አይደለም የአገራዊ ጉዳዮችን ሹመት ለመስጠት የተሰየመ ገዥው የብልጽግና ፖርቲ አይደለም በአንድ ተራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የክፍል አለቃ ምርጫ እንኳ አስመራጭ ተመራጭ የሚሆንበት አሰራር በእኔ የህይወት ልምድ አላየሁም።
የበሻሻው አራዳ ምን ተፍረቱ ተመራጭም አስመራጭም ሆኖ እንደ አዋቂ መድረኩ ላይ የስብሰባውን ታዳሚዎች መካሪና ገሳጭ ሆነውና እንደ ተመራጭም ያለ እፍረት መቅረባቸው ሁሉንም በበሻሻ ስነ ልቦና የማሰብ ያህል ነው ያየሁት ፤ ከተሰበሰቡት ታዳሚዎች መካከል አስመራጭ ኮሚቴ ለማስመረጥ ልቦናቸው ስላልፈቀደ ብቻ የበሻሻው አራዳ ብልጣብልጥ “ከእኔ በቀር ላሳር” የሚመርጧቸውን ቀድመው አዘጋጅተው” ለፕሬዝዳንት ብለው ወደ ታዳሚዎች ሲያቀርቡ “ቆይ ብዙ እጅ በዛ” ብለው” አዲሱ የሲዳማ ፕሬዚዳንት” ብለው በራሳቸው ቀመር የራሳቸውን ስም ሲጠቆም ሲሰሙ እውነት ሁሉም ሰው “የኦሮሞ” ሜንታሊቲ ያለው ይመስላቸው ይሆን?
አኔ በጣም ነው የፈርኩት። አስመራጭ እሳቸው፣ ተመራጭም እሳቸው ፤ግን ምን ያደርጋል ለምንድነው እርስዎ አስመራጭ የሚሆኑት? ብሎ የጠየቀም አንድም እንኳ ታዳሚ አላየሁም። አስመራጭ እኮ በቀድሞ ልምዳችን አይመረጥም ወይም ገለልተኛ አካል ነው የሚሆነው ብሎ የጠየቃቸው ማንም የለም። እዚህ ላይ ነብስ ያለው እኔ አልፌ ሀቁን ተንፍሸ መስዋዕት ልሁን የሚል አንድም ኢትዮጵያዊ አላየሁም ።
መኖሩ ለምን እንደሚጠቅመው አላውቅም ግን ዝም ማለት መልስ ነው?
በአጠቃላይ ምርጫው የውሸት መሆኑን ታዝቤአለሁ።
ሌላው አማራ በዚህ ጦርነት ተጎጅ ሆኖ ሳለ ለአማራው የቀኝ እጅ የሆነውን ፋኖ መሸለም መወደስና መመስገን አለበት ያሉ የአማራ የቀድሞ አመራሮች ልብ ገዝተው ህዝቡን ሲቀላቀሉ ከአማራም ሆነ ከአብይ መንበር ተፈናቅለው ቦታ እንዳጡ አይተናል።
እኔ ይቅርባችሁ የምለው በትዕቢት የተወጠሩ ተረኛ ኦነጋዊያንን ነው። ከጠቅላዮ ጀምሮ በተዋረድ የተዘረጋው የፋራ ኔት ወርክ አብሮ ለመኖር አያስችልም ሽመልስ አብዲሳ አዲስ አበባ ተሻግሮ እዝ የሚሰጥበት አውድ ከኦሮሚያ ለአዲስ አበባ ከተማ የማይመጥኑ ከንቲባ የሚሾምበት ለእኔ ግልጽ አይደለም።
አሁን ደግሞ 50,000 የፖሊስ ሰራዊት ለአዲስ አበባ ከየት?
ይህ የእናንተን አይነት ሰዎች ሊያሳምን ይችላል ነገር ግን የአዲስአበባ ተወላጆችን አያሳምንም የቅርብ ጊዜ ትውስታችን አዲስ አበባ “ከርሷን ሞላታ ፈርሷን ለኦሮሚያ ” ብሎ የተናገረው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሚሰራው ለኦሮሚያ መሆኑ ገሃድ ወጥቷል ። የአዲስ አበባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኖ ሳለ ነገር ግን የሚጮኸው ለኦሮሚያ ነው። ይህ ከሆነ ቄለም ወለጋ መሔድ እንጅ አዲስአበባ መጥቶ ያልሰልለጠነ አንደበቱን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የማይመጥኑ ቃላቶች የሚያወራበትና ያልተሟሸ አፉን የሚፈታበት መሞከሪያዎች አይደለንም።
እኛ የአዲስ አበባ ተወላጆች በሰለጠኑ የአዲስ አበባ ተወላጆች ውክልና ተሰይመን ከተማችንን ማስተዳደር መብታችን መሆን አለበት።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ምልመላ ለአዲስ አበቤዎች መሰጠት አለበት። አስታወሱ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንጅ ሌላ አይደለችም እንደማንኛውም ክልል ከተማ ነች።
የፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎች ሊውጣጣ ይችላል የአዲስአበባ ፖሊስ ግን ከአዲስ አበባ ብቻ ሊመለመል ይገባል ።
የእነግ ተረኝነትን በጥብቅ አወግዛለሁ!