January 26, 2019
2 mins read

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እስከዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን ህግ ተቃውሟል

93876

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እስከዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን ህግ ተቃውሟል፡፡ የተቃወመውም በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአብላጫ ድምፅ የፀደቀውን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅን ነው፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

የክልሉ ምክር ቤት አዋጁ ‹‹ህገ መንግስቱን ስለሚፃረርና ህገመንግስቱን ስለሚጥስ በሕገመንግስቱ አንቀፅ 9/1 መሰረት በክልሉ ውስጥ እንዳይፈፀምና ወደ ተግባር እንዳይገባ›› የሚል ውሳኔ በትላንትናው እለት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። 

ይህ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀበት ወቅትም ሁሉም የትግራይ ክልል የምክር ቤቱ አባላት ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ድርጊት ትግራይ ክልል በፌዴራል መንግስት ለመመራት ፈቃደኛ ለመሆኑን ማሳያ መሆኑን የጠቆሙት የፖለቲካ ታዛቢዎች የህወሀት አመራሮችን የመጨረሻ ትእቢት እንደሚያመላክትም አስረድተውናል፡፡ አንድ ክልል በፌዴራል ስርአቱ ህግ ካልተገዛ ራሱን ከፌዴራል አስተዳደሩ እያገለለ ለመሆኑ ጠቋሚ በመሆኑ ከወዲሁ ሊታሰብበት እንደሚገባ ታዛቢዎቹ ተናግረዋል፡፡ በተወካዮች ምክር ቤት ካለው 547 መቀመጫ ውስጥ የትግራይ ክልል ድርሻ 38 ብቻ በመሆኑ ቀሪዎቹ በሚወስኑት ማናቸውም ውሳኔ የመገዛት ግዴታ አለባቸው፡፡

93867
Previous Story

የመንግስቱ ኃይለማርያም የቀኝ እጅ የነበሩት ሻምበል ለገሰ አስፋው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

93879
Next Story

‹‹ሀገርን ለማረጋጋት እየተሄደበት ያለው እርምጃ ግን አዝጋሚ ነው›› አረጋሽ አዳነ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop