” ጉርጥ አደፈጠም ዘለለ ያው ጉርጥ ነው።” ማለት ካልቻልን ለውጥ ለማምጣት አንችልም። – ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

” ጉርጥ አደፈጠም ዘለለ ያው ጉርጥ ነው።”
     ማለት ካልቻልን ለውጥ ለማምጣት አንችልም።
 ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
ህሊናችንን ቸብችበን ባዶ ጭንቅላት ካልቀረን በሥተቀር ፣የወንድማችን ህመም ያመናል።የእህታችን መወገር ሥቃዩ ይሰማናል።የወንድማችን መወጋት አጥንታችን ደረሥ ህመሙ ይሰማናል።ወዘተ።
   እኛ ሰዎች ነን እና  እሥከ ህሊናችን እሥካለን ዘንዳ፣ ፣በሐሰት ክሥ በእሥር የሚማቅቀው ሰው………. ፣እንግልት፣ወከባ፣እርግጫ እና ጥፊ የሚደርሥበት ሰው…..በደረሰበት የአካል እና የአእምሮ ህመም  የሚሰቃየው ሰው…..በግፋ የሚገደለው ሰው ….እንደኛው የእግዜር ፍጡር ነውና  የትም ይኑር የት ፣የማንም ሀገረ ዜጋ ይሁን ወይም ሀገር አልባ፣ ሰው በመሆኑ ብቻ ህመሙ  ሊሰማን ፣የሠቃዩ  ሥሜት ሊዘገንነን፣ ካልቻለ ምኑን ሰው ሆነው? ሰው ሥለመሆን ከእኛው አቡን ከቅዱሥ ጴጥሮስ ፣ከሰመዓቱ ጴጥሮሥ እና ከህንዱ ጋንዲ መማር ይቻላል።
   ሰው መሆንን እና ሥለሰው ማሰብ ከሰማዕቱ የምንማረው ሰለኢትዮጵያዊያን ክብር ውድ ህይወቱን ለመሥጠት ያለመሣሣቱን ነው። ከህንዳዊው
ጋንዲ የምንማረው ደግሞ  ሰላማዊ   የሆነ ተቃውሞን እና የመብት ማስከበርን ትግል ወደላቀ ከፍታ ማድረሱን ነው።
    ጋንዲ ልክ እንደኢየሱስ “ግራ ጉንጫችሁን ሲያጮሎችሁ ፣ቀኙንም ድገሙኝ በሉ።”ብሎ ያስተምራል።”ምንም ቢሆን ክፉን በክፉ አትመልሱ።ጠላቶቻችሁን ውደዱ እንጂ አትርገሙ።እንደዚህ ባደረጋችሁ ቁጥር እሳት በአናታቸው ላይ ትከምራላችሁ።በድርጊታቸው እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ ታደርጋላችሁ።”  ይላል። ቢያንስ ራሱ ይህንኑ ተግብሯል።
       የህንድ ነፃ አውጪ፣ በሰላማዊ ትግሉ የእንግሊዞችን ህሊና ያሸበረ ጋንዲ ነው ።ጋንዲ በአኗኗሩ ሳይቀር ማንንም የሚያሥገርምና የሚመሥጥ ነው ።
    በእውነት    አንድ በቂ ዕውቀት ያለው ምሁር ፣ራሱን አንቀባሮ ማኖር ሳያቅተው ፣ለተራው ህዝብ ነፃነት፣ፍትህና ብልፅግና ሲል፣እራሱን ዝቅ አድርጎ ፣እንደ ተራ ሰው የበታች ሆኖ በመኖር እንደሻማ እየቀለጠ፣ ለመላው ህንዳዊ(ቋንቋ፣ ኃይማኖት፣ዘርና ቀለም ሳይለይ) የነፃነት ብርሃን እንዲፈነጥቅ አድርጓል።
     ሥለፍቅር ፣ሥለመቻቻልና ሥለሰው ልጅ እኩልነት እየሰበከ ፣ሰልጥነናል ያሉትን እንግሊዞች በታላቅ ህዝባዊ ትዕግሥት ለእኩይ ድርጊታቸው፣ህዝብ ተመሳሳይ ድርጊት ባለመፈፀም፣ ለኢ_ሰባዊነታቸው እና ለብልግናቸው ህሊናን፣ የሚቆጠቁጥ ንቀት በማሳየት ፣ በድርጊታቸው እንዲያፍሩ አድርጎ፣በሰላማዊ አመፅ ፣ህንድን ለነፃነት ማብቃቱም ይታወቃል።
     ዛሬ በእኛ ፖለቲከኞች የሚሥተዋለው ለግል ጥቅም እንጂ ለትውልድ ጥቅም ያለማሰብ የህሊና ቢሶች ተግባርን ከጋንዲ ህሊናዊ ትግል ጋር ሥናሥተያየው ያሳፍረናል።
ነገ ወደ አፈር ሲገቡ ትተውት ለሚሄዱት ቁስ፣ ለሚሥገበገቡ፣የቁስ ሰቀቀን ጨምድዶ ለያዛቸው፣ ፖለቲከኞች የጋንዲ ታሪክ በእጅጉ ያስተምራል።…(እንዴት የሀገር አሥተዳዳሪዎች በሚያሥተዳድሩት ላይ አፓርታይድን በቋንቋ ሥም ይተገብራሉ???)
     የአንድ ሀገር ፖለቲከኞች ሥነ ምግባር በቀጣይ ትውልዶቻቸው እንደሚፀባረቅ ህንዶችን በማየት መረዳት እንችላለን።በአንድ ሉአላዊ መንግሥት የመንግሥት መዋቅር ውሥጥም ፣በሥነ ምግባሩ የተመስገነ ህዝባዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ባለሥልጣን እና ሰራተኛ ፖሊስ ና ወታደር ከሌለ፤የአጠቃላይ ህዝቡ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል።ከህንድ እና ከጋንዲ የምንማረው አለ።ከራሳችንም ሀገር ውድቀትና ትንሳኤ ብዙ መማር እንችላለን ። ለመማር ዝግጁ ከሆንን።
   እርግጥ   የእኛ አበሣ ማለቂያ ያጣው፣ ጉርጥን  በአንድ ድምጽ ጉርጥ ነህ ለማለት ድፍረት ሥለሌለን ይመሥለኛል።ይህንን እውነት በድፍረት እንዳንናገር ጠመንጃ እና እሥር ቤትን እንፈራለን።
   በየወቅቱ የሚነግሡብንም መንግሥታት ሥልጣንን እንደያዙ እውነትን ይፈራሉ።(የፀጋዬ ገ/መድህን ግጥምን እዚህ ላይ ትመጣለች።ፈራን፣እውነትን ፈራን፣ፍቅርን ፈራን…)  ትግላቸው  የሆድ እና በክላሽ የመንገሥ ምኞት በመሆኑም ሥለ ትውልዱ የወደፊት መፃኢ እድል አይገዳቸውም።
     ሥለ ትውልዳቸው መፃኢ ዕድል የሚገዳቸው፣ከ2050 በኋላ ልጆቻቸው ቀጥተኛ የኃኪም ድጋፍ ሣያገኙ እንዲታከሙ ፣(ምገባቸውን አዘጋጅቶ ፣ፅዳታቸውን ጠብቆ ፣መድሃኒታቸውን በሰዓቱ እየሰጠ የሚያገለግል ሮቦት ፈልሥፈው እርፍ ለማለት ካቀዱ ከረሙ። በህክምናው ዘርፍ ብልጭታዎችን እያሳዩን ነው።)
   ይህም ብቻ አይደለም።በ2099 እኤአ ደግሞ፣የሰው ልጅ የፈለገውን እንሥሣ በጄኔቲክ ኢንጂነሪግ ፈጥሮ እና አራብቶ መብለት የሚችልበት ዘመን እንዲሆን እየጣሩ ነው።ሥለ ሆድ ቅንጦት ለትውልድ ሲጨነቁ አይገርሙም??
    እኛ አፍሪካዊ እንደመሆናችን ከሡልጡኑ አውሮፓና ከአሜሪካኖቹ በ200 ዓመት ወደኋላ ቀርተናል። ጥንት ከግሪክ  ጋራ ነበር የኢትዮጵያ ፉክክር።  ምን ያደርጋል ?!እሥከ 16 ኛው ክ/ዘ ድረሥ ተኛን። …በአእምሮ ድህነት
   እንዲህ   ወደኋላ ያሥቀረንም በአይምሮ ድህነት ተጠፍረን በመያዛችን ነው።የቀለም ትምህርቱን ከነጮቹ ብንኮርጅም፣ እንደ እነሱ ሰው መሆናችንን መገንዘብን ሳይሆን ቆዳችንን እንድናዋድድ ነበር ያሤጠኑን። በማቅረብ እና በማራቅ፣የጦር መሣሪያ በመሥጠትና በመፈንግ እርሥ በእርሥ እንድንጨራረሥ ነበር የሚያጀግኑን።
   ይህንን የቅርብ ዘመን ታሪክ እንኳን፣ከህዝብ ጋር በቀጥታ የሚገናኙት የእኛዎቹ የሚዲያ ባለሙያዎች ፣ ህዝብን ለማንቃት  በእውነት ላይ የተመሠረተ ሰው ሰውነቱን እንዲገነዘብ የሚያደርግ መረጃ አያቀርቡም።
     በየዘርፋቸው ፣ ሰው ሰው መሆኑን እና ለተሻለ ኑሮ መተባበር እንደሚያሥፈልገው አበክረው አይነግሩትም። አብዛኞቹ  ብዙሃኑን ከድህነት ወለል በታች የሚኖረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ፈፅሞ የዘነጋ አርቴፊሻል ፕሮግራም ነው የሚያቀርቡት። ህዝቡን ለሥራ የሚያነቃቃ፣አንድነቱ ለእደገቱ ወሳኝ እንደሆነ፣በዓለም ላይ ሰው ተባብሮ፣ተጣምሮ፣ተጋግዞ እንጂ ተለያይቶ ለብልፅግና እንዳልበቃ፣ታሪክን እና የበለፀጉ ሀገራትን ምሳሌ በማሳየት ተጨባጩን እውነት ለመሥጨበጥ አይጥሩም።
    ቋንቋ የህዝብ እንጂ የአንድ የተወሰነ ገዢ መደብ ንብረት እንዳልሆነ አያሳውቁም።  “አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ አርሶ አደር እና አርብቶ አደር እንዴት አድርጎ ነው ሌላ ቋንቋ ተናጋሪን የሚበዘብዘው? ኦሮምኛ ተናጋሪ ላብአደር፣አርሶ አደር በምን ዓይነት መንገድ ነው፣በተረኝነት ሥሜት የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ መሰሉን የሚያሰቃየው??? ወዘተ። ” በማለት ቋንቋ ከጨቋኝ ገዢ መደቦች ጋር ተዛምዶ እንደሌለው የማያሥረዱት?
    የነሱ እበላባይነት ብዙ ባያሥደንቀንም እና ሁሉም ሰው ለመኖር መብላት እንደሚያሥፈልገው ብናምንም ትንሽ ይሉንታ ቢኖራቸው ግን መልካም ነው፣የሚል ተሁት ምክራችንን ከመለገሥ ወደኋላ አንልም።ከእነዚህ በባሰ ግን የሚያሳፍር እና አሥቀያሚ ሀገር አውዳሚ ተግባር የሚፈፅሙ ፖለቲከኞቻችን ናቸው።
    በህዝብ  ጭቆና ሥም  ትልቁን  የፓለቲካ ሥልጣን  በመያዝ በተዋረድ ሀገር የሚመሩ ሆዳቸው አምላካቸው የሆነ ፖለቲከኞች።…
     ትልቁ የኋላ ቀርነታችን መንሥኤ ራሳቸውን እንኳ በቅጡ መምራት የማይችሉ  በግርግር ተጠቅመው ፣በደርግ ና በወያኔ በጠመንጃ አፈሙዝ ሥልጣን መያዛቸው ነው።…”ሥዩመ ክላሽ ”  ይሉታል ይህንን ሥልጣነ መንግሥት።….
    በዚህ መንገድ ሥልጣን የያዙት የትላንት ተጨቋኞች ጨቋኝ በመሆን እንደታወቁ አይካድም ።ፍትህ ፣ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣እኩልነት ለሁሉም ዜጎች በእኩል አይዳረሥም ነበር።
       የባሰበት ደግሞ የ27 የወያኔ ኢሕአዴግ ሥርዓተ መንግሥት ነበር።በዚህ መንግሥታዊ አሥተዳደር ውሥጥ ያሉ  አንዳንድ በየክልሉ ያሉ  አመራሮች ከቀበሌ የዕድር ኮሚቴዎች ያነሰ ማህበራዊ እሳቤ እንዳላቸውም ህዝብ የሚያውቀው እውነት ነው።
    በዚህ የወረደ ንቃተ ህሊናቸው፣ ለመጪው ትውልድ ድህነትን ላለማውረሥ ሳይሆን ቤተሰባቸውን ለማበልፀግ እና  “አገልጋይህ ነን ።” የሚሉትን እና ለሥልጣን ያበቃቸውን  ጎሣ ፣ቋንቋውን እየተናገሩ ሆኖም በጀርባው እንደመዠገር  ተጣብቀው፣ ደሙን መጠው ለመግደል ሢጥሩ  አሥተውለናል።
   ከሁሉም የሚገርመው፣  ሚዲያዎችም፣ በመዠገሮቹ ደሙ የተመጠጠውን ምንዱባን ሳይሆን ዘበናዊውን ጥቂት ከተሜን እና የደልቃቄ  ኑሮውን ነው የሚያሳዩን።
   በማሥተዋል ብትፈትሹ፣  በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኞቹ መገናኛ ብዙሃኖች የፕሮፖጋንዳ መሣሪያዎች  መሆናቸውን ታረጋግጣላችሁ።የፕሮፖጋንዳ እና የቅሥቀሳ ሥራም የማያልቅ  የማዕድ ምንጫቸው ነው።ያለቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ    ፆም አደር እንደሚሆኑ ሥለሚያውቁ ሰው ሥለእውነት እንዲያውቅ  ከቶም አይፈልጉም።አለቆቻቸው ፣በውሥኪና በጮማ የታወሩ ሹሞችም እውነትን እንዲዘግቡ አይፈቅዱላቸውም።እናም እውነትን ትንፍሽ አይሏትም።
   “ሰው ማለት 99.9 ፐርሰንት አንድ ዓይነት የሆነ ፍጡር ነው።0.1 ፐርሰንቷ የቆዳ ቀለምን ልዩነት በትፈጥርም፣የሰው  ሁለንተናዊ ገፅታውም ሆነ አካላዊ ተፈጥሮው አንድ ነው።
    ጥቁር ነጭ ሳይል ሁሉም ሰው ዘሩ አንድ ነው።ጥንተ ፍጥረቱም አፋሪካ ነው።
   አንድ ወጣት   ሰው  100 ትሪሊየን ሴል፣320 ጡንቻ እንዲሁም፣ሣንባ፣ልብ፣ጣፊያ፣ጉበትና ኩላሊት ፣እንዲሁም የመራቢያ አካል አለው።ከሁሉ በላይ፣ለ 5 ደቂቃ ኦክሥጂን ካጣ የሚሞት፣180 ቢሊዮን የነርቨ ሴል እና 100 ትሪሊዮን የነርቨ ድር ያለው ፣268 ማይል በሰዓት እየፈጠነ መልዕክት የሚያደርስ እንዲሁም፣ከ12እሥከ25 ኪ/ዋ  ኤሌትሪክ ማመንጨት አቅም ያለው ሁሉጊዜ ሣይታክት ክፉና በጎን የሚያሥብ ሆኖም እንደ አካባቢውና ሁኔታ ፣  ከአደጋ እንዲጠበቅ የሚያሥችል አንጎል አለው።…
 ጥንት  የሰው ሁሉ ቋንቋ አንድ እና አንድ ብቻ ነበር። እጅግ በጣም ጥቂት የነበረው እፍኝ የማይሞለው ሰው፣ ( ሁለት ሦሥት እያለ የበዛው) የዛሬ 100,000 ዓመት በፊት ከአንድ ቋንቋ ውጪ አይናገርም ነበር። ዛሬ የሰው ልጅ ብዛት፣ ከሰባት ቢሊዮን በላይ የሆነው ይኸው ሰው ግና   6000 (ሥድሥት ሺ) ቋንቋዎችን በዓለም ዙሪያ እንደሚናገር በጥናት ተረጋግጧል።
   አሁን እና ዛሬ እነዚህ አሉ የተባሉ 6000 ቋንቋዎች ዳግም ቢጠኑ ፣ጥቂቶቹ ሊጠፉ ወይም በመጥፋት ላይ ሊገኙ ይችላሉ።ያልተመዘገቡ ቋንቋዎችም ሊገኙ ይችላሉ።  እርግጥ ነው፣ቋንቋ ይፈጠራል፣ያድጋል ወይ ይቀጭጫል  ፣ቀጭጮም ሊሰነብት አልያም ደግሞ ሊሞት የቋንቋ ተፈጥሮ ግድ ይለዋል።
   ደሞሥ ይህን ታውቁ ነበር?  ሰው ለመናገር ያሥቻለው፣ያአንገት በላይ ፣የመተፈሻ አካሉ አፈጣጠር ከሌሎች እንሥሦች ሁሉ በመለየቱ እና ከ100,000 ዓመት በፊት በተፈጠረው ሆሞ ሰፕያንሥ ውሥጥ  Foxp2 የተሰኘ ለመናገር የሚያሥችል ጂን በውስጡ ሥለያዘ እንደሆነ። …እናም ኢትዮጵያዊያን ሆይ አትሳቱ፣አይደለም እናንተ በዓለም ያለ ሰው ሁሉ ዘሩ አንድ ነው።በቀለም እንጂ በሌላ አንዳችም ልዩነት የለውም።
    ሥድሥትሺውንም ቋንቋ ለማወቅ በመማር ወይም በህፃንነትህ እዛ ሄደህ በመኖር ለማወቅ ትችላለህ።እናም በቋንቋ መደራጀት ትርጉመ ቢሥ ነው።ትርጉመ ቢሥ ይሁን እንጂ መዠገሮቹ ደም እየመጠጡ ለመኖር የሙጥኝ ብለው ይዘውታል።
  ራሥን በራሥ ማሥተዳደር ማለት ፣ፍትህ፣ዴሞክራሲ፣ሙሉ ነፃነት ያለውን አኗኗር ሁሉም ሰው ባለበት ሥፍራ እንዲያገኝ ማድረግ ነው።ለአሥተዳደርና ለተግባቦትም ቋንቋውን ተናጋሪ ሰው በቅርብ እንዲያገለግለው ማድረግም ተገቢ ነው። ልብ በሉ አገልጋይ እንጂ መዥገር በሥሙ ሊነግድበት አይገባም። ወዘተ።”እያለ የሚያሳውቅ የክልል መገናኛ ብዙሃን የሉም። እንደውም እውነት ለመናገር ከሦሥት የማይበልጡ ለጥበብ ግድ ያላቸው የቴሌቪዥን ጣብያዎች ናቸው ሰው ሰው እንጂ ቋንቋ ያለመሆኑን ለማሳወቅ የሚጥሩ።በተለይም ” አርት ቲቪ”…
ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅኔው ንጉሥ ፈላስፋ - የትውልድ ግሥ፤ የኑሮ ስዋሰዋዊ - ምዕት፤ (የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሙት ዓመት መታሰቢያ)

2 Comments

  1. ጓድ ሕላዊ

    እንኳን በደህና ተመለስክ። ዉሎህ አዳርህ እንዴት ነበር? ስትጠፋ ጊዜ በጣም ሰግቼ ነበር። ምናልባት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ለሽልማት ለማጀብ ወደ ኦስሎ ተሻግረህ ይሆናልም ብዬ አስቤ ነበር። ዋናዉ ነገር ሰላም ሁነህ ከነመርዝህ ወደዚህ መድረክ መመለስህ ነዉ። ጥሩ አጀንዳ ይዘህ መጥተሃል። እርሱም በምርጥ ዘሩ አማራ አመራርነትና በአማርኛ ቋንቋ የበላይነት ያልካቸዉን “600 (ሥድሥት ሺ) ቋንቋዎችን” ጨፍልቆ ከዓለም ላይ ማጥፋት ነዉ። ጭፍለቃዉ መጀመር ያለበት በጋልኛ ነዉ። ጋልኛ እንዲጠፋ ከተፈለገ ግን ተናጋሪዉ ብዙ ስለሆነ መጥፋት ያለበት ከነሕዝቡ ነዉ። ይህን ነገር አስብበት፤ አለባለዚያ ይህ ያንተ ቅዱስ ዓለማ ይስተጋጎላል።

Comments are closed.

Share