ስንትና ስንት ጉድ እየሰማን ስንትና ስንት መስከረም እየጠባ እንደሆነ እናንተም ታውቃላችሁ፡፡ አሁን ደግሞ ሌላውን ሰሞነኛ ጉድ ባይናችን በብረቱ እያየን የመስከረም መምጣት ሳያስፈልገን በየሣምንቱ አዳዲስ ጉዶችን ለማስተናገድ ተገደናል፡፡
የበረከትና የመለስ ፍቅር መቼስ ለጉድ ነው፡፡ በረከት መቀሌ ላይ ለመሰሎቹ እያቀረበው ባለው “ጥናታዊ ዘገባ”ም አፍ መክፈቻው ሁሉ መለስ ሆኗል፡፡ በአማራ ላይ ዕልቂትንና የዘር መድሎ ያወጀውን መለስ “አማራው” በረከት እንዲህ ለአምልኮት በሚደርስ ደረጃ ማፍቀሩ መብቱ ቢሆንም አማራን ስላለመወከሉ ግን በዚህ ብቻ መረዳትና ይህን ሰውዬ በአማራ ጠላትነት መፈረጅ ይቻላል፡፡ የሁለቱን ፍቅር በበኩሌ በተለዬ አቅጣጫም አየዋለሁ፡፡ የጫካ ነገር አይታወቅምና በሌላ ነገር እስክንጠረጥራቸው ድረስ እንዲህ ብን ያሉበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ አታማትብብኝ – ኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት ስትገዛ የኖረችው ከመልካም ቤተሰብ ባልተወለዱ፣ ከመደበኛ ሕይወት ባፈነገጡ፣ ሀገርንና ሕዝብን በሚጠሉ፣ ሃይማኖት በሌላቸው፣ ከአወንታዊ ዕውቀትና ትምህርት ጋር በተጣሉ ፍናፍንትና ሶዶማውያን የባንዳ ልጆች በመሆኑ እነዚህን የአጋንንት ልጆች በብዙ መጥፎ ነገሮች መጠርጠር ነውር ሊሆን አይገባም፡፡ እናም በኔም ሆነ በአስተያየቴና በግምቴ ላይ ቅሬታ አይኑርህ፡፡
ለማንኛውም “ጅብ በማያውቁት ሀገር…” እንደሚባለው በረከት አድማጭ አግኝቶ መቀሌ ላይ ዲስኩሩን እየለቀቀ ነው – ሊያውም በባዶ ኩራት እየተኮፈሰና ባዶ ብርጭቆ ውኃ እየጠጣ፡፡ የማይለው የለም – አድማጮቹም እንደሱው ባዶ መሆናቸው ይገርማሉ – ተያይዘው ባዶ፡፡ በየጊዜው መጽሐፍ መለቅለቁን ደግሞ ተያይዞታል፡፡ በፍሬ ፈርስኪ የተራ ውሸቶች ቃርሚያ የተሞሉ ፀረ- ኢትዮጵያ መጻሕፍቱን ወቅት እየጠበቀ ያስመርቃል፡፡ አንባቢ እስካገኘ ያስመርቅ፤ጥሩ ነው፡፡ ያጣነውስ እንደርሱ ያለ ደራሲ ምሁር አይደል?
በረከት እንደሚለው አማራ ሆኖ ለምን ፀረ-አማራ አቋም እንደሚያራምድ ገብቶኝ አያውቅም፡፡ በረከት በስሜት አማራ መሆን ስለፈለገ ብቻ አማራ ነው አልኩ እንጂ አማራ እንዳልሆነና የወያኔ ትግሬን የበላይነት ለማንገሥና አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በብአዴን ስም ወደ አማራ ምድር መግባቱን አላጣሁትም፡፡ በበኩሌ አንድ ሰው እንኳን አማራ ዛፍም እሆናለሁ ቢል ምርጫው የርሱ ነው፡፡ ግን ዛፍም ሆነ አማራ እሆናለሁ ካለ በኋላ ዛፍንና አማራን ለማጥፋት ከተሰለፉ ኃይሎች ጋር ወግኖ እነሱን ሊያጠፋ ከቆረጠ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ግፍም ነው፡፡ ተመሳስሎ በመግባት “የኔ ነው” የሚሉ ወገኖችን ማጥቃት ሥርየት የሌለው ኃጢኣትም ነው፡፡ እንጂ በረከት በዘመኑ ቋንቋ ኤርትራዊ መሆኑን ከጥት ጀምሮ ማንም ያውቃል – የለዬለት ማንነቱን የተረዳንበትን የአሁኑን ጥርት ያለ ሁኔታ ምሥጋን ይግባውና አስቸግሮን የነበረው የሌሊት ወፍነቱ ነበር – የሌሊት ወፍ በራሪ ሲሏት አጥቢ፣ አጥቢ ሲሏት ደግሞ በራሪ ወፍ የምትሆን የሁለት ዓለም ሰው ማለቴ እንስሳ መሆኗን ልብ ይሏል በእግረ መንገድ፡፡ የኤርትራ ሰው መሆኑ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ ከየትም ቢመጣ አማራን ሊወክልና ሊሆንም ይችላል – ነገር ግን ይህ የማስመሰል ሂደት የወያኔን እምነትና አስተሳሰብ እንዲሁም ህገ መንግሥት ተብዬውን የቁጩ ሰነድ በእጅጉ ይጣረሳል፡፡
“ወዶ አይስቁ” ይባላል፡፡ ሰሞነኛው የትግራይ ነገር ሳንወድ በግዳችን እያሣቀን ነው – የምንስቀው ግን ለሰዎቹ ሀፍረትና ይሉኝታ የለሽነት በመሳቀቅም ጭምር ነው – የባለጌዎች የጥፋት ድግስ ምን ሊያስከትል እንደሚችል በማሰብ ነገንም በመፍራት፡፡ አጥፍቶ ጠፊዎች እንኳን ለሌላ ሰው ነፍስ ለራሳቸውም ነፍስ እምብዝም አይጨነቁም፡፡
ተረቶችም ለካንስ ቦታ ይለዋወጣሉ፡፡ ቀደም ሲል ዕብሪተኛው ወያኔ ከኛዎቹ አፋሮች ይሁን ከዐረቦች ተውሶ “ግመሎቹ ይጓዛሉ፤ ውሾቹም ይጮሃሉ” የሚል ተረት ያዘወትር ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ያ ተገልብጦ “ውሾቹ ይጓዛሉ፤ ግመሎቹም ይጮሃሉ” የሚመስል አዲስ ተረት የተፈጠረ ይመስላል፡፡ ዓለም ተለዋዋጭነቷን አትረሳምና ዛሬ እንዲህ ሆነ – ይሆናል ብለን ሳናስብና ብናስብም በዚህን ወቅት ይደረጋል ብለን ፈጽሞ ባልጠበቅነው ሁኔታ፡፡ ለአንድዬ ከቶ ምን ይሳነዋል?
አዎ፣ ውሾች የነበሩት የግመልን ቦታ ወስደዋል – ግመል የነበሩት ደግሞ የውሾችን፡፡ ጉዞውም ጩኸቱም ቀጥሏል፤ ምክንያቱም ሕይወት አንድ ቦታ ቀጥ ብላ አትቆምምና፡፡ እንደሚባለው ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነውና ብዙ እናይ ይሆናል፡፡
አንድ ትንቢታዊ ማሳሰቢያ ልስጥ፡፡ ለውጡ በምንም መንገድ አይቀለበስም፡፡ ግን አሟረትህ አልባልና ሊከሽፍ የሚችልበት መጥፎ አጋጣሚ ይታየኛል – የክሽፈትንና የቅልበሣን ጽንሰ ሃሳቦች መለያየት ያዙልኝ ታዲያ፡፡ ለምን ይከሽፋል ቢባል የሀገራችን ችግር ለውጥን ማምጣት አለመቻል ሳይሆን የመጣን ለውጥ በተፈለገው መንገድ ማስኬድ አለመቻል እንደሆነ በኔ ሕይወት እንኳን ከሁለትና ምናልባትም ከዚያ በላይ በመታዘቤ ነው፡፡ ስለዚህ ዋናው ሥጋት ያለፈው ችግር ይመለሳል ሳይሆን ችግሩ በምን መልክ ተሻሽሎ ወይም ተባብሶ ይቀጥላል የሚለው ነው፡፡ እንጂ ከእንግዲህ ወያኔ አራት ኪሎን ያያታል ማለት ዘበት ነው፡፡
በፈጣሪ ጥበብና በሚሊዮኖች የሕይወትና የኅሊና እንዲሁም የሥነ ልቦና (ቀውስ) መስዋዕትነት የተገኘው ይህ የነፃነት ጭላንጭል በሌላ የዘረኝነት አዙሪት ተጠልፎ ወደባሰ የጭቆናና የጎሠኝነት አዙሪት እንዳንገባ በጸሎትም፣ በብልኃትም፣ በገንዘብም፣ በጉልበትም፣ በጥርስም በድድም መተጋገዝ ይኖርብናል፡፡
ትንሽዬ ማሳሰቢያ ልስጥ – ማለባበስ ይቅር፡፡ መንግሥት የሚሾማቸውን ሰዎች ይወቅ፡፡ ምድረ ውሪን እየሾመ በሕዝብና በሀገር የተስፋ ጭላንጭል ላይ ቀዝቃዛ ውኃ አይከልብስ፡፡ አንድ በጣም የማውቀው ትልቅ ሹም ለምሣሌ ለተመደበበት ቦታ ስለመብቃቱ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ በዕድሜ ጎልማሣነቱ ወይም ጎሣዊ ተዋፅዖው ወይም ለአንዱ የለውጥ አርበኛ ያለው ቀረቤታ ለዚያ ቦታ አሳጭቶትና አብቅቶት ካልሆነ በስተቀር በምንም መንገድ እዚያ ቦታ ሊያንጠለጥለው የሚያበቃ ሀገራዊና ልምዳዊ ረድዔት በረከት አለው ብየ አላምንም – ምቀኝነት ምናምን አይደለም፤ ከዚያ ዓይነቱ የኢትዮጵያዊነት ልዩ መታወቂያ ማምለጥ ከባድ ቢሆንም ብዙም ልታማበት አልፈልግም፡፡ ምን ልጠቀምበት?
በቂም በቀል ተነሳስቶ በሀሰተኛ የፖለቲካ ወንጀል አንድን ሰው ያሳሰረ ሰው – ለዚያውም በዚያ የ97 ምርጫ ወቅት – በዚያ ወያኔ በጥርጣሬና በዘራቸው ሳቢያ ስንቶችን በፈጀበት ክፉ ዘመን – መለወጡንና ንስሃ መግባቱን እርግጠኛ ባልሆንኩበት ሁኔታ ተሹሞ ሳየው በውነትም ይቺ ሀገር የሰው ድርቅ መትቷታል አልኩ (ታሳሪው እንዴትና ማን እንዳስፈታው በቅርበት የማውቀው ታሪክ ነው)፡፡ በሌሎች ሰዎች የሚወራውን የሌሎች ዜጎችን ሹመትና የአሹዋሹዋም ሁኔታ ሁሉ ብናገር ችግሩ ብዙ ነውና ይቅር፡፡ እኔን ጨምሮ አንዳንድ ጦማሪዎች የምናየውን ሁሉ ላለመናገር ዝም የምንለውም ለጠላት ድንጋይ ላለማቀበል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መጠቆም እፈልጋለሁ፤ እንጂ ችግሮች የሉብንም ማለት ራስን ማታለል ነው፡፡ የአሠራር ችግሮች እየታረሙ መሄድ ግን ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ ደህና ደህና ሰዎችንና የተማሩ ዜጎችን በልመናና በማባበልም ቢሆን እያነጋገሩ መሾም ሀገርን ከዳግም ጥፋት ያድናል፡፡ የአንድ ሹም ደህና ሰው መሆን ያን እርሱ የሚመራውን መሥሪያ ቤትም መታደግ ነው፡፡ ዶ/ር ዐቢይ የመራቸውን መሥሪያ ቤቶች በወፍ በረር ቅኝት ለመረዳት ሞክሬያለሁ፡፡ በሥሩ ያሉ ሰዎችን እያረቀና እያስተካከለ ብዙ መልካም ሥራዎችን እንዳከናወነ ተገንዝቤያለሁ፡፡ ችግሩ አንድ ብቻ ሆነና በቶሎ እንዳያልቅብን ፈራሁ፡፡
… ትናንት ማታ በኢሳት የተከታተልኩት የነዶክተሮች ተድላ ወ/ዮሐንስና አብርሃም ዓለሙ ውይይት እጅግ የሚማርክ ነበር፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ አልኩ …. ግን ግን ይሄ ለአንዳንዶች የእግር እሳት ለአንዳንዶች ደግሞ የቀኝ እጅ የሆነ ኢሳት የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባይኖር ምን ይውጠን ነበር? ሳይደግስ አይጣላም ማለት አሁን ነው፡፡ … እነዚህን ብርቅዬ ልጆች እነዐቢይ ቢያገኗቸው እልል በቅምጤ ነበር፡፡ ተድላ ከአፉ ማር ነው የሚዘንበው – አብርሃምም፡፡ እባካችሁ ለኔ የምትሰውት አምስት ደቂቃ ይኑራችሁና በኢሜሌ ሰላምታችሁን ላኩልኝ – ስለመብርሃን ይሁንባችሁ – [email protected] በነዚህ ውዶች አንደበት ይፈስ የነበረው ማርና ወተት ስለቋንቋና ማኅበረሰብ ትስስር፣ ዋልጌና ስድ ፖለቲከኞች ለፍላጎታቸው ስኬት ሲሉ የዘር ቅስቀሳን እንዴት እንደሚጠቀሙበት የሚያብራራ … ነበር፡፡ … በዚህ ጉዳይ ብዙዎቻችን ብዙ ጊዜ ጮኸንበታል፤ ሰሚ ጠፋ እንጂ፡፡ በፈጣሪ ይሁንባችሁ የርዕዮት ዓለሙ ዝግጅት ላይ የቀረበውን ይህን ወርቅ ውይይት ያላያችሁ ካላችሁ ተጋበዙልኝ፡፡…
በረከት ትግራይ ላይ ሆኖ በስድብና በዛቻ የሚወርድበት አዴፓ ከወያኔ ወኪሎችና ተላላኪዎች ራሱን በአፋጣኝ ካላጸዳ አማራ በራሱ ልጆች ትብብር ግብኣተ መሬቱ ይፈጸማል፡፡ ተናግሬያሉሁ! ምላሤ ደግሞ ጥቁር ነው፡፡ ለምሣሌ ያ አቻምየለህ ታምሩ የተባለ አክቲቪስት በአዴፓ ውስጥ ስለመሸጉ ቀንደኛ የሕወሓት ሰዎች ዝርዝር ከነኃላፊነታቸው ጠቁሞ ነበር፡፡ አዴፓ ግን እነዚያን ሰዎች አቅፎ “ለውጥ እያካሄድኩ ነው” እያለ እያሳቀን ነው፡፡ ወንድሞቼ – አዴፓዎች ጥፋት ካለባችሁ በንስሃ ታጠቡና ወደ ሕዝቡ ግቡ እንጂ መንታ መንገድ ላይ ቆማችሁ ለውጡን አታጨልሙ፡፡ በአንድ ጊዜ ልጭና ጎፈሬ መሆን አይቻልም – ግንጥል ጌጥ ይሆናልና፡፡ “እንጠየቅ ይሆናል” ከሚል ፍራቻ የለውጡን ሀዲድ ጠበቅ አድርጎ ለመያዝ ፈራ ተባ የሚል ሰው ካለ ያ ሰው ለአማራ ብቻ ሳይሆን ለፌዴራል ተብዬው ሥርዓትም ትልቅ ችግር ነው – ከነጃዋር ባልተናነሰ የኢትዮጵያ ራስ ምታት፡፡ በኔ ግምት በዚህ ነጥብ ዙሪያ ኦሮሞ ተሽሎ ተገኝቷል፡፡ አዴፓ ግን ሲንከረፈፍ ይህን ዕድል እንዳያጣውና ለይቶለት ራሱንም ሕዝቡንም ወደ ባርነት እንዳያስገባው በጣም እፈራለሁ፤ ወደ ቀን ጅቦቹ እንዳንገባ በተለይ የአማራ ወጣትና ጉዳዩ የሚመለከተው የተፎካካሪ ጎራ ሁሉ ጠንቀቅ ብሎ ለውጡን ይጠብቅ – ያ አማራን የተሳደበው ሰውዬ – ማን ነበር ስሙ – አዎ፣ ዓለምነው መኮንን — ለአብነት አሁን በአደባባይ ቆሞ መሄድ ነበረበት? ይሙት እያልኩ አይደለም – ጠላቱ አይሙትና ይቆይልን፡፡ እርሱ ከሌለ በክፉ ቀን ማን ይሰድበናል? ማንስ ያዋርደናል? ግን ግን ማረሚያ ቤት ቢጤ መግባት አልነበረበትም?
…. ስለዚህ አዴፓ አሁንም ሁለት ነገር መውደድም ሆነ በጨለማና ብርሃን በሚመሰሉ ሁለት ምርጫዎች መሀል ተሰንቅሮ ማወላወል የለበትምና አንዱን ይሁን – ብዙ “አማሮች” ተስፋ እየቆረጥንበት መሆናችንን ተረድቶ አፋጣኝ የሆነ ራሱን የማስተካከል እርምጃ ይውሰድ፡፡ የከፈለውን ያን ሁሉ መራራ መስዋዕትነት የሚያጠይሙ የውስጥ ሁኔታዎችን በቶሎ ያርም፡፡ ይህ ወቀሳየ የወዳጅነት እንጂ የጠላትነት ምልክት ተደርጎ እንዳይታይብኝ ደግሞ፡፡ እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደርን መልመድ አለብን፡፡ በግልጽ መወቃቀስና ጆሮ መሰጣጣትም ብልኅነት እንጂ ክፋት የለውም፡፡ ፈረንጆች ቡጢ ቀረሽ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተው … አንዳንዴም ተቧክሰው … ሲያበቁ በኋላ ግን ፍቅራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ይሄ ኩርፊያና አሽሙር፣ ጥላቻና ቂም በቀልን የመሳሰለ አስጠሊታ ባህላችንም ይቅር፤ እየጎዳን ነውና እንጠየፈው፡፡ እስኪ ሰው እንሁን!
የተማረ ሰው ብዙ አለ፡፡ የተራበ ሰው የምግብ ምርጫ ውስጥ አይገባም፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው፡፡ ሀገራችን የሰው ርሀብና ጠኔ መትቷታልና የተማረና የበቃ ይሁን እንጂ የፖለቲካ አስተሳሰቡን በማየት ከኃላፊነት ማራቅ ወይም አለመሾም አግባብ አይደለም፡፡ በቀረቤታና በውዴታ ሳይሆን በ“ሜሪት” ወይም በችሎታ እንመን፡፡ ሙያውና የሀገርና የወገን ፍቅር ካለው፣ ሙስናን የሚጸየፍ ከሆነ፣ እንደተራው ሕዝብ እየተቸገረም ቢሆን በገቢው ብቻ የሚተዳደር ከሆነ… ማንም ኢትዮጵያዊ በተገቢው ቦታ ይሾም፡፡ በትግል ብዙ ጊዜ አብሮ ማሳለፍን እንደምክንያት በመቁጠር እርስ በርስ መሹዋሹዋም ሀገርን ያጠፋል እንጂ አያለማም፡፡ አካሄድን መመርመርና ማዘመን ከአዴፓም ሆነ ከሌሎች በብርቱ ይጠበቃል፡፡ የኃላፊዎችን “ፕሮፋይል”ና የሕይወት ውጣ ውረድም በጥልቀት መመርመር ይገባል፡፡ ስለሹሞች አስቀድሞ ከሕዝብ አስተያየት መሰብሰብም ጠቃሚ ነው፡፡ ዝም ብሎ ከየሥርቻው በአምቻ ጋብቻ እየጎተቱ፣ በመጠጥ ቤት የአምቡላና ቅራሪ ትውውቅ እየተሳሳቡ ሹመትን እንደቡና ቁርስ መከፋፈል ዛሬ ባይሆን ነገ ዳፋው ከባድ ነውና ይታሰብበት፡፡ ኢትዮጵያ ሰው አላጣችም፡፡ ሰው አላት፡፡ የሚያሠራ የመንግሥት አካል ነው የጠፋው፡፡ የተተበተበው ቢሮክራሲ ነው ያስቸገረን፡፡ ሙስናው ነው የጠመሰን፡፡ ተንኮልና ምቀኝነቱ ነው አላፈናፍን ያለን፡፡ ማይምነቱ ነው ያወከን፡፡ በቅርብ ከመጣብን ዘረኝነት ጋር ታዲያ…..
… እነ በረከት ግን ….ሆ!…. “ምንትስ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች” ብላ የተረተችው ማን ትሆን ግን? ልክ ሳትሆን ትቀራለች? ያገራችን ሁኔታ እኮ ቁልጭ ባለ ሁኔታ እየለየለት ነው…. ግን ግን ፌዴራል መንግሥቱ ለህገ መንግሥታችን ለምን አያከብርም? ሕወሓት ስንትና ስንት ዜጎችን ያሰቃየውና ያኮላሸው እኮ ህገ መንግሥቱን በማክበርና ለህገ መንግሥቱ ኅልውና ሲል ነበረ፤ ለህገ መንግሥቱ በጎዳና ነውጠኞች እንዳይናድ ሲል ነው እኮ ግብረ ሶዶማውያን መርማሪዎችን በየከርቼሌው መድቦ ነጭ ጥቁር፣ አጭር ረጂም ሳይባል የሰው ዘርን በሞላ ሲያዋርድ የነበረው፡፡ ታዲያ አሁን ለምን ህገ መንግሥቱ አይከበርም…? ምን ሽግር አለው? ሀገሪቱ እንዳትፈራርስ ህገ መንግሥቱ ይከበር እንጂ! ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም እንዴ ያ ሁሉ ሀፍትና ንብረት ወደ ትግራይ ሌት ተቀን የተጓጓዘው? ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም እንዴ 1.08 ትሪሊዮን ብር በወያኔ አባላት የተዘረፈው? ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም እንዴ የክልል “መንግሥታት” ሰፋፊ መሬቶች ለወያኔ ኢንቬስተሮች የታደሉት? ለህገ መንግሥቱ መከበር አይደለም እንዴ ከላይ እስከታች የወያኔ ትግሬ አባላት ባለሥልጣን እንዲሆኑ የተደረገው? ህገ መንግሥቱ ስለተከበረ አልነበረም ወይ እነስንሻውና እነታንጉት የመንግሥት ሥራ ለማግኘት ሲሉ ስማቸውን ወደ ጠንክርና ሐጎስ ሲቀይሩ የነበሩት? የምን ቀልድ ነው! ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም እንዴ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በማይማን ታማኝ የወያኔ ትግሬ አባላት ሲታጨቁ የነበሩት? ለህገ መንግሥቲ ለማክበር አይደለም እንዴ ካለምንም የሕዝብ ፈቃድ በጉልበት ብቻ ወልቃይትና ራያ እንዲሁም ሰሜን አፋር ወደ ትግራይ የተካለሉት? ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም እንዴ ኦሮሞና አማራን ለማጋጨት ብዙ ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገው? ህገ መንግሥቱን ለማክበር አይደለም ወይ ከሀገሪቱ 60 የጦር ጄኔራሎች ውስጥ 68ቱ ወያኔ ትግሬ የሆኑት? ለህገ መንግሥቱ መከበር አይደለም እንዴ ሜቴክ ያን ሁሉ ምዝበራና ዘረፋ ያካሄደው? ለምን ልፋቱን ሁሉ መና እናስቀራለን? ህገ መንግሥቱን ለማክበር እኮ ነው በትግሬ ጄኔራሎችና ቱባ ቱባ የወያኔ ባለሥልጣናት ምክርና የሞራል ድጋፍ አብዲ ኢሌ በአሥር ሽዎች የሚገመት ሕዝብ በቁም ቀብሮ የጨረሰው! ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል፤ ምዕመናን … እንዲያውም ለዚህ ህገ መንግሥት መጣስ ተጠያቂዎቹ ለፍርድ ይቅረቡ! እንዴ ህገ መንግሥቱማ ይከበር እንጂ!