ቁጭ ብዬ አንድ ሌሊት
ሳሰላስ በዋልኩበት ።
አንደበቴ ቃል አውጥቶ
በእራሴ ላይ ተነሳስቶ ።
ቢጠይቀኝ ማንህ አንተ
ብሎ ቢለኝ እያቃተተ ።
መልስ አጣሁኝ ምን ልበለው
ባዶነቴን የማስበው ።
እንዴት ልሁን እኔ ራሴ
ከራሴው ጋር መካሰሴ ።
ነኝ ወይ እኔ አንድ ሙሉ
ወይስ ባዶ እንክብሉ ።
የማልሆነውን የሆንኩ
በባዶ ቤት የተኮፈስኩ ።
ደሞ ጉራ ህልም የሌለው
ለራሴ እንኳን የማይገባው ።
ባዶ ቀፎ የድምፅ አልባ
ጥላት እረሴን የምቀባ ።
ላይ ያልወጣው ታች ያልወረድኩ
ድክመቴንም የመሰከርኩ ።
ሆኜ ስገኝ ጫፍ የሌለኝ
በተፈጥሮ የማልቀኝ
ጭልጥ ያልኩኝ ምን የሌለኝ
ከሰው ሁሉ እኔ እኮ ነኝ
ንገሩኛ እኔ ማነኝ ።
ሴፕቴምበር 2019