የአማራ ክልል አዲስ ርእስ መስተዳደር አገኘ September 30, 2021 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የቀድሞ የአማራ ክልል ረeስ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር ተነስተው በምትካቸው የአማራ ክልል አዲሱ ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል። ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነውም ሲሰሩ ነበር፤፡ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡ ባደረጉትን ንግግር ቀዳሚ ተግባራቸው የክልሉን ሕዝብ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን፣ የተጀመረውንም የሕልውና ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መሆኑን ገልጸዋል። —————————————— ስለ ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በአጭሩ የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር በመሆን በዛሬው ዕለት የተሰየሙት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ትውልድና ዕድገታቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ነው። የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ ከአዲስ በአበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ በህንድ ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል። በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህርነት፣ በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከመምህርነት እስከ ዲንነት ሰርተዋል። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እስከ ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። ርዕሠ መስተዳድር እስከተሰየሙባት የዛሬዋ ዕለት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ። ዶ/ር ይልቃል በስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በደቡብ አቸፈር ምርጫ ክልል ብልፅግናን በመወከል ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ማሸነፋቸው ይታወቃል። ካሚሎት አማራ ሚዲያ ——————- Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story ” ሽርፍራፊ ስልጣን ለግለሰብ ኢጎ እና ጥቅማጥቅም እንደሆነ እንጂ ለህዝብ የተለየ አማራጭ ሃሳብ እንዲያገኝ አያደርግም ! ” ተክሌ በቀለ Next Story ለቸኮለ! ሐሙስ መስከረም 20/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች