‹‹ሀገርን ለማረጋጋት እየተሄደበት ያለው እርምጃ ግን አዝጋሚ ነው›› አረጋሽ አዳነ

ዛሬ በአዲስ አበባ ለንባብ ከበቃው ኢትዮጲስ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን ለውጥ አድንቀው ‹‹ሀገርን ለማረጋጋት እየተሄደበት ያለው እርምጃ ግን አዝጋሚ ነው›› ብለዋል፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

የህወሀትና ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪና ሌሎች ስልጣኖች ላይ ቆይተው የህወሀት ክፍፍልን ተከትሎ ከእነስዬ አብርሃ ጋር የተባረሩት ወ/ሮ አረጋሽ በአገሪቱ ውስጥ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ 

በዚህ ቃለምልልስ እንደተናገሩት ጥያቄዎቹ ምላሽ የሚያገኙበት ሁኔታ ግን በሰከነ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሁን የአረና ትግራይ ፓርቲ አመራር የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ ሲናገሩ ‹‹በአገሪቱ እየተነሱ ላሉ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች መሰረታዊና የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት፣ የመድብለ ፓርቲ ስርአቱን ወደሙሉ ቁመናውና መገለጫው ለማሸጋገር፣ ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን፣ ፍትሀዊ በሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ እንዲከናወን፣ እውነተኛ ፉክክርና የሀሳብ ፍጭት የሚታይበት እንዲሆን ለማድረግ ዋነኛው ሀላፊነት ያለበት ኢህአዲግ ነው›› ብለዋል፡፡ ይሁንና ከቀጣዩ ምርጫ በፊት መሰራት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

 ወ/ሮ አረጋሽ ለኢትዮጲስ በሰጡት በዚሁ ቃለምልልስ ሲያስረዱ ‹‹ከምርጫው በፊት በአገሪቱ ላይ ፍፁም ሰላም ሊኖር ይገባል፡፡ ምርጫው ከመደረጉ በፊት አገሪቱን የማረጋጋት ስራ መቅደም አለበት፡፡ ምርጭውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማስኬድ እንዲቻል ሁሉም የሞመለከተው አካል የተግባባበት የምርጫ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት ያስፈልጋል›› በማለት ተናግረዋል፡፡ 

በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩትን ግለሰቦች በተመለከተ በጅምላው ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ ‹‹ሁሉም የሚመለከተው አካል ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ ያ ካልሆነ የተሳሳተ ትርጉም ይሰጠዋል›› ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍትሐዊ ያልሆነ ግብር ተተመነብን ያሉ ነጋዴዎች እርምጃ ተወሰደባቸው
Share