ፖለቲካዊ መነጣጠቅ በእርግጥ አክትሟልን? ዛሬሥ በቢላዋ የሚቀልዱ የሉምን? ሥንቱስ ሰው ነው በፈጣሪ በየነ መረብ ውስጥ   እንዳለ የሚያውቀው? (መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ)

 የማናጠቅ ማህበራዊ ጠቀሜታን ማሥተባበል አይቻልም። የኩባያ የጣሳ ፣ወዘተ  እጥረት በየድግሱ እና ለቅሶ ቤት ካለ  እያናጠቅህ ታዳርሳለህ። አንዱ የሌላውን መጠጫ የሚጠጣውን እንደጨረሰ  ያለክልከላ እንዲናጠቅ ታደርጋለህ።
 አሥተናጋጁም ሆነ ኩባያ ያጣው  ወይም ያልያዘው፣ለመንጠቅ አሠፍሥፎ ፣ ዓይን እና አእምሮውን በጠጪው  ኩባያዎች ላይ ያደርጋል። አሥተናጋጁም ኩባያዎች በባዶነት ቂጣቸው መሬት ሲነካ ለማየት በጉጉት ይጠባበቃል።መሬት እንደነኩም ላፍ፣ላፍ ያደርጋቸውና የኩባያ ያለህ ለሚለው ተሥተናጋጅ  ፣እንቃሪውን እዛው ፊት ለፊቱ ደፍቶ ጠላውን ይቀዳለታል።
     ተሥተናጋጁም አጠገቡ ያለ ባለኩባያ ባዶ ኩባያ ካሥቀመጠ ፣ ላፍ ያደርግና  በቅርብ ላለው አሥተናጋጅ እንዲቀዳለት ባዶነቱን ያሳየዋል።ማንቆርቆርያውን  ይዞ የቆመውን ንቁ አሥተናጋጅ የኩባያውን ባዶነት እና ተነጣቂነት አሥተውሎ ይቀዳለታል።ለነጣቂው እየቀዳለትም ” ጎበዝ እየተነጣጠቃችሁ ጠጡ። ” በማለት በድጋሚ ያሳስባል።እናም መነጣጠቁ ይቀጥላል።
     የእኔ፣የግሌ፣የብቻዬ መጠጫ ነው ብሎ ይዞ ኮራ፣ጅንን ብሎ ፣መቀመጥ የለም።መደጋገም የለም።የተቀዳለትን ጠላም ይሁን ውሃ ጠጥቶ እንዳሥቀመጠ ከፊት ለፊቱ ላፍ ነው። ማጠብም ሆነ ማለቅለቅ ሳያሥፈልግ ውሃ ወይም ጠላ የሚያዞረው ወዲያው መጥቶ ይቀዳልሃል።  ይህ ድርጊት የመጠጫ እጥረት ባለበት፣ሁሉ ይከናወናል። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በለቅሶ ቤት፣ከቀብር መልሥ   የሚፈፅም ተግባር ነው።
    በቅርቡ ምንጃሮች ዘንድ ለልቅሶ ሄጄ ፣  ይህንን ክንውን በተግባር አይቼዋለሁ።
      ከቀብር መልስ ፣የእምባ ማድረቂያ፣ ወይም የዕለት ተሥካር፣ የሚበላው ሰው እና መጠጫ ኩባያው በማጠሩ፣ አንድ አሥተናጋጅ አዛውንት “ኩባያውን እያናጠቃችሁ ተጠቀሙ።” ሲሉ ሰመኋቸው።ድርጊቱ አንዱ የጠጣበትን ኩባያ ከእጁ ወሥዶ፣ወይም ነጥቆ ውሃ ወይም ጠላ አሥሞልቶ መጠጣት ነው።ማናጠቅ የሚባለው።ይህ በሥምምነት መጠጫን የመውሠድ ኩነት  የማናጠቅ ድርጊት ነው። የእኔ የምትለው ኩባያ አይደለምና የተሰጠህ፣ኩባያውን ማንም ካሥቀመጥክበት ላፍ  ያደርገዋል።  ” የኔ መጠጫ ነው።ከወንበሬ እስክነሳ ማንም ከእግሬ ሥር ኩባዬን አይወሥዳትም ። ” ማለት አትችልም።ምክንያቱም በአሥተናጋጁ የማናጠቅ ህጋዊነት ታውጆልና ይህንን አዋጅ የመፈፀም የውዴታ ግዴታ አለብህ።  አንድ ጠጥተህ  ቁጭ እንዳደረግህ ኩባያዋ በአሥተናጋጆች ትወሰዳለች።ወይም በሥምምነት አብሮህ ለተቀመጠ ትሰጣለህ። ወይም እንደጨረሥክ  ከእጅህ ላይ ይነጥቅሃል።
  ይህ የኩባያ ማናጠቅ ድርጊት በእጥረት ወቅት የተፈቀደ ተግባር ነው።ይህ ተግባር ለለቀሥተኞቹም ሆነ ለእድምተኞቹ  ብዛ ቢል ተላላፊ በሽታ ሊያሲዛቸው ይችላል እንጂ የሚያመጣባችው አንዳችም ሌላ ጉዳት አይኖርም።እጅግ በጣም የከፋ ጉዳት የሚያደርሰው ሥልጣንን የማናጠቅ ሥርዓት መዘርጋትና ለሥልጣን ሲባል የሚደረግ ያልተገባ  የማናጠቅ  ድርጊት ነው።
  ወያኔ ኢህአዴግ  ሥልጣንን እንደያዘ ቀጥታ ያደረገው ከፍተኛውን  ሥልጣን ለራሱ አድረጎ ሲያበቃ ፣ዝቅተኛውን ሥልጣን ዘጠኝ ክልል መሥርቶ  ለወያኔ ኢህአዴግ  በታመኑለት መጠን ሥልጣን ላይ እንዲቆይ አልያም በግምገማ ሥልጣንን እንዲነጣጠቁ ማድረግ ነው።እርሥ በራሳቸው እየተጠረናነፉ ለሆዳቸው እንዲሟሟቱ ማድረግ ለ 27 ዓመት የተጠቀመበት ሥልት ነው።ይህ የማናጠቅ ሥልት አደገኛ ተግባር ነበር።
  የኩባያ ማናጠቅ ተግባር ይህን ያህል አሥከፊና ወዲያው ጎጂነቱ አይታወቅም።ኩባያ ተናጥቀህ ተላላፊ በሽታ ቢይዝህ ታክመህ ትድናለህ።በእርግጥ የምትሞትበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል።የምትታከምበት አቅም ከሌለህ
     የወያኔን   ሥርአት በመቃወምህ፣ በመተቸትህ … “ግንባር፣ብሄር ብሄረሰቦች ፣ቋንቋዊ አገዛዝ የተባሉ ፣ ‘የባርያ አሳዳሪ ሥርዓት  መዝሙሮች’ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አይበጁም በማለትህ እና ይልቁኑም እንደበለፀጉት ሀገሮች፣በሰው እና በዜግነት ላይ የተመሠረተ ሥርዓት በመፍጠር ሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ነፃነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትህን ፣ዴሞክራሲን የሚያሰፍኑ ጠንካራ ተቋማትን(በቡድን መብት ሥም የዜጎችን መብት የማይጨፈልቅ ህገመንግሥት ፣ መከላከያ፣ፖሊሥ፣ ደህንነት፣አቃቢህግ፣ ፍርድ ቤቶች ወዘተ) መገንባት ለዛሬውም ሆነ ለመጪው ትውልድ ይበጃል ።… ” ብለህ በድፍረት እውነትን ከተናገርክ ሳትውል ሳታድር   በግምገማ ሥልጣንህን ትነጠቃለህ።ባንተ ላይ ‘ትምክህተኛ፣ጠባብ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ለመንጠቅ ከሚጥሩ የፊውዳል ርዝራዦች ጋር ተባባሪ። የፊውዳል ሥርዓት ናፋቂ ወዘተ ”  የሚል ሥም ይለጠፍብህና  ሥልጣንህ ተነጥቆ ” የግም ገማ ” ማአት ላወረደብህ ጓደኛህ  ሥልጣንህ ይሰጠዋል።
  የሚገርመው ራሱ ወያኔ ንጉሥ እና ፊውዳል   ሆኖ በበላይነት እንዳሻው በህዝብ እና በመንግሥት ገንዘብ እየተጠቀመ ወይም የዓለም ባንኮችን ሰነድ የሚያውቁት ምሁር እንዳሉት  በመንግሥት ሥልጣን ተጠቅሞ ” መንግሥታዊ ምዝበራ እየፈፀመ”  እርሱ ጠፍጥፎ የሰራቸው ድርጅቶች ውሥጥ ያሉ አባለት በጊዜ ሂደት በመንቃት ፣”ብዝበዛው ይቁም።ውሳኔ ያገኘ ጉዳይን እያመጣችሁ ለጭብጨባ አትጥሩን።ንጉሥ አትሁኑብን።  የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ አምባገነንነት ይወገድ ፣ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩል ይታዩ።የሰው እንጂ የቋንቋ አገዛዝ ይብቃ!  ወዘተ ” በማለት ‘በአሥብቶ አራጁ ‘ የወያኔ ግምገማ ሳት ብሏቸው ከተናገሩ።በማግሥቱ ከፓርቲው ይባረራሉ። በሚሰጣቸው ተለጣፊ ሥምም ” ካካ የነካው እንጨት” ይሆናሉ።
   የሃያሰባት ዓመቱን ሥርዓት የወያኔ ኢህአዴግ  ንጉሳዊ ሥርዓት ብንለው ፣የሥርዓቱን ተጨባጭ ማንነት በትክክል እና በተገቢ መንገድ ይገልፅልናል።
     ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ሲያደርጉ የነበረው ይህንኑ ነው።ሥልጣንን ከማከፋፈልና ቅንጣቢ እየወረወሩ በየጠቅላይ ግዛቱ ያሉትን ፊውዳሎች ከማናከሥ አንፃር።  ሥልጣንን ለመንጠቅ ሁሉም የመሬት ከበርቴ  ደፈጣ እንድይዝ ከማድሩግ  አንፃር።
     ዛሬሥ  ፣  ሥልጣንን ለመንጠቅ ከማድፈጥ አንፃር  ፣ በኢትዮጵያ ጠ/ሚ  በዶ/ር  አብይ  አህመድ  አሸጋጋሪ መንግሥት የተለወጠ ነገር አለ  ወይ? የተለወጠ ነገር አለ።የተለወጠው በአሸጋጋሪው መንግሥት አሸጋጋሪ የቤት ሥራ ምክንያት የተፈጠረ ነው።
    አሻጋሪው መንግሥት  ቤቱን ያለመጠን በመክፈቱ፣ አሠሡም ገሠሡም በሀገሪቱ ፖለቲካ ሜዳላይ እንደልቡ እንዲፈነጭ ከመጠን ያለፈ መብት  – ያለግዴታ በመሥጠቱ ነው። በሀጉሪቱ ጠቅላይ ሚኒሥቴር ላይ ከጀርባ ቢላዋ እየሳሉ ፣ጠቅላይ ሚኒሥቴሩ  ”  በቢላዋ ቀልድ የለም ! ” ያለማለታቸው ምን ያህል ታጋሽ እንደሆኑ ቢመሰክርም ፣የሳቸው አደጋ ላይ መውደቅ ፣ሀገሪቱን ከዛሬው አሥጠሊ ሁኔታ በአሥር እጥፍ  አሥከፊ ወደሆነ ዘግናኝ እልቂት ውሥጥ ሊገፈትራት ይችላልና ቢያንሥ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ሲሉ ጠ/ሚሥትራችን  ” በቢላዋ ቀልድ የለም በማለት ” ፣ለፖለቲካዊም ሆነ ለኃይማኖታዊ ተልኳቸው ሥኬት ከውጭ ኃይላት ጋር በህቡ በማበር፣ የሰው ህይወት ለማጥፋት ሌት ተቀን ለሚያሴሩ ፣የፓለቲካ ቁማርተኞችና ሤረኞች ግልፅ የሆነ ” የበህግ ዓምላክ ” ማሥጠንቀቅያ በመሥጠት  ሳይረፍድባቸው ወደ ህጋዊ እርምጃ  ቢገቡ መልካም ነው።
      በአሻጋሪው መንግሥት ከጅምሩ ካየነው እና በጣም ከተደሰትንበት ለውጥ እጅግ  የላቀ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው፣የፓለቲካው፣የኢኮኖማው፣የማህበራዊ ዘርፉ መንገድ በአሳታፊ ፖሊሲ  በወጉ ሲጠረግ፣ እና ሲደለደል፣ ነውና ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ጓዶቻቸው  ይህንን መንገድ ቅን በሆነ ልቦና እና ታላቅ ሀገር በመገንባት እውነተኛ ስሜት ውስጥ ሆነው ዘላቂ ወደሆነ የብልፅግና መንገድ የሚወሥደንን ከዘመኑ ጋር የሚጓዝ ፓሊሲዎችን በማቅረብ ፣ፓርቲዎች በነፃ፣ፍትህአዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ በሆነ ምርጫ እንዲወዳደሩ  መንገዱን ሳያመቻቹ ነው።
  እሳቸው ለመሪነት የበቁበትን፣ በሥም ብቻ ያለ የይስሙላ ፓርቲ” ኢህአዴግ ተብዬውን “፣ ወደ እውነተኛ ጥምር ፓርቲ ለማምጣት አሥረአንደኛው ሰዓት ላይ ናቸው።የዚህ ፓርቲ በአዲሥ ፓርቲ መተካት  መበሰር ያለበት አዲሥ አሥተሳሰብን ይዞ መሆን ይኖርበታል።
     በአዲሥ አሥተሳሰብ አራቱም የኢህአዴግ  ፓርቲዎች መጠመቅ ይኖርባቸዋል።ከፍተኛ አመራሮቹ ከራሳቸው ጥቅምና የሥጋ ድሎት ይልቅ ለአጠቃላይ ህዝቡ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል።ማሰባቸውን በተጨባጭ ካላሳዩ ግን እንወክለዋለን የሚሉት ምንዱባን የኋላ፣ኋላ፣  ይሰለቅጣቸዋል።  ይህ ከመሆኑ በፊት ፣ ሳይረፍድባቸው የፓርቲያቸውን ሥም ህብረ ብሄር ያድርጉ፣ያለአንዳች ወንጀል ያሰሯቸው የፓለቲካ እሥረኞች አሊ ይባላልና  ይፋቱ። የማሠቃያ ባዶ ሥድሥታቸውንም አሥጠሊታነት ተናዘው፣ህዝብን ይቅርታን በመጠየቅ፣ ከህዝብ  ይታረቁ ።
    ኢህአዴገን ከፈጠሩት በዋነኝነት  ተጠቃሹ ፣ ሆኖም ግን ዛሬም ባለበት ረጋጩ ወይም ቆሞ ቀሩ ፣የትኛውን በባርነት ላይ ያለ ህዝብ ነፃ እንደሚያወጣ የማያውቀው ህወሓት  በአሥረአደኛው ሰዓት ራሱን ፈትሾ ፣ሳይረፍድበት በትግራይ ከሚቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር ከልተቀላቀለ እና ቋንቋ ላይ ሳይሆን ሰው ላይ የተመሰረተ ፓርቲ በጥምረት ካልመሰረተ የመጨረሻ እጣ ፋንታው ጥርሥ ማፋጨት ይሆናል። “ቀኃሣዊ እና ኃይለሥላሤያዊ ውድቀት ሢያጋጥመው ጥርሱን በንዴት ከማፋጨት ውጪ ምን ያመጣል??። “
    ዶ/ር አብይ አህመድ መራሹ  የለውጥ ኃይል ፣ በታላቅ ትዕግሥት ሁሉም የቆመ የሚመሥለው ፓርቲ እንዳይወድቅ እንዲጠነቀቅ መክሯል። ህወሃት  ከድል በኋላ በ1983 ዓ/ም  በእውን በሁለት እግሩ  መቆሙን ለማረጋገጥ የነፃነት ታጋይነቱን  ሥያሜ ማክሰም ነበረበት።ድል አድርጎ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ሆኖ ሳለ በልተገባው ሥም ሀገርን ማሥተዳደር አልነበረበትም። ራሱ ከግትር እና ከማይም ፓለቲካ ወጥቶ ሌሎቹም እንዲወጡ ማድረግ ነበረበት።ግና ይህንን ያልፈለጉ ለግል ጥቅማቸው ብቻ የቆሙ ከፋተኛውን ሥልጣን የያዙ ግለሰቦች ለውጡን አልፈለጉም።በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በአንካሣ ፓለቲካ ለ 27 ዓመት ንጉሥ ሆነው ገዝተዋል።አቶ ኃይለማርያምም (የቀ/ጠ/ሚ) ብዙዎቻችንን ባላሳመነን ምክንያት በድንገት ሥልጣን ሲለቁ ፣ ኢትዮጵያን መሪ የማያሳጣት ፈጣሪ ዶ/ር አብይ አህመድን ሰጣትና  በእሳቸው አማካኝነት ፣ አያሌ ጥፋቶች የፈፀመው ፣በህግ  ከተያቂነት የማያመልጠው  ኢህአዴግ በይፋ  የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ ወደምትፈልጉት ዴሞክራሲ አሸጋግራችኋለሁ በማለት ቃል ገባ።  እንሆ ከእሾህ፣ከጋሬጣ፣ከአደናቃፊ መሰናክሎች ጋር እየተናነቀ ፣ቃል የገባውን ፣ሁሉም ሰው፣ወይም ዜጋ እየተጠባበቀ ያለውን ዴሞክራሲ በለገሪቱ ለማሥፈን ሌት ተቀን እየጣረ ነው።
    የዶ/ር አብይ መንግሥት  በሂደት ላይ ያለ  አሻጋሪ መንግሥት ነውና የራሱን የቤት ሥራ ውሥጥ ፣ውሥጡን እየሰራ ነው? በበኩሌ የአብይ አህመድን የትላንት  መልካም ሀሳቦችን አደንቃለሁ።  የተናገራቸው ሃሳቦች እውን እንዲሆኑም ከፀሎት ባሻገር የበኩሌን አሥተዋፆ አደርጋለሁ።ሱሪ በአንገት ካላወለቃችሁ  ሞቼ እገኛለሁ በማለት ለመሪው ውድቀት ቢላ የሚሥሉትንም የኢትዮጵያን ውስብስብ ፓለቲካዊ ችግር ሳይሆን የራሳችሁን የማይጠረቃ ሆድ ለማሥታገሥ የምትጥሩ ጅቦች ናችሁ እላለሁ።
   እነዚህ ጅቦቾ፣ ፣  በፓላሥ ቤታቸው እና በየአምሥት ኮኮብ ሆቴል ተኝተው እየተቀለቡ ” ቅንጣቢያቸውን በሰፊው በመበተን” ሰው ሰው መሆኑ ቀርቶ ቋንቋ እንደሆነ በመሥበክ ፣ ሰው ከሰው ባህሪ ወጥቶ በቋንቋ ልዩነት ብቻ ሰው የሆነውን የራሱን አምሳያ ወይም እራሱን  አርዶ እንዲባላ የሚያደርጉ(አዝናለሁ… እንዲህ ያለ ድምዳሜ ላይ በመድረሴ) በዝምታ መታለፋቸውም እያሳዘነኝ ነው።
    እርግጥ ነው ያላዋቂው ሰው አይፈረድበትም።በዛሬው እለት እንኳን በናዝሬት (በአዳማ) በጎሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመምህራን “የአብሮነት” ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር።  በብሄር ብሄረሰቦች ሙዚቃ መምህሩ  በፍቅር  እየተዝናና በጋራ ይጨፍራል።ወደመቀመጫው ሲመለሥ  ደግሞ የቋንቋ ልዩነቱን ያሥጮኸል።ይህ እጅግ ጠርዝ የወጣ የግለሰባዊ ሰብእና መዘበራረቅ ነው።በአንድ በኩል ፍቅር እየገዛው በዛው ሰዓት የቋንቋው ሶሻል ኖርም በማሥመሰል እንዲወግን ያደርገዋል።ይህ   ያላዋቂ ሰው ድራማን በኢትዮጵያ  ምድር  የትም ታገኝቷላችሁ።በዚህ አድራጎቱ   የሀገሬ ሰው  የሠለጠነው ዓለም መሳቅያ እየሆነ ነው። ይህንን ለሥጋ ያደላ  ድራማዊ ድርጊት እየፈፀመ እስከመቼ እንደሚሳቅበት  እግዜር ይወቀው።
     በበኩሌ ይኽ ዓይነቱ  የአድርባይነት ድራማ የሚወገደው፣ በኢትዮጵያ ያለ ሰው ሰውነቱን ሲገነዘብ ብቻ ነው።ባይ ነኝ።
     ይህ ሰውነትን የመገንዘብ እና  ” የዓለም ህዝብ በሙሉ ወንድም እና እህቴ ነው።” ብሎ የማመን መገለፅ ላይ የሚደረሰው አንዳችም መገለጥ የሌላቸው፣ሰው የመሆን ታላቅ ከፍታ ላይ ያልደረሱ ሆነም አውቀናል በቅተናል የሚሉ የጅብ አሥተሳሰብ ያላቸው   ሰውን ለማሥተዳደር እድሉን እንዳያገኙ ሲደረግ ነው።  እነዚህ ሰዎች ሥልጣን ከተሰጣቸው በቢላዋ መቀለዳቸው አይቀርም እና የሀገሪቱ የሰላም እጦት ችግርን ቋሚ እንደሚያደርጉ አትጠራጠሩ።
 እነዚህ ሰዎች እኮ ለአነጋገራቸው እንኳ ለከት የሌላቸው ናቸው።  በአነጋገራቸው ሰውን እጅግ የሚያሳዝኑ ” መንግሥት ውሥጥ ያሉ ባለሥልጣኖች ከብት ወደበረት  ማሥገባትእንኳን  አይችሉም።”  በማለት ያለኃፍረት በቴሌቪዢን  የሚናገሩ ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች በተፈጠሩበት ሀገር፣የፓለቲካ መጫዎቻ ሜዳ መሥፈርት ያለማውጣት  በቢላዋ መቀለድን በቸልታ ማየት ነው። እንዲሁም ያበዳ አይነ ሥውር ቪዲዮ ክፈቱልኝ ሲል የመክፈት  ተግባር እንደመፈፀም ነው።
     እነዚህ የሰው ህሊና ከአእምሯቸው የጠፋ ፖለቲከኞች   ሥለ ሰው ሳይሆን ሥለቋንቋ ነው የሚገዳቸው ፣ የዓለምን ሥልጣኔ እና ታሪክ ያልተረዱ ፣ በቋንቋ ላይ ሙዝዝ ብለው ኦሮሞ ፣ትግሬ፣አማራ ፣ሱማሌ፣አፋር፣ወላይታ ወዘተ።እያሉ ኡ!ኡ! እያሉ ሀገር ይያዝ እያሉ  የሚጮሁ ” ጫታም፣ሺሻም እና ሆዳም ናቸው በተግባር። ” እናም  በአሻጋሪው መንግሥት ይበቃል ሊባሉ ይገባል እላለሁ።…
   በበኩሌ፣ የቋንቋ አምላኪዎችን እና የመሰሎቻቸውን ሥግብግብነትና እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል ባይነት እና   ለገዛ  ምቾታቸው ዘላቂነት ሲሉ፣ለሰው ሳይሆን ለቋንቋ ተሟጋችነትን አጥብቄ እቃወማለሁ።…
   የዚችን ሀገር መሬት ማንም ሰው አልፈጠራትም ።(የዓለምን አፈጣጠር በሣይንሥም ሆነ በኃይማኖት ለመረዳት ከፈለግህ በበየነ መረብ በድምጽና በምሥል ግንዛቤ ማግኘት ትችላለህ።የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ መሬትን ጠፍጥፎ አልሰራትም። እናም የእገሌ መሬት ብሎ ነገር ከእውነት አንፃር የለም።ሁሉ ሃሳብ እና ተጨባጭነት የሌለው የሰው የጋራ እምነት ነው። ትላንት የሌላ የነበረው ዛሬ ያንተ ሆነ ።በቃ።)
    የትኛውም  ቋንቋ ተናጋሪ በቅድሚያ በምድሪቱ እንደኖረ ምሥክርነት አያቀርብም።ይህንን ለማመን  ሥለ ሰው እና ሰለሰው ልጅ ቋንቋ አፈጣጠር  ማንበብ እና ” ከበየነ መረብ ” የድምፅ እና የምስል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።እናቃለን ግን እንጀራችንን የምናገኘው በዚህ እኩይ መንገድ ነው ካላችሁ ደግሞ ይኽ መንገድ የሲኦል መንገድ እንደሆነ እወቁት።በዓለማዊም ሆነ ፣በኃይማኖታዊ መንገድ።በሙሥሊሙም  ሆነ  በክርሥቴያኑም መንገድ። ሄደህ እውነትን ብትመረምር መሬት ባለቤቷ ፈጣሪዋ ብቻ ነው።…
     አንተ ሜንጫ ይዘህ አምሳያህን በቋንቋው ልዩነት ብቻ ለመግደል የምትፎክር ክርሥቴያንም ሆንክ እሥላም በኃይማኖት መፅሐፍህ ላይ ይሄተግባርህ   የማያፀድቅህ ወይም ጀነት የማያሥገባህ  ተግባር እንደሆነ መፃፉን እያወቅህ ለምን ፊደል በቆጠሩ  ጂኒዎች ተገፋፍተህና ተደልለህ ይህንን የዳቢሎሥ ተግባር ትፈፅማለህ?? ህይወትህን በማይቀይር    ከጫት በማይዘል ሳንቲም ተገዝተህሥ ክቡሩን የሰው ልጅ ህይወት ለምን ታጠፋለህ??
     ይህንን ጥያቄ የጠየቅሁ ምናልባት ተፀፅተህ ወደሰውነት ትመለሳለህ ብዬ ነው።አንተ አምሥት ጊዜ ሰጋጁም ሆንክ ዘወትር ወደ ቤተክርሥትያን ተመላላሹ ወንድሜ ነህ።ፈጣሪ ለሰው ፊት እንደማያዳላና ሥለገደልክ ገነት እንደማያሥገባህ አውቃለሁ።ፈጣሪን በግብዝ ሰው ከመሰልከው ተሳስተሃል ።ፈጣሪ በጊዜ ፣በቦታ፣በሁኔታ፣በመዓበል እና በወጀብ የሚታገድ አይደለም ።ከሁላችንም ጋር በተመሳሳይ ማይክሮ ሰኮንድ ውስጥ ምንጊዜም አብሮን ይኖራል።በእንቅልፋችን ሰዓት እንኳን አይተወንም።እኛ  ሰዎች ለዘላለም በፈጣሪ በየነ መረብ ውሥጥ ነን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ወይ የኢሣት ነገር! ጊዜ ደጉ ስንቱን ያሳያል? - ግርማ በላይ

5 Comments

 1. ዉድ ህላዊ፣

  ስም ቀይረህ ደግሞ ፍልስፍና (ድንቄም ፍልስፍና) በሚመስል ማጣጥፍ ፀረ ኦሮሞ መርዝህን መርጨት ጀመርክ? እንኳንስ መርዝ አቶሚክ ቦምብ ኦሮሞ ላይ ብታፈነዳ ያባቶችህን የነፍጠኛ ስርዓት መመለስ አትችልም። ተስፋ ቁረጥ እርሱ ላይመለስ አክትሞአል። ይልቅስ ትኩስ ዜና አለኝ ላንተ። ሞት የምትመኝለት ጀዋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ ምርጫ ዉስጥ ሊገባ ነው። እንደሚያሸንፍና ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስቴር መሆኑ ደግሞ ሳይታለም የተፈታ ህልም ነዉ። ምን ግድጓድ ይዉጠሃል ያኔ?

 2. ለምን እንደ 1970 ዓ/ም የደርግ አብዮት ጠባቂ ዓይነት ድርጊት ለመፈፀም ፈለግህ ያልሆነ ታርጋ በግለሰቦች ላይ በመለጠፍ እንዲጠቁ ለማድረግ አሥበህ ከሆነ ይህ የማክሸፍያ መልሴ ነው። “እኔ ህላዌ አይደለሁም። እነዛ ቀይ ሽብርተኞች “ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ቁም!ይሉ ነበር።”
  ደሞሥ ለምን ከጃዋር ጋር ታነካካኛለህ? በግለሰብ ደረጃ ከጃዋር ጋር ፀብ ያለኝ አሥመሰልከው።በኑሮ ደረጃ እንኮ ብንመዘን እኔ እና እሱ ጫማ እና ኮፍያ ነን።
  ጃዋር አንድ ግለሰብ ነው።ደሞም ሰው ነው።እንደማንኛችንም የበላል ይጠጣል፣ይፀዳዳል።…ይሞታል። ወንድሜ ሆይ፣ ሁሌም የማቀነቅነው፣በብዙዎች ውሥጥ የሰረፀው ሃሳቤ አንድ እና አንድ ነው።እሱም ፣አማራ፣ትግሬ፣ኦሮሞ የሚባል ሰው የለም።ያለው አንድ መጠሪያ ያለው ሰው ነው። ሰው ሰው ነው በቃ።አንበሣ።ጅብ፣ነብር፣ወዘተ የወል ሥም እንደሆነ ሁሉ የሰውም የወል ሥም ሰው ነው።ይሰኛል።
  በሣይንሥም፣በኃይማኖትም።እገሌ ትግሬ ነው።አማራ ነው።ኦሮሞ ነው።አይባልም። እገሌ ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው እንጂ እገሌ ትግሬ ነው እያልን ነው ዘረኝነትን በገዛ ፈጠራችን ያመጣነው ።በትግራይ የሚኖር ሰው አበዛኛው ትግሪኛ ቋንቋ ብቻ በመናገሩ ሰውነቱ ተረስቶ ቋንቋ መሆን ይለበትም። የሌላውም እንዲሁ። ይህ የእሥከዛሬ ፅሁፎቼ ማጠንጠኛ ሃሳብ ነው።
  ውድ ወንድሜ ሰው በመሆንህ ወንድሜ አልኩህ።ኃይማኖትም ሳይንሥም ሥለሚያመሳስለን ወንድሜ ሥልህ እየፎገርኩህ አይደለም።አንተ ግን ሰው ሰው መሆኑን አታምንም መሰለኝ።ሰውንም ታመልካለህ ልበል?(ሥለ ጃዋር ምን አገባኝ። በበኩሌ ሥለ አንድ ግለሰብ ሳይሆን የምጨነቀው በግለሰቡ አማካኝነት ሥለሚሰራጨው አፍራሽ ሃሳብ ነው። እስከዛሬም የምቃወመው ሃሳቡን ነው።
  በእውነቱ ቋንቋ ሊያባላን አይገባውም ነበር።እያንዳንዱ ሰው እንደሚግባባበት ቋንቋ ባለበት ሥፍራ ተገቢው ኢኮኖማያዊ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖማያዊ ፍላጎቶቹን የሚያሞላለት ራሱ መርጦ ሥልጣን የሰጠው ተቋም እና ሰላሙን፣ደህንነቱን፣ መሰረታዊ ፍላጎቱን፣ጤንነቱን የሚጠብቅለት እና የሚያሥጠብቅለትም ተቋም ያሥፈልገዋል።
  ማንም ሰው ፊደራሊዝምን አይጠላም።ፊደራሊዝሙ ግን ሰው ላይ ያነጣጠረ፣የሰዎችን ሰብዓዊ መብት የሚያከብር፣መሆን ይኖርበታል።
  ቋንቋ ሃሳቦችን የምታደርሥበት ነው።በቋንቋ ተጠቅመህ ይኸው ያለሥሜ ሥም ሰጠኸኝ። እሥከ አያቴ የተጠቀሰውን እውነተኛ ሠሜን እንኳ ማመን ከበደህ።በብዕርም ሥም ፃፍኩ በመጠሪያ ሥሜ አድርባይ ብዕር እንደሌለኝ እወቅ።ገንቢ እንጂ አፍራሽ ሃሳብም እንደሌለኝ ተረዳ።
  ውድ ወንድሜ ሆይ ሁላችንም ቆመናል እንላለን እንጂ በመጥፎ ሃሳባችን እያነከስን በመንገዳገድ ላይ መሆናችንን ተረዳ። ሰው መሆናችንን ተገንዝበን በፍቅር ፣ለጋራ ብልፅግና ካልተደጋገፍን ደግሞ መውደቃችን አይቀርም።

 3. አኡጂሉ ይህ ነፍጠኛ ማለት እንደዚህ የሚያባንንህ ፈሪወች ስለሆናችሁ እኮ ነው።

 4. ሂላዊ (aka ገለታ)
  ወስፋታም ያንተ ጀግንነት ደግሞ ምኑ ላይ ነዉ? ኦሮሞንና ደቡብን በሙሉ በሙሉ ያሸነፋችሁት አዉሮፓ በሰጣችሁ መሳሪያ ነዉ። አርሲ፤ ጨለንቆ፤ ከፋና ወላይታ ላይ የሕዝቡን ጀግንነት አይታችኃል። በመሣሪያ እንኳን ሲያቅታችሁ ወደ ጅምላ ግድያ (genocide) ገባችሁ።

  ነፍጠኛ ሲባል በሕዝቦች ለይ አባቶችህ ከፈጸሙት የግፍ ግድያ (genocide) ጋር ስለሚያያዝና የምትጠየቅበት ቀን እየቀረበ መሆኑ ስለታወቀ ጭንቀት ገብቶሃል። ንስሓ ግባና በሰላም ኑር። Reconcile.

 5. መኮንን- ለእነዚህ ሰዎች ሃቅን መንገር ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው::ታላቁ መጽሃፍ አይን ኣአላቸው አያዩም ጆሮ አላቸው አይሰሙም የተጻፈባቸው ተምረናል ብለው ይህ መሰረታዊ ሃቅ የሚክዱ ህዝባችንን በዘር በሃይማኖት ሊያባሉ የተነሱ ናቸው:: በሃገራችን ዘወተር እልቂት የሚቀሰቅሰው ያደግሁበት አካባቢ 99 ከመቶ ሙስሊም ነው ማንም ቢናገረን በሜንጫ(ሰይፍ) ይመታል ብሎ ኢትዮጲያ ከኦሮሚያ ይውጣ በማለት ጎራዴ ታጥቆ የተሰለፈ ቆይቶ ፈግተው ቤት የሰሩ ወገኖች ቤቱን ከተረከቡ ደም ይፈሳል በማለት ጀሌዎቹን አስልፎ ቤቱን ያስከለከለ የሲዳማ ሪፈርንደም በሰላም ካልተከናወነ በጉልበት ይካሄዳል በማለት እጄቶን ተጠቅሞ ሰላማዊ ዜጎችን ያሳረደ ቤተክርሲያን ለመቃጠል ያበቃ በኦሮሚያ ክልል የፌደራል ቋንቋ ኣማርኛ ለተማሪዎች ይሰጥ ዘንድ ክልሉ የወሰነውን በዛቻ ያስቀየረ ገና የታሰበው ምርጫ ቢፈጸም consequence ይኖረዋል ቄሮን ስራህን ጨርስ እለዋለሁ ብሎ የዛተ ጃዋርን በጭፍን ከሚከተል ምንም በጎ አይጠበቅም::

Comments are closed.

Previous Story

በኢህአዴግ ውህደት የሚፈርሰው ህወሓት ወይስ ኢትዮጵያ? – ስዩም ተሾመ

Next Story

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስለውሕደቱ አቅጣጫ ሊያስቀምጥ እንጅ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደማይችል አስተያዬት ሰጭዎች ገለጹ

Latest from ነፃ አስተያየቶች

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት

የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው  በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያ ማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን  ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ  (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው  በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።    ________________________________________ ያማራ ፋኖ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ

Share