October 10, 2020
17 mins read

መች ይሆን ሁከት ከኦሮምያ፣ ሽምቅ ግድያ ከቤንሻንጉል፣ እብሪት ከትግራይ፣ ሃሰተኛ ነብይነትና ሽንጋይ ፓስተርነት ከሃገራችን የሚወገዱት? – በየነ ከበደ

ስለ ኦሮምያ ሁለገብ ሁከት፣ ስለ ቤንሻንጉል ሽምቅ ግድያ፣ ትግራይ መቀሌ ስለመሸጉት ሕወሃቶች እብሪት በርካታ ተጽፏል። በቅጡ ያልተዳሰሰው በሃገራችን አንዳንድ ቦታዎች የሚፈጸመው ሃሰተኛ ነብይነትና ሸንጋይ ፓስተርነት ንግድና ዝርፊያ ነው። ሁከቱም ግድያውም የሚፈጸመው አያት ቅድም አያቶቻቸው ኢትዮጵያን ያቀኑ የአማራና ኦርቶዶክስ ልጆች ላይ ነው። የሕወሃቶቹ እብሪቱ አማራው ላይ አነጣጥሯል። ሃሰተኛ ነብይነትና ፓስተርነት የሕወሃት ቅጥፈትና የድለላ ሥራዎች ውጤት ናቸው። ልማታዊቀማኝነት” ቁልፍ የምጣኔ ኃብት መሠረት ሲሆን እግዚአብሄርን መፍራት ይቆማል።

ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዘመን ታሪክና ኅልውና ያላት አገር ነች። ነገሥታት አንዴ እየሰፋ እንዴ ደግሞ እየጠበበ የሚሄደውን የሃገሪቱን ግዛት ከውጭ ወራሪ እየጠበቁ በብልሃትና በጥበብ አስተዳድረዋል። ኢትዮጵያ ቀድሞ የብሉይን ኋላም የአዲስ ኪዳን እምነቶችን የተቀበለች፣ በተጨማሪም የአይሁድና የእስልምና ኃይማኖቶች የሚመለኩባት፣ በፍቅርና በመተሳሠብ ተዋዶ የሚኖር መልካም ሕዝብ ያላት ምድር ነች። ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው ትልቁ ነገር አንዱ ሶስቱንም ታላላቆቹን ኃይማኖት እኩል የምታስተናግድ ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ የሚኖሩባት ሃገር መሆኗ ነው። በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን…” ተብሎ በታላቁ መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው የአምላካችን ቃል የአይበገሬውን ሕዝቡ የቀለም ልዩነትና የልብ አንድነት ያስገነዝባል።

ሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ኃይማኖቶችን መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ለምድራዊ ሥልጣኔ የበኩሉን አስተዋጾ ያደረጉ ታላላቅ ምሁራንን ያፈራ አካባቢ ነው። ፍልስፍና፣ ሥነ ዓዕምሮ፣ ሥነሕንጻ፣ ሥነፈለክም ይሁን ሕክምና ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሃገሮች መሸጋገሩ በፈረንጆቹ መጽሃፍ ላይ ሳይቀር ሠፍሯል። የፋሲሊደስ ቤተመንግሥት፣ ከአንድ ቁጥቋጥ የተቀረጸው የላሊበላ ቤተ ክርስትያን ተዓምራዊ ገጽታና የአክሱም ሃውልት ውበት – የዛን ታላቅ ሕዝብ ማንነት አጉልተው ያሳያሉ። ይሁንና ግን ምን ጊዜም ቢሆን የማይተኙት የሃገሪቱ ተፈጥሯዊ ጠላቶች ሲቻላቸው በጦርነት ሳይቻላቸው ደግሞ ሁከትና አምባጓሮን እየዘሩ ኢትዮጵያ በእድገት እንዳትራመድ እግሯንና እጇን ሸበቡ።

መልካም የሆኑት የአውሮፓ ሚሲዮናውያን ትክክለኛውን የአዲስ ኪዳን ቃል በማስተማር በነዋሪው ማህል ቅንነት፣ ትጋትና መተሳሰብ እንዲዳብሩ ብዙ ጥረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የቅኝ አገዛዙ የፖለቲካው ክፍል በአስመሳይ ሚሲዮናውያን እየታገዘ ስሜት የሚያዋዥቁ አሳሳች ትምህርቶችን በትኗል። የቅኝ ገዥዎች አንዱ የማፍዘዥያ መተት ኃይማኖትን አወላግዶ መጋት ነው። በድህነት፣ በእርዛትና በረሃብ የሚሰቃይ ሕዝብ በቀላሉ እንደሚታለል የተረዱት የቅኝ ግዛቱ ፖለቲከኞች ኃይማኖትን ሥነልቦና ማጥቂያና ማሰርያ አድርገው በመጠቀም አፍሪካውያንን አሞኝተው፣ መሬቶችን ተቀራምተዋል። ለኬንያ ነጻነት በቁርጠኝነት የታገሉት የቀድሞው ፕረዚዳንት ጆሞ ኬንያታ ይህንኑ በደል በአጭሩ ሲገልጹት እንዲህ ብለው ነበር። ሚሲዮናዊዎቹ እዚህ ሲመጡ አፍሪካውያን መሬት ሲኖራቸው እነሱ ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ነበራቸው። ዓይናችንን ጨፍነን እንዴት እንደምንጸልይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጽ እነሱ መሬት እኛ ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ነበረን። «When the Missionaries arrived, the Africans had the land and the Missionaries had the Bible.They taught how to pray with our eyes closed. When we opened, they had the land, and we had the Bible» ቅኝ አገዛዙ የተወገደላት ኬንያ ዛሬ ብዙ ወንጌላውያን አሏት። በኬንያ መንገዶች ሁሉ ወንጌል ይሰበካል። ችግሩ ግን አሁንም ድረስ አልተቀረፈም። ምጣኔ ኃብቱን ከእጅ አዙሩ ቅኝ አገዛዝ መዳፍ ማላቀቅ ያልቻሉት የኬንያ ወንጌላውያን አሁንም ይጸልያሉ። ችግሩ ግን ከቀን ቀን እየባሰ የሥራ ኃይሎችና ምሁራን ሳይቀር እንዲሰደዱ ያደርጋል። የሌሎቹም የአፍሪካ ሃገሮች ችግር ከኬንያ ጋር ተመሳሳይ ነው።

የእግዚአብሄር ዓላማ አፍሪካን ባዶ ለማድረግ አልነበረም። ቁልል ችግሩ ነው አፍሪካ ዓይኗ እያየ የሥራ ኃይሏን እንድትነጠቅ ያደረጋት። ድህነቱ፣ የበሽታ መስፋፋት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ሥራ አጥነት፣ ወዘተ፣ ናቸው የወንጌሉን ውብ ጸጋ ከአፍሪካ ያራቁት። ምኞት ሌላኛዋ ወጥመድ ነች። አንዳንዱ ምኞቱ መጠነኛ ሲሆን አንዳንዱ ደግሞ የተራራ ያህል የገዘፈ ሥጋዊ ፍላጎት ተሸክሟል። ችግርና ገደብ ያጣ ምኞት ሰው ስጋዊ መሻቱ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ያደርገዋል። በእርግጥ መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚመለከው ኃብት፣ ዝና፣ መኖርያ ቤትና ትዳር፣ እውቀት፣ ወፍራም ደሞዝ፣ በረከት እንዲሞላ ብቻ አልነበረም።

ቅኝ ገዥዎችን ያምበረከከችዋ ኢትዮጵያም ብትሆን ከእጅ አዙሩ ቅኝ አገዛዝ አመለጠች ማለት አይቻልም። የፖለቲካው አለመረጋጋት፣ የምጣኔ ኃብት መድቀቅ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት የሃገሪቱ ትልቅ ፈተና ሆነዋል። ሕወሃት በልማት ስም የበረገደው በር ለምዕራቡ ባዕድ ባህል መግቢያ ሆነ። ሊበራሎቹ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በቤተክርስትያን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ገንዘብ ከመልቀቅ አንስቶ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤተ ክርስትያናትን እስከመሥራት ቃል ገቡ።

አዲሱ የኃይማኖት ነጻነት – ስሑት አገባብ ለሚችሉ መሰሪዎች መልካም አጋጣሚ ሆነ። እውቀትን መጨበጥ እንጂ ከባዱ አታላይ ለመሆን ዓይነ ደረቅነትና በቅኝ ገዥዎቹ የሠለጠኑትን ፓስተሮች አካሄድ መከተል ብቻውን በቂ ነው። አንዳንዱ በተፈጥሮው ተናጋሪ ነው። የእግዚአብሄርን ቃል በችግረኞች ፊት በድፍረት መናገር የሚችል አስመሳይ ደግሞ ትልቅ የገቢ ምንጭ ይፈጥራል። የግል ኃብት ማካበት የሚፈልጉ ጮሌዎች በየቤቱ በሚልኳቸው የሃይማኖት መልክ ባላቸው ሠላዮቻቸው አማካኝነት የሰዎችን ፍላጎት ያጠናሉ። ሠላዮቹ በበሽታ የሚሰቃይን ሰው ጠያቂ መስለው ያጽናኑታል። ሠላዮቹ ለፍቶ ጥሮ ኃብቱን መቋጠር ለማይችል ሰው ምክር መለገስ ያውቁበታል። ሠላዮቹ – አዛኝ፣ ትሁት፣ ቅን፣ መስለው የሰውን ቀልብ መረዳት ይችሉበታል። ዋነኛው የሰላዮቹ ተልዕኮ – መጽሃፍ ቅዱስ ይዞ ችግረኞችን ሊያፈዝና ጥሪታቸውን ሊቀማ ለተዘጋጀው ነቢይ ነኝ” ባይ መረጃ መሰብሰብ ነው።ጉባዔው በየምዕመኑ መካከል ተሸንቅረው ወከባ በሚፈጥሩ አገልጋይ ተብዬዎች ጭብጨባና ጩኸት ሲጋጋል የድሆች ዋይታና ለቅሶ ይበዛል። በምስኪኖች እዬዬ የሃሳውያን ሙዳየ ነዋይ ትሞላለች።

በተለያዩ የአገራችን ክፍሎችወንጌል ሲቀለድባት ደፍረው የገሰጹ የሐይማኖት አባቶች ጥቂት ናቸው። በሃሰተኛው ነብይ የሚነዳው ኳየር የሙዚቃ ክፍል የአፍዝ አደንዝዝ ሚናውንሲጫወት ተዉ” ያሉ የእግዚአብሄር መልዕክተኞች ብዙ አይደሉም። ሃገራችን በጸጋ የሚያገለግሉ ዘማሪዎች እንዳልነበሯት ሁሉ ዛሬ ነብያት” ተብዬዎቹ ቃል ባወጡ ቁጥር የሕዝቡን ቀልብ ጣራ አድርሶ ከወለል የሚለውሰውየኳየር” ስብስብ ካለአንዳች እፍረት ከጉባኤው ፊት ይሰየማል። ተቸግሮ ወደ አምልኮ ቤት የመጣ የዋህን ልብ የማንጠልጠሉ ስልት እንዲሁም ፍላጎቱ በመጠኑ የተሟሉለትን ምስኪን አውገርግሮ ማንደፋደፍ የኳየሩ የሥራ ድርሻ ሆኗል። ሃሰተኛው ፓስተር ወይንም ነብይጨለማው በርቶልሃል፣ የጠላት አሰራር ተመቷል፣ በቃ አትቆዝምም፣ በረከት በደጅህ ነው፣ የአሜሪካ ቪዛ ይሰጥሃል፣ ወዘተ፣ – ሲል በኦርጋኑ ቅላጼ የሚታጀበው የከበሮ ቅጽበታዊ ድለቃብዙዎችን ንጀረጅራል። አታላዮቹ ነብያት በኳየር ተብዬዎቹ ወጀብ እየታገዙ፣ የሰውን ናላ እናውጠው ሲያበቁ፣ መባውንናሥጦታውን፣ ወዘተ፣ ሞጭልፈው ለበታቾቻቸው የየድርሻቸውን ይወረውሩላቸዋል። ሃሰተኛው ነብይእስከነቤተሰቡ እውጭ ሲንሸረሸር፣ የተሻለ ቪላ ሲቀልስና፣ በምቾት ሲቀማጠል – ያኔ በመካከላቸው ቅራኔ ይፈጠራል። የሚገርመው አንዳንዶቹ አታላይ ፓስተርና ነብያት በጸጥታ አስከባሪዎች ሳይቀር የቪአይፒ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ብዙዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ሃሳዊ መሲሆቹን ደፍሮ ከመናገር ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትርን መዝለፍ ቀላል ነው።

ወገኖቼበየዘመናቱ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ የወንጌላውያኑም ሆነ እምነት ተቋማት ገድል እንዳይራከስ እንዲህ ዓይነቱን ኢግብረገባዊ ሥራ ፈጽሞ እንጠየፍ። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ቤቱ የንግድ ቤት ሲሆን አይወድም። ዛሬ ላይ ቤቱ የንግድ ቤት ብቻ አይደለም የሆነው። ስሙ በከንቱ ይነሳል፣ ስሙ መቦረቅያ ሆኗል፣ ስሙ ማፍዘዥያ ሆኗል፣ ስሙ ማስፈራርያ ሆኗል፣ ስሙ መሰለያ ሆኗል። እግዚአብሄር ታጋሽና ርህሩህ ሆኖ እንጂ እንደ ድፍረታችን ቢሆንማ የድምጹ ነጎድጓድ ይጠራርገን ነበር

ወገኖቼወንጌል መንፈሳዊ በረከት ብቻ ሳትሆን የምድር ብርሃን፣ መልካም እውቀትና ፍትህም ጭምር ነች። ወንጌል እርዛትን፣ ረሃብን፣ ጥማትን መቅረፍያ ምስጢር ነች። የወንጌሉን ምሥጢር ለመፍታት መጣሩ አስተዋይነት ነው። የፀሃይ ጨረርን ፍጥነት በሂሳብ ከማስላት ይልቅ ወንጌልን መረዳት ከባድ ነው። በዘናቸው ጥረው ግረው ሠርተው እንደ ላሊበላ ያለውን ታላቅ ጥበብ አውርሰውን እንዳለፉት ክርስትያን ወገኖቻችን እኛም የሚታይ፣ የሚዳሰስ በጎ ሥራ ተክለን ወገኖቻችን ከችግር ተላቀው ነጻ እንዲሆኑ እንርዳቸው እንጂ ድህነታቸውንና ገበናቸውን ማትረፍያችንና የኃብት ምንጫችን አናድርገው።

ወገኖቼሃሰተኛ አገልጋዮች ገንዘብ ያግኙ፣ ቪላና ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይግዙ፣ በአገልግሎት ስም በየምዕራቡ ሃገሮች፣ ዱባይና ሲንጋፖር ይንሸራሸሩ እንጂ ለቆዩ እሴቶች፣ ሥነ ምግባር፣ ግብረገብም ሆነ ለሃገር ክብር አይጨነቁም። እኛ ግን ነቅተን ወደ ልቦና ጸጸት ተመልሰን እግዚአብሄርን በሃቅ ከተከተልነው፣ ሁከት ከኦሮምያ፣ ሽምቅ ግድያ ከቤንሻንጉል፣ እብሪት ከትግራይ፣ ሃሰተኛ ነብይነትና ሸንጋይ ፓስተርነት ከውድ ሃገራችን በቅጽበት ይወገዳሉ። ኢትዮጵያም ዳግም የድል አክሊል ትቀዳጃለች።

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop