November 13, 2021
16 mins read

ወሳኝ ጥያቄዎች ለአብይ አህምድ አፍቃሪዎች – ሰርፀ ደስታ

abiy 1ዛሬ በአገራችን እየሆነ ያለውን እንዳይሆን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ልንሰጥ የሞከርን ጥቂትም ብንሆን ነበርን፡፡ ሆኖም በሴራ አድጎ በሴራ የጎለመሰ ቡድን የገዛ ሴራው ይዞት እስከሚጠፋ ድረስ እንዳያስተውል የገዛ ክፋቱ አእምሮውን ያጨልምበታል፡፡ ታላቁ ፈላስፋ እግዚአብሔርን (እውነትን) ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን ለማይረባ የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡ ይሄ የፈላስፋው ንግግር ሁሌም ይገረመኛል፡፡ ከኖህ ዘመን ጅምሮ ሰዎች ሞታቸው ከፊታቸው ቀርቦ እያዩ እንኳን እንዳያስተውሉ የሆኑበትን አንብበናል፡፡ ዛሬ በአገራችን እየሆነ ያለውን ሳሰብ እጅግ ይገርመኛል፡፡ እየገረመኝ ያለው የሴራው መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አጫፋሪዎቹ ናቸው፡፡ አብይ አህመድ ኢትዮጵያነና ኢትዮጵያዊነትን ስልጣን ከያዘባት ቀን አንድ ጀምሮ በተግባር እያጠፋ አይናችን እያየ ብዙዎች የሚያዩትን የአብይ አህመድ ጸረኢትዮጵያዊነት እውነት ሳይሆን በአብይ አህመድ አዚም ተለክፈው የማይታየው የአብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነት በግድ ለማየት የፈልጋሉ፡፡ እስኪ ልቦናችሁ ጭላንጭል ነገር ቢኖረውና እወነት ወደ ውስጣችሁ ቢገባ የሚከተሉትን የአብይ አህመድ ኢትዮጵያን የማፍረስና የኦነጋውያንን ሥርዓት የመተካት ሴራዎች በጥያቄ መልክ ላቅርብ ላቅርብ፡፡ እንግዲህ የማነሳቸው አብይ አህመድ በቀጥታ ራሱ ያደረጋቸውን ወይም አዞ ያስፈጸማቸውን ጥቂቶቹን ለማሳያ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ይህ ባንክ ዛሬ እየተመራ ያው ከኦሮሚያ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ መስራች፣ ባለድርሻና የዚሁ ባንክ የቀድሞ ሥራ አስኪያች ነው፡፡

ለመሆኑ አብይ አህመድ ይሄን ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሲሾም ሌላ ሌላ ሌላውን ትተን ግለሰቡ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ባላው የባለድርሻ ጥቅም የኢትዮጵያ በዘርፉ ዋና ተቀናቃኝ የሆነው የንግድ ባንክን ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አሳልፎ አይሰጥም? የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና ሌላው የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተስፋፉበት ያለው ሂደትስ ምንን ያሳያል?

ዛሬ አብይ አህመድና ጋሻ ጃግሬዎቹ አሸባሪ ምናምን እያሉ የሚያጃጅሉን ለመሆኑ የገንዘብ ምንጫቸውና የገንዘብ መተላለፊያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አይደለም? ከዚህ በፊት በዘረፋ ሥም ከሀያ በላይ በሆኑ ዘረፋዎች ለኦነጋውያን ገንዘብ እየተላለፈላቸው አልነበረም? ሚዲያ ላይ እየወጣ ስላሳጣቸው እንዳይወራ እንጂ አሁንስ ይሄው ሂደት አልቀጠለም? በሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት በስታዲየም ሳይቀር እያሰመረቀ ያለው ኦነግ ገንዘቡን የሚሠጠውና የሚተላለፍለት እንዴት ነው? በአጠቃላይ የኢትጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከገንዘብ ኪሳራው ይልቅ ለነፍሰ በላዎች ገንዘብ በመሥጠት አገርና ሕዝብ እያጠፋ እንደሆነ እንዲደረግ መዋቅሩን በኦነጋውያን ከዛም በላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ጋር ሳይቀር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በባንኩ ቁልፍ ቦታዎች ያስቀመጠው ማን ነው? አብይ አህመድ አደለምን?

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ወሳኝ የዲፕሎማሲ ሥራ ባስፈለጋት ወቅት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በደመቀ (ምክትል ጠ/ሚኒስቴር) በተደራቢነት እንዲመራ ሲያደርግ ምን ማድረጉ ይመስላችኋል? ዛሬ ውጭ ጉዳይ እየተመራ ያለው በዋናነት በዲና ሙፍቲ አደለምን? ዲና ሙፍቲሰ ማን ነው? ሌሎች በሰበብ አስባብ ከቦታው ከሌሎችም ቦታዎች ሲነሱ ዲና ሙፍቲ እዚህ ቦታ ለምን ተቀመጠ? ለመሆኑ ግን ውጭ ጉዳዩን በተደራቢነት እየመራ ነው የሚባለው ግለሰብ (ደመቀ) ሥራው ምንድነው? ሁለቱም ጋር ሥራ ስለሌለው እንጂ አንዱ ጋር ሥራ ቢኖረው ሁለቱን ደርቦ የመምራጥ አቅም ይኖረው ነበር? ያም ሆኖ ለምን ብላችሁ ጠይቃችኋል?

አዲስ አበባ፡ አዲስ አበባን በቀጥታ ከኦሮሚያ እያመጣ እየሾመ ያለው ለምን ተብሎ እንኳን መጠየቅ ያስፈልጋል? አዲስ አበባ ውስጥ ባለፉት ሶስት አመታት የሆነው ምንድነው? ብዙዎች መናፈሻ ተሰራ መስቀል አደባባይ ተሰራ ይሉናል፡፡ በማን ገንዘብ? ሥንት ወሳኝ አገራዊ ነገሮች ተሰርዘው? ከሁሉም በላይ ዛሬ አዲስ አበባ ከወያኔ ወረራ ባልተናነሰ ወረራ አልተፈጸመባትም? ይሄን ሁሉ ያረገው ማን ነው?

የኢትዮጵያ መከላከያ፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ከወያኔ ጊዜ በከፋ በኦሮሞነት ብቻ ያደራጀው ማን ነው? አብይ አህመድ ራሱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ (የሚያዘው ካለ)፣ ብርሀኑ ጁላ ታማጆር ሹም፣ ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል አዛዥ፣ ቀነዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስቴር( አሁን በትግሬ ተክቶታል)፣ ባጫ ደበሌ በተቋሙ ያለው ቦታ ባይገባኝም ዋና በሚመስል ደረጃ የሚፈነጭበት የሆነው በማን ነው? እስኪ ከእነዚህ ግለሰቦች ውጭ በመከላከየው ወሳኝ ሚና ያለው ማን ነው? ሣዕረን ያስገደለው ማን ነው? አሳምነው? በዚህ መልኩ እየተመራ ያለ ተቋም ዛሬ ለጠላት መሳሪያ እያስረከበ ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል አብይ አህመድና ቡድኑ ጠላቴ ብሎ በሚያስበው አማራ ላይ ወረራ ቢፈጸም ለምን ይገርማል? በመከላከያው ውስጥ ያለው ዋናው ሴራ ከጀምሩ ከአራት ኪሎ አደለም? እዚህ ላይ ጉዳዩ የጸረኢትዮጵያ ኦነጋዊነት እንጂ የመሠረታዊ ኦሮሞነት አደለም፡፡ እንጂማ የአገሪቱ ታላላቅ ጀግኖችና የጦር መሪዎች የነበሩት እንደዛሬወ ሳይሆን ከኦሮሞ ሕዝብ የወጡ ነበሩ፡፡ የሚገርመኝ ወያኔ ትግሬን ሁሉ ለጦርነት አሰማርታ ባለችበት ሁኔታ የትግራይ ተወላጅ መከላከያ ሚኒስቴር የተደረገበት ነገር ነው? ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ግለሰቡ ከወያኔ ጋር ምንም ንክክ ባይኖረው እንኳን ዘመዶቹ ወራሪ በሆኑባት አገር የመከላከያ ሚኒስቴር ተደርጎ የሾመበት እውነትን እያየን ለምን ማስተዋል ተሳነን? ግለሰቡ የወያኔ ጠላት እንኳን ቢሆን በዛ ቦታ ሊሰየም የለበትም ነበር፡፡ አሁንስ እየተዋጋ ያለው ማን ነው?

እስክንድር ነጋ፡ በመጀመሪያ እስክንድር የታሰረው ለምንድነው? እስክንድር የታሰረው በማን ትዕዛዝ ነው? ከወያኔ በከፋ ያየንውንና የሰማንው የፍትህ ነወረኝነትን የዘረጋው ማን ነው? አብይ አህመድ አደለምን? በነገራችን ላይ እነ ጀዋርና በቀለ ለመታሰራቸው ምን ማስረጃ አለ? አሁን እያየነው ባለው ነውረኝነት አብይ አህመድ እነ ጀዋርን በሻራተን አልጋ ይዞ ሊያኖራቸው እንሚችል ነው፡፡

እንግዲህ የአብይ አህመድ አፍቃሪዎች ከምል አምላኪዎች ብል ይሻለኛልና ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ካላችሁ፡፡ ቀለል አደርጌ ነው የጠየኳችሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ጊዜው የመሸ ይመስለኛል፡፡ ከጅምሩ ለሁሉም መልካም ይሆን ዘንድ በመለክምነትና በቅንነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሰው መስለውን አብይንም ሆነ ሌሎቹን አሳስበናቸው ነበር፡፡ አብይ አህመድ አሁንም ቁማሩንና ሴራውን ቀጥሏል፡፡ አገርን ከውጭም ከውስጥም አስወርሮ የሚቀርለት መስሎት ከሆነ ነገሮች ከሚጠብቀው ፍጥነት በላይ ወደእሱ እየመጡ ነው፡፡ የንጹሐን አማላክ ስለንጹሀኑ ደም አይፋረደኝም ብሎ ሴራውን ቀጥሏል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪክ እንዲህ ያለ ጠላት ገጥሟት አያውቅም፡፡ ያም ቢሆን እየሆነ ያለው ሁሉ መሆን ስላለበት ነው፡፡ የሁሉም ሴራ በጊዜው ይገለጽ ዘንድ እየሆነ ያለው ሊሆን ግድ ነው፡፡

ኢትዮጵያኖች ተጠንቀቁ፡፡ በአሜሪካ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የአገራችሁን ጉዳይ ለወዳጅ አሜሪካኖችና ባለስልጣናት ጠቁሙ፡፡ አፍቃሬ አብይነት አያዋጣም፡፡ አሜሪካ በትረምፕ አስተዳደር ዘመን ኢትዮጵያ ከዘር ሥርዓት ተላቃ እኛ ወደምንፈልጋት ለማድረግ ብዙ ሞክረዋል፡፡ ችግሩ በወያኔ አድጎ የጎለመሰው አብይ የኦነጋውያን ተራ ነው በሚል ስንት ተስፋ የተደረገበትን ሁሉ አበለሻሸው እንጂ፡፡ እንደ ኦነጋውያኖች ቢሆን ከዚህም የከፋ በሆነ፡፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት ያላየንው መቼም የለም ግን ከዚህም የከፋ ነገር እንዳይከሰት አሜሪካ ባለውለታችንም ነች፡፡ ከጅምሩ ወያኔ እንድትወገድ የትረምፕ አስተዳደር ሚና ነበረው፡፡ ኋላም የከፋ ቀውስ እንዳይፈጠር፡፡ ከዛም አልፎ ኢትዮጵያ ገንዝብ እንድትቀይርና አሸባሪዎች እንዲነጥፉ ያደረገቸው አሜሪካ ነች፡፡ በማግስቱ ግን ገንዘቡን አሳትሞ ለአረመኔዎቹ የሰጣቸው አብይና ለዛ ያደራጀው ባንክ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ የሰራው የትረምፕ አስተዳደር ትረምፕ በተናገረው አንዲት ንግግር ትረምፕን የተበቀለ መስሎት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች ወደሥልጣን እንዲመጡ ትልቅ አስተዋጾ ነበረው፡፡ የትረምፕ አስተዳደር እስከመጨረሻው በተለይ የውጭ ጉዳይ የነበረው ፓምፒዮና የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት እንደሁመ ቀድመውም (1999-2002) በኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዤ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ደጋፍ የሚገርም ነበር፡፡ የትረምፕ የተሳሳተ ንግግርም የመነጨው በዋናነት በዲፕሎማሲ ክፍተት ነው፡፡ ያ ባይሆንማ በተቃራኒው እኔ እያለሁ በኢትዮጵያ ላይ ጣት የሚቀስር ወዮለት ሊል በቻለ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ከእኛ ጋር በቀጥታ የሚመለከታቸው የራሱ ውጭ ጉዳይና የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊው በኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዤ በእርግጥም ወዳጆቻችን ናቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን ቲቦር ናዤ ለኢትዮጵያ ዘብ እንደቆሙ ነው፡፡ እንግዲህ በየአደባባዮ ከመውጣት በተሻለ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑ አሜሪካውያን ባለስልጣናትን መቅረብና እነሱንም ማገዝ ጠቃሚ ነው፡፡ እኔ ከጅምሩም ዛሬ ያሉት ከዚህ የተለየ እንደማያደርጉ አገምት ስለነበር በወቅቱ ባአቅሜ ኢትዮጵያውያንን ሳሳስብ ነበር፡፡ ግን ማን ይሰማል? እንዲህ ሆኖም በአይናችን የምናየውን እየካድን ነው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

አሜን

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop