መኳንንት ታዬ (ከሚኒሶታ)
ዘመናት አፍ አላቸው ፤ይጣራሉ፤ እስትፋሳቸው እና አንድያ ነፍሳቸው በትውልድ እንቅስቃሴ መውጣቱና መውረድ ይገለፃል።ይፈነትዋሉ። ምን እንኳን አሮጌ ሥርአት አርጅቶ ወድቆ ሞቶ አዲስ በምትኩ ቢያብብ፤ያ ትውልድ ይሄ ትውልድ በቅብብሎሽ ከሚያቆዩት አንዱ ነገር ትላንትናን መጣልና ዛሬን መከተል ላይ ነው።መጣል እንደምንድነው ለሚለው ቅብብሎሽን መርሳት ሳይሆን መልካሙን በመደገፍ መጥፎን በመንቀፍ መሆኑን ለማያያዝ ነው።ይኼም ብቻ አደለም፤ በሥርአትና በሥርአቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ማህበረሰብ ከመሆን በጠበበ ሁኔታ የአንድ ቤተሰብ ሠዎቸ ይሆኑና ትላንትና በኛ ግዜ ዛሬ በእናንተ ግዜ በማለት ቅብብሎሹን የጋራ ወደ ማድረጉ ሲያዘነብሉ ይስተዋላሉ፡ በዚህም መንገድ የአበብዮሽ(የሽብረቆሽ) ዘመኖችም አሉ።አንዱን ሲያስደስቱና ሲያሸበርቁ እና እነሱን ለሽግግር ያበቁ እተሰቀለው ላይ ሰቅለው ከሩቅ ለመታየት ምክንያት ሆነው በዙር የሚጠቀሙበት መንገድ ሲፈጥሩ ይታያል። ይሁንና እነዚህም በውበት ለሚቀጥለው ትውልድ በማስተላለፍ ትላንትን ያየንበት እንደሆነ ለነገ የሚበቃ እናተርፋለን።”የሗላው ከሌለ የለም የፊቱ” እንደተባለ ሁሉ። ነገር ግን በፍለጎትም ይሁን ያለፍለጎት ግድ በሆነ ምክንያት …..ተሰብረው በመውደቅ ሁነቶችን ሲያኮላሹት ይታያል።ይህ ደግሞ አከባቢውን ፀጥታ ቀዝቀዛ ያደርገዋል።
ይሁንና ለዛሬ በመረጥኩት ርዕስ ከላይ የጀመርኩት ከሰል ያለቀበት ባለ እጅ ሆነናል። በዚህ ሌላ ምክንያት ሃገር ታሪክ መንገዱን ይስታል፤ ጠፋ የሚባል ነገር ይበዛዋል መተማመንና አብሮ መክረም በስስት የሚታይ አንዳች እሩቅ ነገር ሆኖ የታያል። ይሁንና ለዛሬ በመረጥኩት ርእስ ጉዳይ የዘመኑን ተጠቃሚ እኛስ በየት አፈተለክን የሚለውን በግራ የዋልንባቸውን መንገዶች ለማት እንሞክራለን።ባለ ብዙ ፈርጅና ውልድ በየማዕረጉ የተቀመጠው የሠው ልጅ በጠባቧ የኢት/መሬት ላይ ለ እናት ሃገሩ ከምን ጀምሮ ምን ላይ ደርሶ እርባን እጣ ምንስ እንበለው ለሚለው ትርጓሜ አንድ ህዝብ ለአንድ ሀገር ህዝቧም(ልጇም) ነውና እስከምን ድረስ ያድግላታል ወይስ ያድግባታል? የሚለውን ለማየት የስራውን ትርጓሜ ማየት አለ አንድምታ መግባባት ላይ ለመድረስ ያስችላል።ይህን ትርፋማነት የሌለው ኩነት የሚፈፅምና የሚያስፈፅም ትውልድ በመጥፋቱ ቅዝቃዜው በዛ፤ ትካዜው እና ነገን ማየት አሩቅ ሆነ ምክንያቱ ደግሞ እንደባላ እጁ ከሰል አልቆብናል፤ጨርሰነው ቢሆን ሰርተንበት ነበር ግንሳ ግን ሆነ።
በሌላው ጉዞአችን መሬት የያዙትን አንኳር ቁም ነገሮች አንስተን በዚህ እርስ እንፈትሽባቸው።
ለምሳሌ የሚሆነውን እንደባተሌ ቀሚስ የሚጎተቱትን ፖለቲካችንና በሃይማኖቶቻችን ላይ ጥላ ሆነውን በሗላ እግራቸው የሚቀዱት በበዛበት ሁነት ሐይማኖት መመሪያችን ፖለቲካም አስፈላጊያችን ነውና እንጠቀምበት ስንል ጎዶሎው እየበዛ የሚነሳለት ጥቅም ጠፍቶ በየደጃፉ ጩኸትን እየፈጠረ በመሆኑ ጥቂቶች ጥለው ሰበሩት መኖሪያችን የሆነውን ከሰላችንን ጨረሱብን እንጂ እኛ አልጠቀምንበትም ግን እሳ ፤ብዙዎች እንደምን ተጎዱበት ብለን እንየው።
የፖለቲካው ምህዳር ወድቆ ለመሰበርም ስሎ ለመስበርም አርዳታ በማይፈልግበት መልኩ እራሱን ያዘጋጀ በሚመስል መልኩ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ትውልድን ሲያወክብ እንደምን እየመታ ወርቀዘቦ የሆነውን ባለግዜ በመግባባትም ባለመግባባትም በየቦታው እያረገፈው ባለበት ዘመን ተጠቃሚው ማነው? የሚለውን ለመመለስ ደራሲውም ተደረሲውም በወከባ ላይ ባሉበት በዚህ ግዜ በድካም እርዳታ የማይለምን የለም። ደራሲው ትወናውን ተቀበሉ ሲል፤ ተደራሲው እኛን አይመጥንም ከዚህ በፊት በተተወኑት ትይንቶች ኢትዮጲያዊያን ለመቀበል የተቸገሩበት ዘመን እንዲህ እንዳሁኑ አለየንምና ሲሉ።ስለዚህ በሗለኛው ዘመን ከነበሩት የፖለቲካ ፍጥረቶች ይሄኛው ልጅ ከሰሉ ያለቀበት ባለ እጅ ስለ መሆኑ ምንም ማስተባበያ የለውም።
ሃይማኖት ደግም ከዚህ አሰከትለን እንየው፤በዚህ ጥልቅና ሰፊ ሚስጥር የታጠረ ባህር ውስጥ እልፍ እለፍ ክንውኖች ቢኖሩቱም በቀደምትነት የክርስትና እስልምና ተብለው በኢ/ት ስለመኖራቸው ጥርጥሩ እንዳለ ማሰቡ ተጠርጣሪ መሆን ብቻ አይገልፀውም።ግን ወደ ቁባችን ስንገፋ በክርስትናው መስመር ባለችው ታላቁ የኢ/ኦ/ተ/ቤ አባቶች ልጆች ቢኖሩአትም ሁሉም የራሱ ድርሻ አለውና እንዲህ ብለን እንጀምረው።
ባለበዙ አባቶች የሆነችም ይህቺው ቤ/ክ በጠንካራነቷና ቀደምትነቷ ባለብዙ ታሪክ ብትሆንም ቅሉ ከትላንቱ የጀመረ ዛሬ ድረስ እየታመሰች ለፖለቲካው ክንድ ጭንቅላታቸውን ያስደግፉ የሃይማኖት አባቶች በመፈጠራቸው ስርዐቷ እንዲጣስ ቅጥሯ እንዲገረሰሰ ከማድረጋቸውም ባሻገር የነገን ታሪካቸውን ምን ሊሆን እንደሚችል ያላወቁ መሪዎችና ተመሪዎቻቸው አማካይነት የብዙሐኑን እና ትልቁን ጥያቄ ጨፈለቁት፤ እነሱ መራጭ እነሱ ተመራጭ፤ እነሱ ተሿሚ እነሱ ሿሚ ብቻ ሁሉም እነሱ ሆነው ለነገ ብለው የምንሞቀወ ላያስቀሩልን እራሳቸውን አዳምጠው እራቸውን በዳይና ተበዳይ አድርገው ክሰላችንን ጨረሱብን፤ እኛም አለቀብን። በሔድንበት ቶሎ ይበርደን ጀመር ይቀዘቀዝን ጀመር ለምን?ለቤተከርስቲያን ወይስ በቤተከርስቲያን?መልሱን ነገን ለማየት እንዳይችሉ ዛሬ እነሱነታቸው በልጦባቸው አድራጊ ፈጣሪ ለሆኑት ይሁን። እኛ ግን ከሰሉ ያለቀበት ባላ እጅ ሆነናል። ግን አስከ መቼ ለሚለው ቃል መልስ ሊሆን የሚችለው አዎ ጨርሻለሁ ብሎ አለመቀመጡ በመጀመሪያው መስመር ላይ የተቀመጠ የመጀመሪያው ነጥብ የዘመኑ ባለማስተዋል የሆነ ትውልድ ጥያቄ ነው።መልሱ የሚፈለገውም አሁን ነው። የሚጠፋው የበዛው ዛሬ ነው ።ሃለፊነት እየጎደለን የመጣው የዛሬዎቹ እኛ ነን።የሚፈርስ የሚከለስ በዛ።ልዩነት አለመደማመጥ ማየላቸው በዝቶ ክፍተቱን ለመድፈን የሚደረገው እሩጫ ለክፍተቱ ምክንያት የሚሆኑ ምሰጉን ያልሆኑ ምክንያቶች ከአቅም በላይ ሆነው መገኘታቸው እውነትም ከሰሉ ያለቀበት ባላ እጅ ለመሆናችን ምንም ጥርጥር የለውም።
ልብ እንበል ሃገራችን ህዝቦቿ በየደጃፋቸው የሚያስተናግዱት መከራ ቁጥሩ የትየለሌ ነው ።በነፃነት ማጣት ድሎት ውስጥ ሃሳባቸው የሗሊት እየተጎደደ የትንፋሻቸው ልኩ እንደ ደም ግፊት እየተለካ ከፍ ብሎአል ዝቅ በል ተብሎ እየተነገረው ባለበት በዚህ ግራ ግዜ ግራ አጋቢው ነገር በነፃነት የሚኖሩ ወገኖች የራሳቸውን ከሰል የጨረሱ ባለ እጆች ያሉበትን ቦታ ለመለየት አዋቂነትን አይጠይቅም።ማስረጃን የሚሻ ከሆነ ግን በየደጀ ሰላም የሚደረገው ሁከት ልኩን ለማወቅ ያህል ሳይበቃ እንዳልቀረ እገነዘባለሁ።የሚገርመው ታሪክ የሁከት ቦታዎች በባለቤታቸው ሰላም ያገኛሉ፤ ምድራዊው ምድራዊውን ይፈራዋልና።ለሰማየዊ ህይወት ሰላም ለማግኘት ሰላም ለማለት የሚሄዱ ግን ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክን ተዳፈረው ከሰላቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፤ትርፋቸው ምን ይሆን?እነሱ ያቁታል።ችግሩ ግን እነሱ ትርፋማ ስለመሆን አለመሆን አልነበረም ፤የተሰጣቸውን የሰላም መንደር ለእሪታ መጠቀማቸው ከቶ ምን ይባል?በሃገር እና በሀገር ውስጥ ካለው ጋር እራሳችንን ስናወዳድረው እኛን(በተለይ ደግሞ በሰላም ሃገር የምንገኘው) በየትኛው ደረጃና መስመር እናሰቀምጥ?ከሰሉን የጨረሰ እና የተጨረሰበት ማንኛውም በእጅጉ ሁነቶችን በጥሞና ለማዳመጥ እና የራሱን ሰላም መጠቀምይችል ይሁን?እውነቱ አንድና አንድ ነው። ያውም ለቤተክረስቲያን ሳይሆን በቤተከርስቲያን መሆኑ ነው።ይህ ላንባቢ ልተወውና ወደማጠቃለያ መዝለቂያ ልንጎድ
በጥቅሉ የምንመራበት መርህ ደረጃውን እንዲጠብቅልን የምናደርገው ሁሉ ትክክል እንደ ሆነ የምናምን ከሆነ የሚደረግበት ሌላው አካል የጉዳቱ ቁጥር ብዛቱን ብሎም ለነገ የሚቋጥረውን መገመት አስቸጋሪ አደለም።ነገር ግን ችገሩን የመፍጠር ያህል ችግሩን የመቅረፍም ሆነ ለነገ አለማዘዋወር ቀላል አደለም ።ስለዚህ ነው ለመኖር የተፈቀደለትና ነገን በስራው ማየት የሚመኝ ትውልድ ራእይ የሚተረጎመው በጠብና በብጥብጥ መሆን እንደሌለበት ሁሉም የሚስማሙት።አጠፋ ብለን የምንወቅሰው አካል ካለ እኛ ከሱ የተሻለ የምንሆንበት መለኪያ የተሻለ ጥፋት ሰርተን ከሆነ ከሰላችን ያለቀብን ሳንሆን እኛው የጨረስን ነን።እኛ ሰለሞችና ሰላማውያን ሆነን ከተገኘን በልማት የምነሸፍነው መንደር ለጎጥ እና ለጎስኝነት ብሎም ለስርአት አልበኝነት አረም አረንቓ በመሆን እድገቱን እንገድባለን።መስመራችን በብርሃን ፍጥነት ተለውጦ በምክንያት ለምክንያት በጠብ የምንወዛወዝባቸውን መንደሮች እና መንገዶች ብርሃናዊ በሆነ መሃንዲስነት ካልቀየስነው እንደ ራሃባችን ሁሉ በጥባጭ እና ተበጥባጭነታችን በ እኛ ስም ለመዝገበ ቃላት ሳይቀርብ እንደማይቀር ማስተዋል የራሳን እና እራስን አለማወቅ ሆኖ እናገኘዋለን።
ቸር እሰንብትS