March 15, 2022
2 mins read

ትኩረት እና ድጋፍ ለአማራ ልዩ ሀይል ተከዜ ብርጌድ! – ያሬድ አላዩ

275995938 344382774266766 5152535491132124400 n 1ፍየል በግርግር….እንዳይሆን እንጠንቀቅ ለመሆኑ 3 ወር ሙሉ ደሞዝ የተከለከለውን እና ሎጅስቲክ ያልቀረበለት የአማራ ልዩ ሃይል ጥያቄውን ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን ያቀረቡትን ሃይሎችን በሌላ ሃይል በማስከበብ ወንድማማቾን ደም ለማቃባት መጋጋጥ ምን አይነት እብደት ነው እረፉ ብለናል።
ለማንኝውም በአማራ ልዩ ሃይል ላይ የታቀደው ሴራ እጅግ በጣም ከባድ ነው! የልዩ ሃይል አመራር እና አባላት ይሄን ጉዳይ ብስለት በተሞላበት መልኩ በመያዝ ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ በታላቅ ትህትና ለመጠየቅ እንወዳለን! ፋ*ሽስቱ የአብይ አህመድ መንግስት እቅዱ ልዩ ሃይሉን ማፍረስ መሆኑ ከልዩ ሀይል ተገፍተው የወጡ የጦር መኮንኖች አስረግጠው ተናግረውዋል በመሆኑም በዚህ አጋጣሚ ልዩ ሀይል የማፍረስ እቅዱን እንዳያሳካብን መጠንቀቅ አለብን !
በነገራችን ላይ የአዲስ ዘመኑ ግርግር በእቅድ የተያዘ እንጅ ድንገተኝ ክስተት አይደለም!!ዋና አላማውም በፖለቲካ ሴራ እና አሻጥር አልዳከም ያለውን የአማራ ልዩ ሃይል በኢኮኖሚ ምክንያት መበተን ሲሆን ከዚህ በተጓዳኝ ከዚህ የሚከተሉትን ዝርዝር እቅዶች ያሳካል ተብሎ ይታመንበታል!
1) በዚህ ግርግር መሃከል ወልቃይትን ለትህነግ መስጠት
2) አዲስ አጀንዳ በመስጠት የትኩረት አቅጣጫ በመቀየር የፖለቲካ ባላንስ ማሳት
3) እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት በዚህ አጀንዳ ማዳከም
4) ልዩ ሃይሉን ስልታዊ በሆነ መንገድ ማፍረስ
#ተማፅኖ በአካባቢው ያላችሁ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ወጣቶች ወንድሞቻችሁ ላይ ምንም አይነት ነፍጥ ባለማንሳት ፍፁም ወንድማዊ አጋርነታችሁን አሳዩ አደራ አደራ አደራ!!
#ክብር_ለጀግናው_የአማራ__ልዩ_ሃይል!
ያሬድ አላዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop