August 3, 2021
8 mins read

ፍፁም ነው ዕምነቴ፣ ናዚስት ወያኔ ነው ጠላቴ!!! – መስፍን ማሞ ተሰማ

tplf nazi

ትግራይ ውስጥ በዕብሪት ተወጥሮ የነበረው ናዚስት የትግራይ ነፃ አውጪ ወንበዴ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሁለት ሳምንት ተወቅጦ እንደ ዱቄት ቢበተንም በዓለም ዐቀፍ የኢትዮጵያ ጠላቶችና በሀገር በቀለ ባንዳዎች ርብርብ እነሆ ጣዕረ ሞቶቹን ትራፊ መሪዎቹን ይዞና ትግራይ ወለድ ጋሻጃግሬዎቹን አደራጅቶ የሰዖል ላንቃውን ከፍቶ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ መዥገርና ታሪካዊ ደመኛ ጠላት የርኩሰት ሁሉ ማህፀን ወያኔ በተረፈ ጣዕረ ሞት መሪዎቹ ያሰባሰባቸው የሽፍቶች ጭፍራ ለመጨረሻው ግብዐተ መሬቱ – ዳግም ለማያንሰራራበት ሞቱ፤ በዲያቢሎስ አውሎ ነፋስ እየከነፈ በአማራና በአፋር የኢትዮጵያ ግዛቶች ሣጥናኤላዊ ጥፋቱን ተያይዞታል።
ላታመልጪኝ፥ አታሯሩጪኝ – እንዲል ብሂሉ – ከመቃብር ወጥቶ ድንጋይ ለድንጋይ የሚዘለው ወራሪው ናዚስት ወያኔ ከመላው ኢትዮጵያ በተመመው የኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ዳግም እንዳይነሳ ሆኖ ወደ ትቢያነት ይቀየራል።
ዕርግጥ ነው ከሲዖል የወጣው ናዚስት ወያኔ ኢትዮጵያን ለመበተን በተረፈ ጣዕረ ሞት መሪዎቹ ምሎ ቢገዘትም ፤ ይህ ቅዠቱ እንኳንና አንድ መቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በህይወት እያሉ ቀርቶ አንድ ኢትዮጵያዊም እንኳን ቢቀር ቅዠቱ የቀን ብርሃን አያይም። ይሁንና ከተበተነበት ተሰባስቦ በአማራና በአፋር ግዛቶቻችን ወረራ ለማካሄዱና ሳጥናኤላዊ ጥፋት ለማድረሱ – በግልፅ የሚታዩና የምናውቃቸው፣ ደግሞም በግልፅ የማይታዩና የማናውቃቸው ምክንያቶች ቢኖሩም – በናዚስቱ ወያኔ የመጨረሻ ግብዐተ መሬትና በኢትዮጵያ ትንሳኤ ላይ ያለን ዕምነት ግን ፀሀይ በምሥራቅ እንደመውጣቷ ያለ ዕውነት ነው!!
ይሁንና የጣዕረ ሞት ወያኔ አፅም ማንሰራራቱ ለጊዜውም ቢሆን ውስጣችንን መናጡ ቆሽታችንን ማድበኑ ፅናታችንንም ባይሆን ተስፋችንን ማንገራገጩ አልቀረም። በዚህ የጦርነት ሂደት ስሜታችን ለመቀያየሩ ሁለት ጉልህ ምክንያቶች አስተዋፅዖ አድርገዋል። አንዱ መረን የለቀቀው የfb አክቲቪስት ተብዪዎችና ዩቱዩበሮች ‘ከውስጥ አዋቂ ምንጮችና ከወታደራዊ ቀጠና የደረሰን መረጃ’ እያሉ የሚለቁት “ሰበር ዜና” ውሎ ሳያድር ‘ዱቄት ዜና’ እየሆነ የሕዝብ ስነ ልቦና መስለቡና ዕምነት መሸርሸሩ ነው።
በእኒህ የfb የጦር አበጋዝ አክቲቪስቶችና ዩቲዩበሮች ‘ያልተደመሰሰ፣ አንገቱ ያልተቀላ፣ መሞቱ በይፋ ያልተነገረ’ ተረፈ ጁንታ የለም። ያልተዘከዘከ ወታደራዊ መረጃ የለም። በኤር ኮንዲሽንድ ቤቱ ሆኖ ‘ስለ ውጊያው መረጃ ሳሰባስብ እንቅልፍ አጥቼ አደርኩ’ ያላለን አክቲቪስትና ዩቲዩበር የለም። አሉታዊ ተፅዕኗቸውን ሳይሆን በየገፃቸው የሚንጋጋውን የአውራ ጣት ብዛት ብቻ ግባቸው ያደረጉ ናቸውና ጉዳታቸው ብዙ ነው።
ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ የፌዴራል መንግሥቱ በዚህ ከናዚስት ወያኔ ጋር በሚደረገው የሞት ሽረት ጦርነት (የመንግሥት አካላት በሚያሳዝን መልኩ ግጭት ይሉታል) ለሕዝብ የሚያቀርበው ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃና ሀገራዊ ማረጋጊያ አለመኖሩ ነው። ከዓለም ዐቀፍ ዲፕሎማሲ እስከ ሀገር ዐቀፍ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ‘ባወጣ ያውጣ’ የመሰለው የመንግሥት ድርጊት በብዙ አጠያያቂ ኩነቶች የተሞላ ቢሆንም ‘መጀመሪያ ሀገሬን’ ያለው ሕዝብ ግን ሁሉን ችሎ በመንግሥት የተጠየቀውን ብቻ ሳይሆን ያልተጠየቀውንም ከማድረግና ከመንግሥት ጎን ከመሆን አልታቀበም፤ ከኢትዮጵያ ህልውና የሚያስቀድመው አንዳች ስንኳ የለውምና።
በሰሜን ወሎና በአፋር ክልል በኩል ‘የሰሚ ሰሚ’ ለሕዝብ ጆሮ የሚደርሰው “ውሀ ቅዳ፥ ውሀ መልስ” አይነት የጦርነት ቀጠና ውሎ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው መንግሥት ‘የመረጃ መዕቀቡን’ አቁሞ ለሕዝብ ዕውነታውን ማሳወቅና መፍትሄውንም ማመላከት ይኖርበታል።
ከወራሪው ናዚስት ወያኔ ጋር የሚካሄደው የፍፃሜው ጦርነት ብሄራዊ እንጂ ከአማራና ከአፋር ጋር ባለመሆኑ የጦርነቱን ልጓም መንግሥት ለመጨበጡና ለመምራቱ በሙሉ ሀይሉና አቅሙ ለሚደግፈው ሕዝብ የማሳወቅና የማረጋጋት ሀላፊነትም አለበት።
የሚሥጢርም ዓይነት አለውና ፌዴራል መንግሥቱ ዙሪያ ጥምጥሙ ሁሉ ለሕዝብ ምሥጢር መሆን የለበትምና በብርቱ ሊታረም ይገባል። ለሞቱ የሚንፈራገጠው ጣዕረ ሞት ወያኔን ፌዴራል መንግሥቱ በዓለም መድረክ በዲፕሎማሲው አፈር ድቤ ማብላት የሚያስችል ሀቅ ተሸክሞ በጁንታው እብለት ለመሸነፉ መንግሥት ራሱን መፈተሽና ማረም የሚጠበቅበት አንዱና ዋናው አብይ ተግባር ነው።
ይህም ሁሉ ሆኖ ግን እንደ ሀገር – ኢትዮጵያ – እና እንደ ሕዝብ – ኢትዮጵያውያን – ምርጫችን አንድና አንድ ብቻ ነው። ኢትዮጵያን ወደ ወጣበት ሲዖል ይዟት ለመግባት በትራፊ ሳጥናኤላዊ መሪዎቹ ፊታውራሪነት የሲዖልን ሠራዊት አሰልፎ በውስጥ ባንዳዎችና በዓለም ዐቀፍ አፍቃሪ ናዚስት ወያኔ ሀይላት ብርቱ ድጋፍ የዘመተብንን ወራሪ ናዚስት ወያኔ ከአኩሪው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ከመላው ኢትዮጵያ ከተመመው ሕዝባዊ ሠራዊት ጎን በፅናት በመቆም የዘመናት የኢትዮጵያን ጠላት ወደ ዘለዓለማዊ መቃብሩ ሸኝተን ሀገራችንን እና ህይወታችንን መታደግ!!! ኢትዮጵያ በተባበረው የልጆቿ ክንድ በግርማ ሞገስ ከፍ ትላለች!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop