገበሪያውን ስንዴ ለማዘጋጀት ሲሄዱ ነቅዞ አገኙት፡፡ ስጋወደሙ ለሚፈትቱት ካህን ሄደው አረ የመገበሪያው ስንዴ ነቅዟል አሏቸው፡፡ መልሱም አውጥተሸ ወርውሪው ሆነ፡፡ እንዲያም ሆነ፡፡ ጆሮ ያለው ይሰማ እንዳንል፣ የዘር ማልያ ለብሶ ለግል ስልጣኑ የሚተጋው ፖለቲከኛን ሁሉ የብሔርተኝነት ኩክ ጆሮውን ከደፈነው ቆየ፡፡

ሌላው ኦሮሚያ ሀብታም ነች የምትሉትን ነገር ቀንሱት፤ ከኮንጎና ከሴራልዮን ተማሩ፡፡ ያለ በለዚያ ህዝባችንን ለከፋ ጦርነት ነው የምትዳርጉት፡፡ ለነገሩ ትግራይም፣ አማራዉም …በጣም የከበረ ታሪክና በተፈጥሮ ሃብትየተባረከ መሬት ነው ያለው፡፡ ቆንጆዋና እድለቢሷ ኤርትራም በረከቶቿን በዶማ ቆፍራ አላወጣችም፡፡ እድለቢስ ያልኳት በረከትም ሆነ መርገም ከ15ኛው ክ/ዘ ጀምሮ ለኢትዮጵያውያን ቢመጣ በዚያው በወደብ ነበር ብዬ ነው፡፡ ታሪካችንን እንመርምር፡፡ መዳረሻ ሆኖ መፈጠር መች በረከት ሆነላትና?

በምስራቅ አፈሪካ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ኃይሎች በየሃገሩ ጉች ጉች እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሐገራቱን ለኢንቨስትመንት ምቹ አያደርጉም፡፡ ወደፊት ለመጓዝ በፊውዳሊዝም ግዜ የነበረን ታሪክና ፖለቲካ በአሁን ዘመን ባለው ፖለቲካ እየመዘንን አንንዘባዘብ፡፡ ያለበለዚያ አዲስ ነገር አይመጣም ያው የፊሽካ – ፊሽካ ነፊ መሆን ነው ትርፉ፡፡ ያውም ተመዝነው ቀለው እንደ ገለባ ወደ እሳት እስኪወረወሩ ግዜ ድረስ፡፡                                                                      ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!! ወደፊት! ፉንዱረኒ!…ትግላችን ይቀጥላል…

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮቫንኩቨር ካናዳ


Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop