እምቦጭ በአባይ ወንዝ ላይም አደጋ ጣለ

December 27, 2018

በተለይ በመስኖ፣ በአሳ ማስገር እና በእንስሳት ህልውና  ለበርካታ አርሶ አደሮች የግብርና እና የህይወት መሰረት የሆነው አባይ ወንዝ በ እንቦጭ አረም እየተወረረ ነው:: አባይ ወንዝንየኑሯቸው መሰረት ካደረጉት መካከል በባሕር ዳር ከተማ የሰባታሚት ቀበሌ ነዋሪዎችም ለአብመድ ጋዜጠኞች  እንደተናገሩት አሁን ላይ እምቦጭ ከጣና አልፎ ለአባይ ወንዝም ሥጋት ሆኗል፡፡ ከሶስት ዓመታት ወዲህ ግን የእንቦጭ አረም በአባይ ወንዝ ላይ በመከሰቱ ከውኃው ሲያገኟቸው የነበሩትን ጥቅሞች እያጡ ነው፡፡ “እምቦጭ በእንሰሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ፤ የውኃውን መጠንም እየቀነሰው ይገኛል፡፡” ብለዋል ነዋሪዎቹ:: 

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ፣ ጽዳት እና ውበት ጽ.ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት የኔው እንደተናገሩት ከጣና አልፎ በአባይ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ ለማስውገድ ለሶስተኛ ጊዜ በዘመቻ ተሰርቷል፡፡እምቦጭ በተከሰተባቸው ቀበሌዎች አዋሳኝ የሚገኘውን ህብረተሰብ በማነሳሳት እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ አሁን ላይ የሰው ጉልበትን፣ ልምድ ያላቸው ዋናተኞችን እና ጀልባዎችን በመጠቀም ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ዳዊት አስታውቀው  የውኃው መጠን ሲቀንስ ደግሞ ማሽን አቀናጅቶ ለመጠቀም እንደታሰበ ተናግረዋል፡፡

ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ(ፔዳ ግቢ) አካባቢ እስከ አንዳሳ ቀበሌ ድረስ በአባይ ወንዝ ላይ የተከሰተው እምቦጭ 163 ሄክታር መሬት ሸፍኗል፡፡ እስካሁን በተደረገው የማጽዳት ሥራ 1ነጥብ 5 ሄክታር የሚሆነውን ማስወገድ እንደታቸለ የአካባቢ ጥበቃ፣ጽዳትና ውበት ጽ.ቤት ማስታወቁን አብመድ ገልጿል::

https://www.youtube.com/watch?v=rcbWeNfbu_o&t=32s

93385
Previous Story

ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ወደ ጦርነት የሚያስገቡ  እንቅስቃሴዎች እያደረገ መሆኑ ተነገረ

93391
Next Story

በዶክተር አብይ የተሾሙት የአምባሳደሮች ምደባ ይፋ ሆነ

Go toTop