April 2, 2022
5 mins read

የዊል ስሚዝ ጋጠወጥነት እና የክሪስ ራክ ንፅፅር ተገቢነት! – አሰፍ ሃይሉ

277527752 4962830707105356 2944035882602330593 nጂአይ ጄን ታዋቂዋ የፊልም ተዋናይት ዴሚ ሙር የልዩ ኃይል ወታደር ሆና የምትተውንበት ፊልም ነው፡፡ ሁልጊዜም ለየት ማለት የምትወደዋና ራሷን የወጣላት ምሁርም አድርጋ የመቁጠር ዝንባሌ የሚታይባት የዊል ስሚዝ ሚስት ጃዳ ፒንከት ደሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፀጉሯን እልም አድርጋ በመላጨት የጥንታዊ አፍሪካውያን ሴት ነገሥታትና ጣዖቶችን ከመሰለች ቆየች፡፡ በሚዲያ አፐሌሺያ የተሰኘ ፀጉሯን የሚያረግፍ ህመም ተጠቂ መሆኗም ሲነገርላት ቆይቷል፡፡

ኮሜዲያኑ ክሪስ ራክ ታዲያ በኦስካሩ ሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ይቺን በእውነትም የዴሚ ሙርን ጂአይ ጄን የመሰለችውን ጃዳ ፒንከት – ፀጉርሽ ጂአይ ጄንን አስመስሎሻል፣ ይመችሽ፣ ከልብ እወዳችኋለሁ ብሎ ሲናገር፣ ንፅፅሩ ሳቅን የሚያጭር በመሆኑ ሁሉም ሲስቅ ነበር፡፡

በሚስቱ የአዕምሮ ቁጥጥር ሥር እንደዋለ ለብዙ ጊዜ ሲነገርበት የቆየው ጅሉ ዊል ስሚዝ ታዲያ በቀልዱ አብሮ ሲስቅ ከቆየ በኋላ የሚስቱን ፊት መለዋወጥ ሲመለከት – ከተቀመጠበት ተነስቶ በመድረክ ላይ የነበረውን የብዙ ዓመት የሙያ አጋሩን ክሪስ ራክን በዓለም በቀጥታ ለሚሊዮኖች በሚተላለፍ መድረክ ላይ በጥፊ አጩሎታል፡፡

ብዙዎቹ ‹‹ሴት የላከው…›› ብቻ አድርገው ወስደውታል፡፡ ብዙዎች ቀልድ እየተተወነም መስሎን ነበር፡፡ የሆነው ግን በጣም የሚገርምም፣ የሚያሳዝንም፣ ለማመን የሚከብድም ጋጠወጥነት ነው፡፡ ከስነምግባሮች ሁሉ የወጣ አስፀያፊ ተግባርን በአደባባይ የፈጸመውን ሰው ደግሞ፣ በዚያው መድረክ እያጨበጨቡ ኦስካር ሸለሙት፡፡ የባለጌዎች ጉባዔ ይህን ይመስላል፡፡ ዓለማችን ምን ዓይነት የሞራል ልሽቀት ደረጃ ላይ እንዳለከች ከዚህ የበለጠ ማሳያ ያለ አይመስለኝም፡፡

ልክ ዊል ስሚዝ ቀልደኛውን ክሪስ ራክ ተነስቶ በጥፊ ሲመታ የታየኝ፣ ሌላ ሰው፣ ሌላ ነጭ ሰው፣ ቢሆን ዊል ስሚዝ ይህንን ዓይነት ፀያፍ ድርጊት ይፈፅም ነበር? ብዬ ነው ራሴን የጠየቅኩት፡፡ በፍጹም አያደርገውም! የዊል ስሚዝን ጋጠወጥ ድርጊት ስመለከት የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤ ናቸው ትዝ ያሉኝ፡፡

የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ‹‹ከሀገራችን ውጡልን!›› ብለው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ወደ ደቡብ አፍሪካ የመጡ ጥቁሮችን በላያቸው ላይ የመኪና ጎማ አጥልቀው፣ ቤንዚን አርከፍክፈው ከነነፍሳቸው ሲያቃጥሉ ሲመለከቱ፣ ሙጋቤ በጣም ተበሳጭተው የተናገሩት ንግግር ነው የመጣብኝ፡-

‹‹እነዚህ ደቡብ አፍሪካውያን እኮ እንግሊዞች መቶ ዓመት ቀጥቅጠው ሲገዟቸው፣ እንኳን ካገራችን ውጡ ብለው ነጭን ሊያቃጥሉ ይቅርና፣ ቀና ብለው ለማየት ሲንቀጠቀጡ ነው የኖሩት፣ ዛሬ አንድን ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ ጠርተህ፣ እንኳን በህይወት ያለ ነጭ ሰው ይቅርና፣ የሞተን የነጭ ኃውልት ምታ ብትለው ሀሞቱ የለውም፣ ጥቁሮችን ግን ከነነፍሳቸው በቁማቸው ሲያቃጥል ታየዋለህ፣ ይሄ የመጨረሻው ወራዳ የባርነት አመል ነው፣ እንጂ ከሀገር ፍቅር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም!››

ዊል ስሚዝ፣ ክሪስ ራክን በዓለም ፊት በጥፊ በመምታት ራሱን ነው ያዋረደው፡፡ ጋጠወጥነቱን ነው ያስመሰከረው፡፡ ሚዲያ ያገነናቸው ያልበሰሉ ሰብዕናዎችን ጉድ ነው ለዓለም አውጥቶ ያሰጣው፡፡ አሳፋሪ ብልግና ነው፡፡ ግን ብልግናው – ተራ ብልግናም ብቻ አይደለም፡፡ ሙጋቤ እንዳሉት – የባርነት መንፈስ የወለደው ብልግናም ጭምር ነው፡፡

Hats off to Chris Rock!

ጋጠወጥ አስጠላኝ!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop