የቀድሞው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ ጠበቃ አቁመው እንዲከራከሩ ጊዜ ተሰጠ

ወደ ኬንያ ሊያመልጡ ሲሉ ዱከም ላይ የተያዙትየቀድሞው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በዛሬው ዕለትም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጅል ችሎት የቀረቡ ሲሆን አሁን በቁጥጥር ስር ካልዋለው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት ዋና ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ በመመሳጠር እና ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል እና ከሥራችው ላሉ ሰራተኞች ትዕዛዝ በማሰተላለፍ በህግ አግባብ መሰራት እና የህግ የበላይነትን ማክበር ሲገባችው :-
• ያለ አግባብ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ ዜጎችን በጨርቅ አፍነው በመውሰድ፣
• በህግ ባልተፈቀደ ድብቅ ቦታ ወስጥ እሰከ 5 ወር በማሰር ፣
• ተጠሪጣሪዎችን የወስጥ እግራችውን ገልብጦ በመግረፍ፣
• ብልታቸው ላይ ውሃ በማንጠልጠል ፣ ብልታችውን በፒንሳ በመሳብ፣
• ራቁታቸውን ቆሻሻ ውስጥ በመጣል ጉንዳን እንዲበሉ በማድረግ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ፡፡
• በተጨማሪም በተፈፀመባቸው ድብደባ ብዛትም የሞቱ ዜጎችም አሉ፡፡
• በሌላ በኩል ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ሄደው ህገ ወጥ መሳሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበርና ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲሳበብ ማድረግ በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸው እና ከፍተኛ የህዝብ ሀብት በሽብር ስም መዝብረዋል በማለት ፖሊስ ጥርጣሬውን ለችሎት አስረድቷል።
የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ከህግ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙና የተጠየቀው የ14 ቀን ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም ለ8 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ የፍርድ ቤት በሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. የመስቀል አደባባይ ዶ/ር አብይ አህመድን ለመግደል በተወረወረው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ፣ እንዲሁም ኮሎኔል ጉደታ ኦላናና ኮሎኔል ሰጠኝ ካሳዬ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ኮሎኔል ጉደታ ቴሌኮም የጥበቃና ደኅንነት ዲቪዝዮን ኃላፊ ሲሆኑ፣ ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡
በተለየ መዝገብ ወንጀሉን አቀናብረሀል በሚል ምርመራ ሲደረግበት የቆየው የቀድሞ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት ሰራተኛ ተስፈዬ ኡርጌ ላይ በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አቃቤህግ ክስ እንዲመሠርት ለዛሬ ጠዋት ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ሳያቀርቡት መቅረቱ ተሰማ:: በቀድሞው የደህንነት ኃላፊው ላይ ክሱ ሳይነበብ ለሰኞ ቢቀጠርም በሌላ ወንጀሎች ተጠርጥሮ አዲስ መዝገብ እንደተከፈትም ተሰምቷል::
https://www.youtube.com/watch?v=x9Np1L1BJWY

ተጨማሪ ያንብቡ:  238 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በአሸባሪው ህወሃት ዘረፋና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል

1 Comment

  1. ሻዕቢያ ወ- ወያነ ስልጣን ላይ ከተፈናጠጡበት ጊዝያቶች ጊዜ ጀምሮ አስመራ ውስጥ የነበሩትን ተጋሩ ቱጃሮችን ንብረታቸውን ቀምቶና, በተለይም መንጋጋቸውን እየተበረገዱ የወርቅ ጥርሳቸውን የተሰረቁትን ማስታወስና የተከናወነን ሌብነት አስመልክቶ Generalabrechnung የሚጀመር ከሆነ, አደራ ቅደም ተከተሉን እያከበርን መሆን ይኖርበታል, ማለትም በቅድሚያ 1991 ላይ መለስ ዜናዊ ኤርትራን ቆርጦ “ለኤርትራዊው” ኢሳያስ, ” ብቻ ኢትዮጵያን አትቀራመተኝ እንጂ ያውልህ ቁራጭ መሬት” ብሎ እንደ ቸሮታ ሲለግሰው, ይሄኛው ግን ምስጋና እንደማቅረብ ይልቅ, አስመራ ውስጥ የነበሩትን ተጋሩ ቱጃሮችን ንብረታቸውን ቀምቶና, በተለይም መንጋጋቸውን እየተበረገዱ የወርቅ ጥርሳቸውን የተሰረቁትን ማስታወስና ለዚህ ኢሰብአዊ ቅምያ በቅድሚያ ተጠያቂነቱን በኢሳያስ ላይ ጥሎ በኢንተርፕል እንዲፈለግና ሃላፊነቱን እንዲጠየቅበት ማድረግም የኢትዮጵያውያን ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት! መረሳት የሌለበት ጉዳይ, እነዚያ አስመራ ውስጥ ቱጃር የነበሩት ተጋሩ, ባዶ እጃቸውን ወደ ኢትዮጵያ ይባረሩና ለዘመናትም ላስቲክ “ቤት” ውስጥ በውርጭና በፅሃይ ተጠበሱ::

Comments are closed.

Share