ከዓመታት በፊት ጀምሬ እኔ በኦነግ-ወያኔ የሴራ እጅግ የከፋና ሄዶ ሄዶ የኦሮሞን እንደ ሕዝብ ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ አሳስቦች ስናገር ነበር፡፡ እንደ እውነቱ እኔ የዘር ጥላቻ ኖሮኝ አልነበረም፡፡ ይልቁንም በትውልዱ ላይ እየተሰራ ያለው ቁማርና ሴራ ትውልዱን ወደ ፍጹም ባዶነትና የጠላቶቹ ባርነት እየከተተው እንደሆነ በደንብ ስለተረዳሁ ነው፡፡ በዚህም ምክነያት ብዙዎች እጅግ ይጠሉኛል፡፡ የእነሱ ጥላቻ ብዙም ጉዳዬ አልነበረም፡፡ የሚሰማ ቢገኝ እያልኩ ከመናገርም ወደ ኋላ አላልኩም፡፡ የምናገራቸው ነገሮች በአብዛኛው ከራሴው ልምድና የማውቃቸውን እውነታዎች ተንተርሼ እንጂ ከራሴ በማፍለቅ አደለም፡፡ እኔ ለወያኔ የ27 ዓመት አገዛዝ ዋና መሣሪያው በኦሮሞ ፖለቲካ የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ የወደቀው የኦሮሞ ምሁርና አዲስ የወጣው ትውልድ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡ ይሄንንም ብዙ ጊዜ ለመጠቆም ሞክሬ ነበር፡፡
ብዙ ጊዜ የማናስተውለው ነገር ቢኖር ነገሮች መሆን አለመሆናቸውን ሳይሆን ጭንቅላታችን በተሰራበት የአስተሳሰብ ባርነት ሊወድቅ እንደሚችልና ክፉና ደጉን፣ እውነትና ሐሰቱን፣ መልካሙንና መጥፎውን ወዘተ ለመለየት መታወር እንደምንችል አለማሰባቸውን ነው፡፡ የኖህ ዘመን ሰዎች ጎርፉ አንገታቸው እስኪደርስ አላወቁም፡፡ ይሄ አሁን ለዚህ በብዙ የተረት ተረት ታሪክ መጥቶ እዚህ ለደረሰ ማህበረሰብ ስለኖህ ዘመን እውነታነት ቢነግሩት እንዴት ይገባዋል፡፡ በመጽሐፍ እንዲህ የሚል አስፈሪ ቃል አለ፡፡ ተናጋሪው ፈላስፋው ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡ እንግዲህ ሰው ለማይረባ አእምሮ አንዴ ተላልፎ ከተሰጠ ለመጸጸት እንኳን አይችልም፡፡ ምክነያቱም የሚያስብበት አእምሮው ነው የተበሸው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር እውነት ነው፡፡ እውነትን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን፣ በአልተፈጠረ ታሪክ ጥላቻንና ዘረኝነትን እውቀታቸው ባደረጉት መጠን፣ አባቶቻቸው ያልኖሩበትን ባርነት በራሳቸው ፈጥረው በፍቃዳቸው ወደ አእምሯቸው በጋበዙና በቀረጹት መጠን፡፡ ምን አለፋችሁ አሉ የተባሉ የጸረ-ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነት ክፋትና አውሬነትን በውዴታቸው ከራሳቸው አመንጭተው ለልጆቻቸውም ይሄንኑ ሐይማኖት አድርገው በነገሯቸው መጠን፣ ዛሬ ግልጽ እየሆነ የምታዩትን የኦሮሞ ምሁራንና፣ አዲሱ ትወልድ ወደ ለየለት አውሬነት መቀየርን ገንዘብ አድርጎለታል፡፡ አዝናለሁ፡፡ አሁንም ላይ ሆነው እየገባቸው አደለም፡፡ ያው ከላይ እንዳነሳሁት እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ነው፡፡ በምን አእምሮ ወደማንነት መመለስ ይቻላል? በተለይ ቤተሰቡ ከቤት ጀምሮ በዚህ የጥላቻና ዘረኝነት አሳድጎት እዚህ ያደረሰው፡፡ ቆይቶ ኦሮሞን እንደማህበረሰብ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ደጋግሜ ተናግሬ ነበር፡፡ ዛሬም እላለሁ፡፡ ለሌሎችም አመክራለሁ እኔም እንደቄሮ የሚል መንፈስ እንዳይከተላችሁ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ዛሬ ቄሮ ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች እየታወቀ መጥቷል፡፡ በሲያትል ሰሞኑን የሆነውን ብዙ ሰው አይቷል፡፡ በሲያትል ተወልደው ያደጉ ኦሮምኛ እንኳን መናገር የማይችሉ በቤተሰቦቻቸው እየተነግራቸው ባደጉት የትላቻና ዘረኝነት ልክፍት ሰውን በአደባባይ መደባደብ ጀምረዋል፡፡ ከዚህም የባሰ አደገኛ ወንጀል ሊሰሩ እንሚችሉ ሕዝባችን ተረድቶ በዚህ አይነት እንቅስቃሴ የሚሳተፉትን ከእነቤተሰባቸው ለሕግ ማሳወቅ አለበት፡፡
ኦሮሞ አሁን ባብዛኛው ማለት ይቻላል ዛሬ እየተከተላቸው የመጡ አስተሳሰቦች በዋናነት የተቀረጹት በወያኔና አጋሮቿ፣ በኦነጋውያንና በእስላማዊ ኦሮሞ ቡድን ነው፡፡ በተለይ እየቆየ በኢትዮጵያ መዋቅርም በብዙ ሌሎች ቦታዎች በብዙ ኦሮሞ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው ደግሞ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን አደገኛ የሆነ አስተሳሰብ ነው፡፡ አኖሌን አርሲ ላይ ሲያቆሙለት ሁሉም በኦሮሞነት ሲያጨበጭብ ነበር፡፡ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን ከድሮ ጀምሮ በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ያለ ስለሆነ የኦሮሞ ታላላቅ የኢትዮጵያ ታሪክ ድርሻ ያላቸውን አባቶች በኦሮሞ ዘንድ ሥማቸው እንኳን እንዳይጠራ ነበር ማድረግ የቻለው፡፡ አጋጣሚውን ሁሉ ይጠቀማል፡፡ በመንግስት መዋቅር የሚገቡ የዚህ ቡድን አባላት በተቻላቸው ፍጥነት የቡድናቸውን ተልዕኮ ለመፈፀም ጊዜ አያባክኑም፡፡ ጁኔዲን ሳዶ በተሾመባቻ ዘመኖች ዋና ሥራው ይሄ ነበር፡፡ ሙክታር ሲሾም በፍጥነት ነበር አኖሌን ያቆመው፣ የኦሮሚያ የመነግስት መዋቅሮችን በፍጥነት ነበር የያዙት፡፡ ወሳኝ የተባሉ የከተማ መስተዳደሮችንም በእጃቸው ለማስገባት ችለዋል፡፡ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ የመሳሰሉ ከተሞች በኦሮሞ እስላማዊው ቡድን አባላት ከንቲባነት ሲመራ ለምን ሊል የቻለ የለም፡፡ ምክነያቱም ኦሮሞ ሁሉ በኦሮሞነት ታውሮ ምን እየተሰራበት እንደሆነ እንዳያስተውል ሆኗል፡፡ በአብዛኛው በከተማ አካባቢ ባአሉ ኢንዳስቲሪዎች የቅርቡ ሰውና ተወላጅ የሆነው ማህበረሰብ እያለ ዘመዶቻቸውን ከአርሲና ባሌ እያመጡ ነበር የሚቀጥሩት፡፡ አንዳች ወደኋላ አይሉም፡፡ ኦሮሞ ከመሬቱ ተፈናቀለ ይሉሃል፡፡ ማን አፈናቀለው ቢባል እንግዲህ ቢያንስ ከላይ የጠቀስኳቸውን ቦታዎች አስተውሉ፡፡
ይህ ቡድን አሁን በጣም አደገኛ ቦታዎች ላይ እየገባ ነው፡፡ ትልቁ ችግር የኦሮሞ ማህበረሰብ በኦሮሞነት ስለታወረ ይሄ ቡድን እያደረሰ ያለውን አደጋ ሊያስተውል አልቻለም፡፡ ሌሎች ብዙም ስለማይገባቸው አይረዱትም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለከፍተኛ አደጋ መጋለጡ የሚያሰጋኝ የሚያደርሰው የኢኮኖሚያዊ ክስረት ሳይሆን ለአደገኛው ለዚህ ቡድን የጥፋት ሴራ የገንዘብ ማስተላለፊያ እየሆነ እንደሆነ ስለምሰጋ ነው፡፡ እርግጥ ነው ዛሬ የተማረ ኦሮሞ በአብዛኛው በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ተጠምቋል፡፡ ሆኖም በአብዛኛው ከጥላቻና ዘረኝነት ውጭ የሆነ ዓላማ ኖሮት አደለም፡፡ የኦሮሞ አስላማዊ ቡድን ግን እንዲህ አደለም፡፡ ዓላማ አለው፡፡ ኦሮሞን በኦሮሞነት አጃቢ አድርጎ ለዘመናት የተመኛትን የኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቅ ድጋፍ ከአረቡ ዓለም አለው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራአስኪያጅ የሆነው ግለሰብ የአረቦችን የባንክ አሰራር በኢትዮጵያ ለመመሥረት የሚሠራ ነው፡፡ ይሄን አሰራር ከእስላማዊነት ጋር ለማያያዝ እየሞከረ ነው፡፡ ከወለድ ነጻ በሚል፡፡ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ተሳክቶለታል ሲባል ነበር፡፡ እንዴት ሊሳካለት ቻለ የሚለው ሆን ተብሎ ከአረቦች ገንዘብ ስለሚገባለት እንደሆነ አለማሰብ አደገኛው ስህተት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንም እንዳያስታቸውሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙ ሌላው ትውልድ በደጋፊነትና በነቃፊነት ጎራ ራሱን መድቦ ያለምክነያት ይደግፋል ያለ ምክነያት ይጠላል፡፡ አሁን ዘመኑ የማህበራዊ ድረ-ገጽ የፈላበት በመሆኑ ሰው ምክነያታዊ ሆኖ እንዳያሰብ ብዙ መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡ አስተላላፊዎቹ ምን እንደሚሰሩ ያውቁታል፡፡ ተቀባዩ ግን ብዙም አይረዳም፡፡ ይሄን አይቶ አለማድነቅ መሐይምነት ነው፣ ይሄን አለመደገፍ ድንቁርና ነው፣ ምናምን የመሳሰሉ መልዕክቶች እጅግ እየበዙ ነው፡፡ ገብታችሁ የሚሉትን ስታዩ እንኳን ሊደነቅ ተራ ጉዳይ እኳን ሆኖ አታገኙትም፡፡ ኢትዮጵያን ለማዳን ጥብቅና በራሳቸው የቆመ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ያስፈልጓታል፡፡
መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን ከመቼም በላይ ዘሬ ሊፈተሽ ግድ ይለዋል፡፡ በኖሩበት የማሴር ቁማር ወጣ በማለት ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ ምርጫ ለማራዘም ኮሮና ምክነያት ሆኖ በታወጀበት በዚህ ወቅት አብይን ለመደገፍ በሚል በየቦታው የምናያቸውን የሕዝብ ትዕይንቶች አስተውሉ፡፡ ለመሆኑ ይሄ ለሕዝብ ማሰብ ነው? በዚሁ የአዋጅ ወቅት ነው ብዙዎች ሰዎችን ለግደልና ንብረት ለማውደም የከተማ መንገዶችን ሞልተው ያየነው፡፡ በዚህ ወቅትም ነው መንግሰት ነኝ የሚለው አካል ዜጎችን ቤታቸውን እያፈረሰ ሜዳ ላይ እየጣለ ያለው፡፡ ሰሞኑን የግድቡን ውጤት አስመልክቶ በጻፍኩት ብዙ አስተያየት ተሰጥቶ አየሁ፡፡ አብዛኞቹ ስማቸውን አልገለጹም፡፡ መልክቶቹ ግን ተመሳሳይና በአብዛኛውም ከተመሳሳይ ሰው ነው የሚመስሉት፡፡ እኔ ስለግድቡ የተናገርኩት በእርግጠኝነት ነው፡፡ የምንፈልገው ኩሬ አደለም! እርግጥ ነው የግድቡ ጉዳይ በወሳኝ ሰዎች እንደተያዘ እረዳለሁ፡፡ ከአብዛኛው ሰውም በተሻለ ስለሂደቱ መረጃው አለኝ፡፡ ግድቡን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲለን የነበረው ሰው ዛሬ ለፖለቲካ ፍጆታ እንዲሆነው እንዲህ ያለ ቅንጥብጣቢ የግድቡን ሂደት ሥኬት ሲጠቀምበት ስላስተዋልኩ ነው፡፡ አብይን ከማንም በላይ ከሚደግፉት ነበርኩ፡፡ ለኖቤል ሽልማት መታጨት አለበት በሚል ምን አልባትም መጀመሪያ የጻፍኩት እኔው ነኝ፡፡ እንደ ዳዊት ልጅ ሮብዓም እንዳይሆን ብዙ የሚያበረታቱ ነገሮችንም ጽፌ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የዘሬን ብተው ይመንዝረኝ ሆነና አብይ አሜሪካ ሚኒሶታ ከእነ ጀዋር ጋር ከተነጋገረ በኋላ እየሆነ ያለውን ሳስተውል ነገሮች ወደ አልሆነ መስመር እየሄዱ እንደሆነ በግልጽ ለማየት ተገድጃለሁ፡፡ እርግጥ ስመኘው እሱ አሜሪካ መጥቶ ተገድሎ ራሱን አጣፋ በሚል ተድበስብሶ ቀርቷል፡፡ እንግዲህ ይሄ የሆነው አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ ከጥቂት ወራቶች በኋላ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን አብይንም ሆነ ለማን የዘር ማንነታቸውን አልጠየቁም፡፡ ያየንውን ሁሉ ድጋፍ በመስጠት በፍቅርና በከፍተኛ መነሳሳት ተቀበሏቸው እንጂ፡፡ ያ ሆነበት ወቅት የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ልክፍት የተያዘው ትውልድ ግን እንዴት ኦሮሞ ሆነው ኢትዮጵያ ይላሉ በሚል አኮረፈ፡፡ እነሱ ብዙ እየሰራንልህ ነው ቢሉትም ብዙ ሊቀበል አልፈለገም፡፡ በእርግጥም ነበር በኢትዮጵያዊነት የቃላት ሽፋን እነአብይ የኦሮሞነትን መዋቅር በፍጥነት ነበር የዘረጉት፡፡ በትግሬ ወያኔ የረገምንውን እነሱ በብዙ እጥፍ አሻሽለው መንግስት መሆንን ፈለጉ፡፡ ኦሮሞ ለሚሰራቸው ወንጀሎች ሁሉ ሽፋን እየሆኑ ኦሮሞን ወደለየለት ሥርዓተ አልበኝነት መሩት፡፡ መጀመሪያ ስላልቻሉና ስለተቸገሩ ነው በሚል ብዙ ታገስን እየቆየን ስናይ ግን ጉዳዩ ሴራ እንጂ አለመቻል እንዳልሆነ ታዘብን፡፡ ይሄው ዘሬም ድረስ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እንጂ እየተሸለ አለየንም፡፡ እንግዲህ ያ ሁሉ እድል ተፈጥሮለት ኢትዮጵያን ዛሬ ወደ ደረሰችበት ችግር የከተተው፡፡ ብዙ መናገር አልፈልግም፡፡ ግን እያስተዋልን ይሁን፡፡ ማንንም በማንነቱ አልጠላውም፣ መለስ ትግሬ ስለሆነ አልጠላውም ስለሰራው ሥራ እጠላዋለሁ፡፡ በተለይ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ ያስቀረበትና የዘር ፖለቲካን በመትከሉ ይቅር ልለው አልችልም፡፡ እርግጥ ነው የዘር ፖለቲካ የመለስ ሳይሆን የ60ዎቹ የእነ ዋለለኝና የዛ ዘመን ትውልድ የእርግማን አስተሳሰብ ነው፡፡ የማዝነው ዛሬም ሊያውም በተለያዩ አገራት ሄደው ያዩ የዚሁ የአስተሳሰብ ልክፍት ተጭኗቸው ሳይ ነው፡፡
ለውጥ የተባለ ጊዜ ሁሉም በደስታ ኢትዮጵያን ለማሳደግ ትልቅ ተነሳሽነት አሳይቶ ነበር፡፡ እኔም እንዳቅሜ ምሁራንን የተለያየ ሐሳብ እንያመነጩና ወሳኝ የሆኑ ሥራዎችን እንዲሰሩ ከሚያስተባብሩ ጋር እየጣርኩ ነበር፡፡ ዛሬ አሜሪካ የሆነች ዳረጎት ነገር ልትከለክል ፈልጋ ነው መሰለኝ እያስፈራራች ነው፡፡ የምሁራኑ እቅድ ግን ትልልቅ የተባለን ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ነበር፡፡ ይሄን ለማድረግ የሚያስችል ሙሉ ዓቅምም ያላበቸው ምሁራን ፍቃደኞች ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ በእርዳታ ሳይሆን በትክክልም ስላሏት ሐብት ገንዘብ ሊሰጡ የሚችሉ ብዙ አካሎች አሉ፡፡ ኢትዮጵያንም ለመጨረሻ ጊዜ በአምራችነት ከራሷ አልፋ ትልቅ የውጭ ንግድ የሚኖራትን ምርት ለማምረት የሚያስችላት ትልልቅ ሐሳቦች ጠረጴዛ ላይ መጥተው ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ለሚቀጥሉት 30 ዓመታት ዓለም ተጨማሪ 100ሚሊየን ሄክታር መሬት ማልማት ያስፈልገዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚያህል ማለት ነው፡፡ ዛሬ መሬት ሥራ ፈቶ ያለው አፍሪካ ነው፡፡ ደቡብ አሜሪካ አቅማቸውን እያጠናከሩ ነው፡፡ ወደፊት ግን አፍሪካ ዳግም ቅኝ ግዛት ውስጥ እንደሚገባ ይሰማኛል፡፡ ምክነያቱም በቴክኖሎጂው ተወዳዳሪ ሆኖ የአሉትን ሀብት መጠቀም ካልቻለ ሕዝብ እየበዛ ሲሄድ ሀብቱ እያለ በረሀብና ድህነት መሞት ስለሌለበት በግድ ያኔ አፍሪካ ሀብቷን አውጥተው ለሚጠቀሙ ትያዛለች የሚል እምነት አለኝ፡፡ አፍሪካ በአስደንጋጭ ሁኔታ ከአዓለም እየራቀች ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ከምንም አያድንም፡፡ በቴክኖሎጂው እውቀትና ምርምር ካልዳበረ ወደፊት አንድ ግለሰብ አቤቱ ቁጭ ብሎ አፍሪካን ሊዘጋት ይችላል፡፡ ትውልዱን በዘረኝነትና ጥላቻ ከመበከል ለእነደነዚህ ያሉ ጥበቦች ቢያጋልጡት ወደፊት ቢያንስ ተፎካካሪ ሆኖ ይኖራል፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ