የመንግስቱ ኃይለማርያም የቀኝ እጅ የነበሩት ሻምበል ለገሰ አስፋው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

 

በደርግ ዘመን ከፍተኛ የስርዓቱ ባለስልጣን እና የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ቀኝ እጅ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሻምበል ለገሰ አስፋው አረፉ:: 

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 3 ቀን 1999 ዓ.ም. የፌዴራሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው ተከስሰው በነበሩት የደርግ ባለሥልጣናት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን ከሰጠ በኋላ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጡ ከወሰነባቸው የደርግ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የነበሩት ሻምበል ለገሰ አስፋው 20 ዓመታት ከታሰሩ በኋላ በአመክሮ ከ እስር መፈታታቸው ይታወሳል::

ሻምበል ለገሰ አስፋው ደርግ 108ቱ መስራች መስራች ወታደራዊ መኮንኖች አንደኛው ሲሆኑ የደርግ ወታደራዊ ንዑስ ኮሚቴ አባል፣ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የድርጅት ርዕዮተ ዓለም መምሪያ ሃላፊ የነበሩት ሻምበል ለገሰ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ ከተያዙ በኋላ ለረጅም አመታት በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወቃል:

ሻምበል ለገሰ አስፋው የ4 ሴት ልጆች እና አንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ::  በኮሪያ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ አርፈዋል::

ሻምበል ለገሰ በትግራይ የተፈጸመውን የሐውዜን ጭፍጨፋ መርተውታል በሚል ክስ ሲቀርብባቸው ቢቆይም; ነባሩን የህወሀት አመራር አቶ ገብረመድህ አርአያን ጨምሮ በርካታ ሕወሓትን ጥለው የወጡ የቀድሞው የድርጅቱ ባለስልጣናት፤ ለዓለማቀፉ ህብረተሰብ የድጋፍ  መጠየቂያ እንዲሆን በህወሀት  ሰዎች በከፍተኛ ዝግጅት በዘመናዊ ካሜራ ለተቀረጸው  የሀውዜን ጭፍጨፋ ዋነኛው ተጠያቂ፦ የህወሀት አመራሮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲከሱ መቆየታቸው ይታወሳል::

የህወሓት አባት የሚባሉት አቶ ስብሃት ነጋም የሐውዜን ጭፍጨፋ ጀርባ የ እስራኤል እጅ እንዳለበት በአደባባይ መናገራቸው ይታወሳል:: ስብሃት የህወሀት 40ኛ ዓመቱ በተከበረበት ወቅት  የደርግ 604ኛ ኮር የተደመሰሰበትን ወታደራዊ ሳይንስ አስመልክቶ  በሽሬ ከተማ በተሰናዳ መድረክ ላይ ባደረጉት ገለጻ “የቀዝቃዘውን ጦርነት ማክተም ተክትሎ ታላቋ ሶቪየት ህብረት መፈራረስ ጀመረች:: ክስተቱን ተከትሎ ሲቪየት  ከኢትዮጵያ እየወጣች በመምጣቷ በእሷ እግር የተተካው የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ ይለግስ የነበረውን እርዳታ  አቋረጠ:: ይህን ዓለማቀፍ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምእራቡ ዓለም እና እስራኤል የደርግ ወዳጅ ሆኑ:: 

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንኳን አገር ቤተሰብ መምራት አትችልም - የአቶ አብይ አህመድ የፓርላማ አሳዛኝና አስቂኝ ጥቅሶች

የደርግን መውደቅ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ ፖለቲካል ሀይል አሰላለፍ በመፍራት እስራዔልና የምእራቡ ዓለም  ደርግን ወዳጅ አድርገው በኛ የግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ  እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” የሚሉት ስብሃት “በወቅቱ ህወሀት ወታደራዊ አቅሙ እየጠነከረ በመምጣቱ አሜሪካና እስራዔል ድንጋጤ ውስጥ ገቡ:: በወቅቱ  ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምእራብ ሀገር የለም፤ሁሉም የሚችለውን አድርጓል፣ አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እስራዔል  ግን የተለዬ ሚና ወሰደች:: አሜሪካ አንድ ጊዜ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን ጠራችን:: ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር ሲያስጠራን የደርግ ልኡካን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን ያገባችሁዋል አሉን፤ወደ ለንደን ስንሄድ ግን ሁሉን ነገር ስለጨረስን ደርግን ጥለን ነበር::  እስራዔል ግን ወደ ሮም ከመሄዳችን በፊት ደርግን ማስታጠቅ ጀምራ ነበር:: ደርግም የታጠቀውን ክላስተር ቦንብ ጁን 22፣ 1988  ዘውዜን በገበያ ቀን ህዝቡ ላይ አዘነበው:: በጥቃቱ ከ2 ሺ 500 በላይ ህዝብ አልቋል:: ይህ ሁሉ የህዝብ እልቂት በ እስራኤል አስታጣቂነት የተፈጸመ ነበር” ሲሉ በንግግራቸው ክስ ማቅረባቸው ይታወሳል::

Share