በኢትዮጵያ የታገቱትን 4 ህንዳዊያን ለማስለቀቅ 12.4 ሚሊዮን ብር ተጠየቀ

ከታገቱ በርካታ ቀናትን ያስቆጠሩት አራት ህንዳዊያን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ የተደረገው ድርድር ያለውጤት ተበተነ፡፡ ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አርብ ሲሆን በዚህ ድርድር ወቅት የህንድ ኤምባሲና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ተወካዮች ቢገኙም ምንም መስማማት ሊደረስ አልቻለም፡፡ ህናዳዊያኑ ሊታገቱ የቻሉት የሚሰሩበት የህንዱ የኮንስትራክሽን ድርጅት ለሰራተኞቹ ደመወዝ ሳይከፍል ወራትን በማስቆጠሩ ነበር፡፡

 

የህንዱ ቢዝነስ ላይን ጋዜጣ እንደዘገበው እነዚህን ህንዶች ለመልቀቅ የድርጅቱ ሰራተኞች 12 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ጠይቀዋል፡፡ ከታገቱት ውስጥ አንዱ የሆነው ቻይታነያ ሀሪ ሲናገር ‹‹የህንድ ኤምባሲ በህይወት እንደምንቆይ ብቻ ማረጋገጫ ሰጥቶናል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንም  እንደማንገደል ነግሮናል›› ብሏል፡፡ እነዚህ ሁለት አካላት የታገቱበትን ካምፕ ደህንነት ከማረጋገጥ ውጭ እነሱን ለማስለቀቅ የሚያስችል ምንም አቅም እንደሌላቸውም አስረድቷል፡፡

 

ጉዳዩ ከአቅም በላይ በመሆኑም የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጣልቃ እንዲገባም ታጋቹ ጠይቋል፡፡ የተጠቀሰው ገንዘብ እስካልተከፈለ ድረስ የመለቀቃቸው ነገር የማይታሰብ እንደሆነም ለዜና ምንጩ ተናግሯል፡፡ የህንዱ አይኤል ኤንድ ኤፍ ኤስ ኩባንያ የመንገድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን ደመወዝ ያልከፈለው በመክሰሩ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ዘግበን ነበር፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=Pe4vPoSA5JM&t=223s

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ሞት ያሳስበኛል!” የኢሱ መግለጫ የኤርትራ | ታሪክ ተሰርቷል ባድል ተሳካ- ጎጃም አብይ ወደቀ- ፋኖ በደማቅ አስመረቀ ስራው ተሰራ
Share