October 8, 2013
5 mins read

Sport: “የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድንን እናከብራለን፤ ግን እናሸንፋቸዋለን” – ሳላዲን ሰኢድ

ከዳዊት በጋሻው

(የኢትዮጵያ ከሕዝብ ከብሄራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች ጋር ባሮ 90 ደቂቃ መጫወት አለበት)
Sport: "የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድንን እናከብራለን፤ ግን እናሸንፋቸዋለን" - ሳላዲን ሰኢድ 1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ተከላካይ ሳላህዲን ቤርጌቾ ጥቅምት ሦስት ቀን ለ 2014 ቱ የብራዚል ዓለም ዋንጫ በአዲስ አበባ ከናይጄሪያ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ« ምርጥ ብቃታችንን ሜዳ ላይ ማሳየት ከቻልን የናይጄሪያን ብሔራዊ ቡድንን እናሸንፋለን » በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እሁድ ከናይጄሪያ አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ጌታነህ ከበደ እንደማይሰለፍ የዋልያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ አቶ ታረቀኝ አሰፋ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፍ አቅም እንዳለው የተናገረው ሳላህዲን ብሔራዊ ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡ ቡድኑ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ የሚያደርግ ሲሆን ፤ በጠዋቱ ፕሮግራም የታክቲክ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የቴክኒክ ልምምዶችን እየሰራ ነው ብሏል።
«ድሉን ኢትዮጵያውያን ይፈልጉታል ፣ ለእዚህም ጠንካራ ልምምድ በማድረግ ላይ እንገኛለን ፤ በሜዳችን ጥሩ ተጫውተን ድል ማስመዝገብ እንደምንችል እተማመናለሁ » በማለት ተከላካዩ በጨዋታው ዙሪያ ያለውን አስተያየት ለሱፐር ስፖርት ሰጥቷል፡፡
በሌላ ዜና የቅዱስ ጊዮርጊስና የዋሊያዎቹ የግራ ተመላላሽ ተጫዋች አበባው ቡጣቆ ከናይጄሪያ ጋር ያለውን ጨዋታ በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ ለመድረስ መጓጓቱን ተናግሯል፡፡አበባው ከአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ ጋር መጫወታቸው ምንም አዲስ ነገር እንደሌለው ገልጾ፤ እርሱና የቡድን ጓደኞቹ ለወሳኙ ጨዋታ በራስ የመተማመን ስሜትን ማጎልበት እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡
«አሁን ዋናው ትኩረታችን ለመጪው የናይጄሪያ ጨዋታ ነው ፤ የ 2013 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዎች በመሆናቸው እናከብራቸዋለን። አሁን ናይጄሪያም እኛም ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ነው ዓላማችን፣ በእዚህ ላይ ታዲያ የቀደመ ታሪክ የሚጠቅም አይመስለኝም » በማለት ለሱፐር ስፖርት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
አበባው በተጨማሪ «ሁለታችንም ጨዋታውን በጣም እንፈልገዋለን። በእግር ኳስ የሚፈጠረው አይታወቅም። በቴክኒክና በታክቲክ በምንሰራው ልምምድ ደስተኛ ነኝ ፣ሁላችንም ለጨዋታው ጠንክረን እየሰራን ነው፤ እዚህ ደረጃ ይደርሳሉ ብሎ ግምት የሰጠን አልነበረም፣ነገር ግን በጠንካራ ሥራና በራስ መተማመን ከአስሩ ምርጥ የአፍሪካ ቡድኖች መካከል አንዱ ሆነናል» ብሏል። ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች እርሱም ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን አስመስክሯል፡፡
አበባው በጠንካራ የቅጣት መችነቱ ይታወቃል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ባደረጉት ጨዋታ ላይ በቅጣት በመታት ኳስ ፓርከር በራሱ ላይ ግብ እንዲያስቆጥር ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እሁድ ከናይጄሪያ አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ጌታነህ ከበደ እንደማይሰለፍ የዋልያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ አቶ ታረቀኝ አሰፋ ገልጸዋል። ጌታነህ በመብራት ሀይል ሜዳ ልምምዱን እያደረገ የሚገኘውን ብሄራዊ ቡድን ለመቀላቀል ዛሬ በስፍራው ቢገኝም በህመም ምክንያት ከዋሊያዎቹ ጋር ልምምድ መስራት አልቻለም።

1 Comment

Comments are closed.

8174
Previous Story

አሰቃቂ ሞት በሊቢያ ሰሃራ – ከዲጄ ቶም (ቪድዮ)

Yidnakachew
Next Story

አደባበዬቻችን እና መንገዶቻችን መሉሱልን ? !!!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop