ከስድስት አመታት በፊት አራት ኪሎ ምንሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት ማርሴል ሬስቶራንት አንደኛ ፎቅ ሰገነት ላይ ተቀምጠን አንድ ሁለት እያልን ከጓደኞቼ ጋር ስንጫወት አስታውሳለሁ፡፡ የኔ ላፕቶፕ ተከፍቶ ክልላዊ የኢትዮጵያን ካርታ ምስል ይታይበት ነበር፡፡መቼም ያ ቦታ የማያሰባስበው ሰው አለነበረም፡፡ የዩንቨርሰቲና የሀይሰኩል መምህራን፣ ጋዜጠኞች፣ደራስያን፣ የሚሊተሪ ተንታቾች፣ ሰላዮችና መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሰራተኞች ለምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የክልል ካርታዎች ምን አይነት ቅርጽ እንዳላችው እንመስል ጀመርን፡፡ የትግራይ ክልል አማራ ክልል ላይ የተቀመጠ ሽጉጥ ይመስላል፣ አፋር ደግሞ ወደ ኤርትራ ዞሮ የሚያበራ ችቦ፡፡ ኦሮሚያ ሁለት መልክ ሲኖርው፣ አንደኛው ሐረር ክልልን ዐይኑ ያደረገ ፈረስ ሲመስል፤ ሁለተኛው የምእራቡ ክፍል ደግሞ ዐይኑ አዲስ አበባ የሆነ የፈረሱን ጀርባ የነከሰ ቀበሮ መሰል እንስሳ ይመስላለ፡፡
ሱማሌ ክልል የፈረሱን ጋማ ነክሶ ተንፈራጦ የተቀመጠ የቀበሮ ዘር ይመስላል፡፡ድሬደዋ በፈርሱ ጋማና በቀበሮው አገጭ መሃል ትገኛለች፡፡ የአማራ ክልል ከላይ ያለው መንታ መልክ ብዙም ባይለይም ወደ አዲስ አበባ የሚጠቁመው ጣቱ ግን ግልጥ ሆኖ ይታያል፡፡ የደቡብ ክልል የንስር እግር የሚታይበት ፊቱን ወደ አዲሰ አበባ ያቀና ውሻ ሲመስል ቤኒሻንጉል ደግሞ ፊቱን ወደ አማራ ክልል ያደረገ ውሻ መሰል እንስሳ ነው፡፡ በጊዜው ጋምቤላ ክልልን ምስል ብናጣለትም አንድ የሆነ የእንስሳ ጭንቅላትን ወደ ደቡብ የዞረ ይመስላል የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስን፡፡
ይህን ተከትሎ ቡትስ ጫማ ስለምትመስለው ጣልያን ውይይቱ ቀጥሎ ስለ ሁለተኛው የአለም ጦርነት የናዚ ታላቋ ጀርመን ኢሪድንቲስም ፖሊቲካም ተነሳ፡፡ ናዚዎች ታላቋ ጀርመን ማለት ትውልደ ጀረመንና ጀርመንኛ ተናጋሪዎች ያሉበት ቦታ ሁሉ ያጠቃልላል በማለት ኦሰትሪያን በመጠቅለል፤ከቸሄክና ፖላንድ መሬት ቆርሰው ካርታ ስሩ፡፡ ጥሬ ሃብት ፍለጋም የስላቮችን ሐገር ወረሩ፡፡
የብዙ ሚሊዮኖች ሕይወት ያጠፋውን በተለይም በአውሮፓ ያሉ ሰፋሪ አይሁዶች ሸረኛና ሴረኛ በማድረግ የዚያን ታላቅ ዘር እድገት ያቀጨጩ መጥፋት ያለባቸው ዘሮች ናቸው ተብለው በመፈረጃቸው ሃብት ንብረታቸው ተዘርፎ የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደባቸው፡፡ ውጤቱ ግን በፊት የነበረችው ጀረመን ሁለት ቦታ ተከፍላ በአሜሪካና ሩሲያ ተጽኖ ስር ከአርባ አመት በላይ እንዲቆዩ አደረገ፡፡ ዛሬም ቢሆን ጀርመንኛ የሚናገሩ ሕዘቦቸ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ ይገኛሉ፤ የኢሪዴነቲዝም ፖሊቲካም በአለማችን በሚገኙ የተለያዩ ሐገራት ውስጥ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
ታዲያ ጀርመንና ኢትዮጵያን ምንና ምን ያገናኛቸዋል ይባል ይሆናል፡፡ በእኔ እሳቤ ውስጥ ይህንን የኋላ ፖሊቲካ ወደ ፊት ጎትቶ ያመጣው ነገር በአለፉት ሁለት አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰማው የፖለቲካ ዲሰኩር ነው፡፡
በቅርቡ በሰለሞን ሹምዬ አዘጋጅነት በዋልታ ቲቪ ሻይ-ቡና ፐሮገራም ስለ ብሔር፤ብሔረሰብና ሕዝቦች የተካሄደውን ውይይት በዩቲዩብ ስመለከት አንድ ተሰብሳቢ፣ ከኦሊቨ አካዳሚ፣ ባህልን አስታከው ስለብሔር መኖር ማረጋገጫ የሰጡት ምሳሌ ቀልቤን ይዞት ነበር፡፡
“እኛ ስንጨፍር፤ ቦረና፣ሸዋና ሰላሌ ወደ ላይ እየዘለልን ነው፣ሌላው ደግሞ እስክስታ…” ሰውዬው ይህን ይበሉ እንጂ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሁሉ አንድ አይነት ጭፈራ እነደሌላቸው ጨርሰው አልነገሩንም፡፡ አዎ እነደሌላው ብሄር ተብለው እንደተጠሩት ሁሉ ኦሮሞም አንድ አይነት ጭፈራ የለውም የተለያዩ ባህሎችም በውስጡ ይነፀባረቁበታል፡፡ ለዚህም የሐረሩን ሸጎዬ፤ በውሎ ኦሮሞዎች የሚደለቁት እስክስታና በጂማ ያለው ጭፈራ ምሳሌዎች ሆነው ሊወሰዱ ይቻላል፡፡
ይሕ ሊፈጠር የቻለው ደግሞ የአለም ታሪክ እነደሚያሰረዳው የሕዝቦች እንቅስቃሴ ከቦታ ቦታ በኃይልም ይሁን በሰላም ሲደረግ አዲስ የሰፈረው ህዝብ በአካባቢው ቀድሞ ከሰፈረው ሕዝብ ጋር በሚደባለቅበት ግዜ ከነባሩ ህዝብ የባህል መገለጫዎችን በቋንቋው፤ሙዚቃው፤ሐይማኖታዊ እሳቤቹ… ውስጥ ቀላቅሎ ይይዛል፡፡
ሌላው አትኩሮቴን የሳበው ደግሞ የኦሮሚያ ምክትል ፐሬዚደንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ በዓል አዲስ አበባ ላይ ሲከበር ያደረጉት ንግግር ነው፡፡ “ኡመነ ኦሮሞ አሲቲ ጨቤ…ከመቶ ሀምሳ አመት በፊት የኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነው የተሰበረው…ዛሬ የሰበረንን ሰብረን ከስሩ ነቅለን…ኦሮሞ እንኳን አሸነፍክ፡፡”
ይህንን ንግግር የሰማው ዕለት ነበር አራት ኪሎ ማርሴል ከጓደኞቼ ጋር ስለ ክልል ካርታ ያደረግነው ጨዋታ ትዝ ያለኝ፡፡ ወዲያውኑም ለምን የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙርያ ወገቡ ቀጠነ የሚለው ጥያቄ ወደ አዕመሮዬ መጣ፡፡
ለዚህ ጥያቄ መልስ ኦሮሞ ሰፊ ግዛት ይዞ ሲኖር ከላይ የሰሜን ሸዋ አማሮች ወደ ታች፣ ከታች ጉራጌዎች ወደ ላይ እየገፉ መጥተው አቅጥነውት ሊሆን ይችላል የሚለው አመክነዮ ሳይነሳዊው የሆነው አዕምሮዬ ውስጥ ሚዛን ሊደፋ አልቻለም ግን አዕምሮዬ ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡
በአስራአምሰትኛውና አስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ መጥተው ስለ አካባቢው የተመለክቱትን የጻፉት አሌሳነደሮ ዞርዚና ፖረቱጋልዊውን ፋዘር አልፋሬዝ እንዲሁም የፍራ ማውሮ የአስራአምስተኛው ክ/ዘመን የአዲስ አበባ አካባቢን የሚያሳየውን፣ አዋሽ ወንዝና ዙቃላ ተራራ እየጠቆመ ከሰሜናዊያኑ ጋር በታሪክ የሚሰትሳስርውን ካርታ ለዋቢነት ማቅረብ ሳያሰፈልግኝ መልሱን አገኘሁት፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ በመምህርነትም ሆነ በጉብኝት በቆየሁባቸው አመታት በወላይታ፤ጋሞ፤ሐድያ፤አላባ፤ሲዳማ… ከ ዳግማዊ ሚኒሊክን ዘመን ከስድስተ መቶ አመታት በፊት ከስሜን የሀገሪቱ ክፍል የዘር ትውልድ ሀረጋቸውን የሚጠቅሱ ጎሳዎቸሀ እነደአሉ ተመልክቼአለሁ፡፡
ጉራጌዎች እነደሚታወቀው ሴማዊ ቋንቋ ተናገሪ ናቸው፡፡ ድንጋይ በመውቀር የተጻፈው ህያው ታሪክም ይህንን ይመሰክራል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት የካ ሚካኤል ፍልፍል ቤተክርሰቲያን፣ አዳዲ ማርያም ፍልፍል ቤተክርስትያን፣ ዱከም ገብርኤል ፍልፍል ዋሻ፣ እንጦጦ እልያስ ፍለፍል ዋሻ፣ ጉፍቲ ገብርኤል…ወለንጭቲ የሚገኘው ዋሻ ቤ/ክርስቲያን ከሰሜን ሸዋ እስከ ጉራጌ አካባቢ ድርስ ያለውን ኦሮሞ መጥቶ በመስፈር ከአካባቢው ህዝብ ጋር በሞጋሳ ተሳስሮ ዜጋ የሆነበት ኢትዮጵያዊ መሬት ላይ እስከአሁን ድረስ ከስድስት መቶ አመታት በላይ በማሰቆጠር የሚገኙ የአማራና ጉራጌ ቀዳማዊ ህልዎት የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡
አንድ ግዜ አንድ ኦሮሞ የታሪክ ሙሁር” በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሚገኙ ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆነው የጨቦ ህዝብ በፊት ጉራጌዎች እንደነበሩና ጨቦ ማለት በኦሮምኛ የተሰበረ የሚለውን ቃል አመልካች መሆኑን የዚያ አካባቢ ህዝብ አሁንም ድረስ፣ ነዎሩ ንበሩ የሚለውን የግእዝ ቃል ለሰላምታ እነደሚጠቀምበት ” ሲናገር ሰምቼአለሁ፡፡
ታዲያ ኦቦ ሽመልስ ነፍጠኛ ኦሮሞን እዚህ ቦታ ላይ ነው አንገቱን የሰበረው የሚለውን ባዶ አተሞ ሰምቶ፣ ገና ለአቅመ ዲኤንኤ ባልደረሰው ሀበሻ የሚለው ፍረጃችው የምታብጠለጥሉተ ህዝብ በእናንተው መንፈስ ቶሞለቶ፤ እናነተን መለሶ የሃበሻ እግር እዚህ ላይ ነው የተሰበረው፤ የተቆረጠው ብሎ ፉከራ ቢጀምር የቱ ሚዛን የሚደፋ ይመሰሎታለ? መቼም ከዳኜ፣ ከነበረን ቅርበት አንጻር ነው ዶ/ርን እንዲህ ብዬ የጠራሁት “ከሮ ማካረር” የሚል ፍልስፍና እንዳለስተማሮ ልቦናዬ ያውቃል፡፡ እባኳትን ገና ወጣት ነዎትና ብዙ ቁምነገር ሊከውኑ ሲችሉ ሕጽጻነ አዕምሮ (Intelectual duwarf) ሆነው አይቅሩብን ፡፡
ነገሬን በክልሎች ካርታ እንደጀመርኩ በዚያው ልጨርስ፡፡ ዶ/ር ዐብይ መሐመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ጀዋር መሐመድ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ አንድ ነገር አድርጎ ነበር፡፡ ይኸውም አዲሱን የኦሮሚያ ካርታ ጊንጪ፣ የኦሮሚያ ቄሮ ወይም የወጣቶች ትግል የተጀመረበት ቦታ ላይ፣በ መሰረተ ድንጋይ ላይ አኑሯል፡፡
በዚህ ድርጊቱ ተቃውሞ በበዛበት ግዜ ይህ ካርታ እኔ የፈጥርኩት ሳይሆን እኔ ከመወለዴ በፊት ኦነግ ይዞት የተነሳው ነው፡፡ ያንን ክብር ለመስጠት ነው ያደረግኩት በማለት ማብራሪያ መስል ማደናገሪያ ለመስጠት ሞከሯል፡፡ እዚህ በምኖርበት ካናዳ ያገኘሁት አንጋፋ የኦነግ አባል ግን በዚህ አይስማማም፡፡ በእሱ እምነት ጀዋር ያንን ያደረገው በአብዛኛው የምዕራብ ኦሮሚያ ተወላጆች ይዘወር የነበረውን ኦነግ ማምጣት ያለቻልውን ለውጥ እኔ በፌስቡኬና ኦኤንኤም ሚድያዬ አሳከቼዋለሁ የሚል ተምሳሌታዊ ምልክት ለማስቀመጥ ፈልጎ እንዳደረገው ነው፡፡
የዚህ ሰው ሀሳብ ሚዛን የማይደፋበት ምክነያት የለም፡፡ ጀዋር የመደመሩን ካልኩሌተር የሰራሁት እኔ ነኝ ሲለን ምን ማለቱ ነው? በአብርሐሙ ስላሴዎች ይሁን በኢንዱ ትሪሙቲ እነደሆነ ባናውቀውም ጀዋር፤ እኔ፣ኦቦ ለማና ዶ/ር ዐብይ እኛ ሶስታችን ነን በኦሮሚያ ላይ ያለንው ብሎንስ አልነበር፡፡ በአንድነታቸው ደግሞ ምንም ቢያደርግ ጠያቂ የልውም፡፡ መካሪቸውና አጽናኝያቸውም እሱ ነውና፤ ቢያንስ ቢያንስ በእሱ ህላዌ ፡፡
ስለ ዲሞክራሲ የሚወራው ጆዋር ስለ አይመከቴው የገዳ ሮባዶሪ ጦር ሲናገር በፍጹም የመሪነት ስሜት ሆኖ ነው፡፡ የዚህን ላም አለኝ በሰማይ.. ጦር ለመምራት እነደ ገዳ የጦር መሪ እድሜው ስንት ሞሆን አለበት? እራሱን አደራጊና ፈጻሚ አድርጎ በፈረጀበት “…ማንም አንገቱን ቀና አድርጎ የሚሄድ ክርሰቲያንን አንገቱን በሜንጫ ነው የምንለው፡፡” ብሎ ከነገረን በኋላ በእውነት ገዳ ክርሰቲያኖችን አንገት ለማሰበር ሜንጫ የሚያቀብል ስርአት ነውን ብለን ብንጠይቅ ምንድን ነው ስተቱ? በኮነዶሚኒየም እደላ ግዜ አዲሰ አበቤነትን በግብግብ ለመግጠም ዝግጁነቱን የነገርን ጀዋር፣ ለሲዳማ ክልል ሆኖ መመስረት ጉልበትን መጠቀምን ያረጋገጠ ጀዋር ፣ በድረሱልኝ ተከብቤለሁ ሮባዶሪ ጦሩን አዝምቶ የሜንጫ ውጊያ በየአብያተክርሰቲያኑ አጠድና በምእመናን ላይ በተግባር ያሳየወ ጀዋር ጭራሽኑ ዲሞክራሲን የማያውቅ ወይንም ለአላማው ግዜው እስኪደርስ ድረስ ለመመሳሰል ወይም ለተጊያ ዲሞክራሲን የሚያነበንብ የመካከልኛው ዘመን ሰው ነው፡፡ በእጁ ይዞ ለደሃው ወጣት የሚያሳየው ዳቦ ላይ ላዩን ዲሞክራሲን እሱ የሚለውን የገዳውን ጨምሮ የተቀባ ቢመስልም ውስጡ ግን ቲዬክራሲ ነው፡፡
ወደ ቀድመ ነገራችን ስንመለስ ጀዋር በጊንጪ ያኖራት የኦሮሚያ ካርታን ሁል ግዜ እሱ እነደሚለው በጉለበትም ቢሆን ለማስፈጸም ሳይሞክር እንደማይመለስ እሙን ነው፡፡ የጀዋር ካርታ ከአሁኑ የኦሮሚያ ካርታ በምን ይለያል? አሁን ካለው ካርታ በላይ ዙረያውን ካሉ ክልሎች መሬት ይነጥቃል፡፡ ከሱማሌ፣ ደቡብ፣ አማራ፤ቤኒሻንጉል …ዛሬ ቃሊቲ ያለው የቀድሞው የሱማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲኢሌ ልዩ ኃይሉን አንቀሳቅሶ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ኦሮሞ ከአካባቢው እንዲፈናቀል ሲያደርግ የአማካሪዎቹ ጀነራሎች ምክር ቢኖረበትም አንድ ፍርሀቱን አመላክቶን አልፉአል፡፡ ኦሮሞዎች ወደብ ስለሚፈልጉ ሱማሌን መጠቅለል ይፈልጋሉ፡፡ ኦነግ በተለያዩ ግዜያት የሃሳብ ለውጦችን አሳይቶል ለዚህም ማስረጃው የነ ሌንጮ ለታ፣ሌንጮ ባቲ፣ ዲማ ነጎ … የዳውድ ኢብሳ ሰላማዊ ትግልን ጨምሮ የፖለቲካ ዲሰኮርሶችን ማዳመጥ ይበቃል፡፡
ጀዋር ጊንጪ ላይ የተከላት ድንጋይ ግን ልዩ ነች፡፡ በሌባ ጣቷ አማራና አፋርን ሰርስራ አልፋ ትግራይን ትጠነቁላልች፡፡ ወደ አሰብ ወደብ መቃረብ ፈልጋ ይሆንን? ዋ ከኢህአድግ በፊት ኖረሽ የማታውቂው ኦሮሚያ! ኋላ ሻብያ ይሄን ያዳመጠ ግዜ…፡፡ ከእራሳችን የጦርነት ታሪክ እነደተማርነው ታላቋ ትግራይ፣ታላቋ ሱማሌ፣ ታላቋ ኦሮሚያ፣ታላቋ አማራ…የሚባለው ሁሉ ህዝብ ለህዝብ የሚያጫርሱ ተምኔቶች ናቸው፡፡ ታላቅ ሆኖ የሚኖር ነገር ካል ዲሞክራሲ፣እኩልነትና ፍትህ የሰፈነባት፣ ያላትን የሰው ኋይል፣ጥሬ እቃ፣ታሪካዊ መሰህቦችና አንጸባራቂ ታሪክ በአማካኝ መሰረት ላይ አስተሳስራና ገንብታ ወደ ፊት የምታበራ ኢትዬጵያ ብቻ ናት፡፡
ዱሮ ዱሮ አንድ አባባል እየሰመሁ ሁሌ ይገርመኝ ነበር፡፡“ ዳሩን እሳት መሃሉን ገነት ያድርግልን፡፡” ይህ ማለት የኢትዬጵያን መሬት መሃሉን ሰላምና የበለጸገ ድንበር ድንበሩን ግን ጦርነት ይሁን ማለት ነው እንዴ ስል ግእዝና ስዋሰውን ለስድስት አመት ያጠኑ ሽማግሌ ሰውን ጠይቄ ነበር፡፡
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መልሱ “መላው እትዮጵያ ገነት ተሁንልን፤ ዳር ድበሩ ግን በጀግና ልጆቿ ታፍሮ ለጠላቶቿ የሚፋጅ እሳት ይሁን ማለት ነው፡፡” ሲሉ መልሱለኝ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ዙሪያውን መንገድ የመዝጋት ሰትራተጂ፤ እኔ እደሚታያኘና እኔ እንደሚገባኝ፣ዙሪያውን የታሪክ ቁስል በኦሮሞ እንቅስቃሴ ወቅት ተፈጽሞብኛል በሚል ብሄሮች ተከቦ መተለም መጨረሻው፤ መሃሉ እሳት ዙሪያውን እሳት ሆኖ ማረርን ያስከትላል፡፡ ለዚህም ተረትንና ምሳሌ ከመፈለግና ከመፍጠር ያውጣን፡፡ በእውነት ይሁን! አሜን! አሜን! መቼ…
አስቻለው ከበደ አበበ
የቀድሞው የፔን ኢትዮጵያ ቦርድ አባል
ቫንኮቨር ካናዳ
ተሀሳስ 3፣ 2019